ዜና
Archive

Month: June 2022

ለዓባይ ወንዝ አንዲት ጠብታ የማታበረክተው ግብፅ 100 በመቶ የወንዙን አጠቃቀም የመወሰን መብት ልትጠይቅ አትችልም -ቲቦር ናዥ

ለዓባይ ወንዝ አንዲት ጠብታ የማታበረክተው ግብፅ 100 በመቶ የወንዙን አጠቃቀም የመወሰን መብት ልትጠይቅ አትችልም ሲሉ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቀድሞው የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናዥ ገለጹ። ቲቦር…

በአፋር ክልል ተይዘው ያሉ ዘጠኝ ሺህ የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች እንዲለቀቁ ኢሰመኮ ጠየቀ

በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ተይዘው ያሉ ዘጠኝ ሺህ የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች በአፋጣኝና ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጠየቀ። ኢሰመኮ በሰመራ ከተማ ሰመራና አጋቲና ካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙ…

ሱዳን ከትንኮሳ በዘለለ የያዘችው ተጨማሪ የኢትዮጵያ ግዛት የለም – መንግሥት

ሱዳን እና ኢትዮጵያ በሚወዛገቡበት አልፋሽጋ ድንበር ላይ የደረሰ ጥቃትም ሆነ ተጨማሪ የያዙት ቦታ እንደሌለ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሸን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ ለቢቢሲ ገለጹ። የሱዳን ጦር በድንበር ግዛቶች ላይ በሚገኘው…

ባለስልጣኑ ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት በሚፈጥሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ

ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት በሚፈጥሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡ ባለስልጣኑ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ÷በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የኢኮኖሚ አሻጥር ለመፍጠር ሲባል ሰው ሰራሽ…

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ የሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች

– ሕግና ስርዓትን የማስከበር ስራዎች አፈጻጸም በመላ ሃገሪቱ የሚገኘው መላው ህዝብ፤ የፀጥታና የደህንነት አካላትእንዲሁም የፖለቲካ አመራሩ ተቀናጅተው ባከናወኑት ስራ ለሰላምና ለህግ ማስከበር መልካም ተነሳሽነትና መነቃቃት ተፈጥሯል፡፡ ከአሁን በፊት የጎላ ችግር…

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት፤ መንግሥት ለሕዝብ ደህንነትና ሰላም ቅድሚያ በመስጠት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠየቀ

ገዢው ፓርቲ አባል የሆነበት ምክር ቤቱ መንግስት ግዴታውን ባለመወጣቱ ችግሮች መባባሳቸውንም ገልጿል ም/ቤቱ፤ መንግስት “የደህንነት ስጋት አለብን” ላሉ ዜጎች ፈጣን ምላሽ መስጠት ነበረበት ብሏል ገዢው ፓርቲ አባል የሆነበት የፖለቲካ ፓርቲዎች…

በጊምቢው ጥቃት በተገደለችው እናቷ እቅፍ የተገኘችው የ15 ቀኗ ጨቅላ ሕጻን

አይሻ ሰይድ የተወለደችው በደቡብ ወሎ ዞን፣ አርጎባ ወረዳ ውስጥ ነው። እዚያ ትወለድ እንጂ እድገቷ ግን በምዕራብ ወለጋ፣ ጊምቢ ወረዳ ፣ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ ነው። ወደዚያ ያቀናችው በ1990 ዓ.ም ነበር። ያኔ…

ሱዳን የኢትዮጵያ ሠራዊት ወታደሮቼን ገደለ ስትል ከሰሰች

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ምርኮኛ የነበሩ ሰባት የሱዳን ወታደሮችን እና አንድ ሲቪል ገድሏል ስትል ሱዳን ከሰሰች። የሱዳን መንግሥት በመገናኛ ብዙኃን ገጹ እንዳሰፈረው፣ አንድ ሲቪልን ጨምሮ ሰባት ወታደሮቹ በኢትዮጵያ መከላከያ ተገድለዋል። ትላንት…

አገራዊ የምክክር ኮሚሽን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቹን አጠናቆ ወደ ዝግጅት ምዕራፍ መሸጋገሩን ገለፀ

አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በአራት ምዕራፎች የተከፈሉ ተግባራት እንዳሉትና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቹን አጠናቆ ወደ ዝግጅት ምዕራፍ መሸጋገሩን የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለፀ፡፡ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ…

የኢዜማ የፓርላማ አባላት ጠ/ሚኒስትሩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠየቁ

የኢዜማ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጠቅላይ ሚንስትሩ ለምክርቤቱ ስለ ሀገራዊው የሰላም እጦት እና የዜጎች ጅምላ ጭፍጨፋ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጡ በምክር ቤቱ አሠራር መሠረት ጥያቄያቸውን በጽሑፍ አስገብተዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ አብን…

መንግስት በኦሮሚያና ጋምቤላ ክልሎች ”የጅምላ ግድያ” የፈፀሙት ለፍርድ እንዲያቀርብ የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጠየቀ፡፡

ምክር ቤቱ ይህን የጠየቀው ”በንፁሃን ዜጎች ላይ በአሸባሪዎች እየተካሄደ ያለው ጭፍጨፋ አጥበቀን እናወግዛለን!” ሲል ሰይሞ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣውና ለአሻም በላከው መግለጫ ላይ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች…

አብን አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎን ወቀሰ

አብን አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎን ወቀሰ ~ የዘር ተኮር ጭፍጨፋው በአጀንዳነት ተይዞ ለውይይት እንዲቀርብ ጠየቀ፣ ~ ጠ/ሚ ዐብይም ስለጉዳዩ ፓርላማ ቀርበው እንዲያስረዱ ጠይቋል፣ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ…

ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ600 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ!

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የ600 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ።ከ600 ሚሊየን ዶላር ውስጥም 200 ሚሊየን ዶላሩ በድጋፍ መልክ የተገኘ ነው ተብሏል፡፡ 400 ሚሊየን ዶላሩ በብድር መልክ የተገኘ መሆኑን…

የኢትዮጵያ አየር ሀይል ያሰለጠናቸውን አብራሪዎች እያስመረቀ ነው

‘’ነብሮች 2014’’ በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ አየር ሀይል በበረራ ሙያ ያሰለጠናቸውን አብራሪዎች እያስመረቀ ነው። በምረቃ መርሐ ግብሩ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ የመከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላን ጨምሮ…

የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ጀመረ

የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴው በተለያዩ ወሳኝ አገራዊ አጀንዳዎችና የፓርቲ ሥራዎች ላይ ተወያይቶ በቀጣይ ስለሚከናወኑ ተግባራት አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከቀናት በፊት…

በምዕራብ ወለጋው ጥቃት ወቅት ታግተው የተወሰዱ ሰዎች እንዳሉ ተገለጸ

በምዕራብ ወለጋው ጥቃት ወቅት ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች በታጣቂዎቹ ታግተው መወሰዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን አመለከተ። ኮሚሽኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉበትን ጥቃት አስመልከቶ ባወጡት መግለጫ ላይ እንዳመለከተው በርካታ ሰዎች…

ወደ ትግራይ ክልል በሚጓጓዙ ነገሮች ላይ የተጣሉ ጥብቅ ፍተሻዎች እንዲላሉ የአውሮፓ ህብረት ጠየቀ

የአውሮፓ ህብረት ለትግራይ አድልቷል በሚል የሚነሱ ጥያቄዎችንም አስተባብሏል ትግራይ ክልል ባንክ እና ቴሌኮምን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶች እንዲጀመሩም ህብረቱ አሳስቧል ወደ ትግራይ ክልል በሚጓጓዙ ነገሮች ላይ የተጣሉ ጥብቅ ፍተሻዎች እንዲላሉ የአውሮፓ…

ባንኩ የወርቅ አምራቾችን ለማበረታታት ከዓለም አቀፍ የወርቅ ገበያ ላይ የ35 በመቶ ጭማሪ አድርጎ ለመግዛት መወሰኑን ገለፀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወርቅ አምራቾችን ለማበረታታት ከዓለም አቀፍ የወርቅ ገበያ ላይ የ35 በመቶ ጭማሪ አድርጎ ለመግዛት መወሰኑን አስታወቀ። የባንኩ የከረንሲ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ አበበ ሰንበቴ በጉዳዩ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው…

ቻይና በፈረንጆቹ 2028 የመጀመሪያውን የጠፈር የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ልትገነባ ነው

ቻይና በፈረንጆቹ 2028 የመጀመሪያውን የጠፈር የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለመገንባት ማቀዷን አስታወቀች። የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ጣቢውን በህዋ ላይ ለመገንባት የሚያስችል ደረጃ ላይ መድረሷን የቻይና የሕዋ አካዳሚ ቴክኖሎጅ አስታውቋል። በሕዋ ላይ…

በኦሮሚያና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ተጨማሪ ኃይል ካልተሰማራ ተጨማሪ ጥቃት ሊፈጸም ይችላል – ኢሰመጉ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሚዥንጋ ወረዳ ተጨማሪ ኃይል ካልተሰማራ ተጨማሪ ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አስታወቀ፡፡ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ሰኔ…

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ከተፈቀደላቸው በጀት በላይ የተጠቀሙ 24 ተቋማት መገኘታቸውን አስታወቀ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ከተፈቀደላቸው በጀት በላይ የተጠቀሙ 24 ተቋማት መገኘታቸውን አስታውቋል። የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስርያ ቤት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ እያቀረበ ባለው ሪፖርት በ24 መሥሪያ ቤቶች በልዩ ልዩ የሒሳብ መደቦች…

“መንግስት ለሚረግፉ ዜጎቻችን ህይወት ተጠያቂ ነው” ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ዜጎች ላይ እየደረሱ ያሉትን ጭፍጨፋዎች በፅኑ ያወግዛል፡፡ እንዲህ አይነት ጭፍጨፋዎች እንዳይፈጠሩ አስቀድሞ መስራት ያለበት መንግስት ለሚረግፉ ዜጎቻችን ህይወት ተጠያቂ መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን፡፡…

ጠ/ሚ ዐቢይ “የሰው ልጆችን ህይወት የሚቀጥፍ ዘግናኝ ድርጊት አንታገስም” አሉ

ጠ/ሚ ዐቢይ “በንጹሃን ዜጎች ላይ በህገወጥና በኢ-መደበኛ ኃይሎች የሚደርስ ጥቃት ተቀባይነት የለውም” ብለዋል በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮና የኦሮሚያ ክልል አስታውቀዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “የሰው…

በመዲናዋ 3ኛው ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ዘመቻ ተጀመረ

በአዲስ አበባ የ3ኛ ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ዘመቻ መሰጠት ተጀምሯል፡፡ ክትባቱ ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ዕድሜያቸው12 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆናቸው ሁሉ በሁሉም የመንግስት ጤና ጣቢያዎችና በተመረጡ ጊዜያዊ…

የስፖርት ውርርድ ወይም ቤቲንግ እንዲታገድ እየሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገለፀ

የስፖርት ውርርድ ወይም ቤቲንግ እንዲታገድ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቀ። በሚኒስቴሩ የወጣቶች ስብዕና ልማት ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ አበበ ሃይማኖት እንደተናገሩት÷ ከታዳጊዎች እና ወጣቶች ስብዕና ግንባታ እንዲሁም…

ብሪታንያ በሩሲያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ላይ ማዕቀብ ጣለች

ከአሁን ቀደም በሩሲያ ቱጃሮች ላይ ማዕቀቦችን መጣሏ ይታወሳል ማዕቀቡ የፕሬዝዳንት ፑቲን ደጋፊ ናቸው በሚል የተጣለ ነው ብሪታንያ በሩሲያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ክሪል ላይ ማዕቀብ ጣለች፡፡ ማዕቀቡ ፓትርያርክ ክሪል የሩሲያ ጦር በፕሬዝዳንት…

ተመድ ስለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ያወጣውን ሪፖርት ኤርትራ አልቀበለውም አለች

ተመድ ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት “በኤርትራ ያለው የስበዓዊ መብቶች ጥሰት ሁኔታ እየተባባሰ ነው” ማለቱ ይታወሳል ኤርትራ “በሰብዓዊ መብቶች በኩል ያሉት ጉድለቶች”ን ለማሻሻል እየሰራሁ ነው ብላለች ኤርትራ በሀገሪቱ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታን…

አምባሳደር ስለሺ በቀለ ከአምባሳደር ቲቦር ናዥ ጋር ተወያዩ

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ስለሺ በቀለ ከቀድሞው የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ቲቦር ናዥ እና ከቴክሳስ የቴክኖሎጂ እና አንግሎ ስቴት ዩኒቨርሲቲዎች 15 ተማሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡ በዚህ ወቅት…

የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ሀይል በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንዲሰማራ ፕሬዚዳንት ኬንያታ ጠየቁ

የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ሀይል በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንዲሰማራ የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጠይቀዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል ያለበትን የፀጥታ ችግር ወደ ነበረበት ለመመለስ በማሰብ ነው የቀጠናው ተጠባባቂ ሀይል…

1ሺ 128 ዕርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቀለ ቀልጠው ቀሩ

«ለሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ትግራይ ከተጓዙት ሦስት ሺህ 297 ተሽከርካሪዎች አንድ ሺህ 128ቱ አልተመለሱም» ሰብዓዊ ድጋፍ ጭነው ወደ ትግራይ ከተጓዙት ሦስት ሺህ 297 ተሽከርካሪዎች ውስጥ አንድ ሺህ 128ቱ እንዳልተመለሱ የኢትዮጵያ አደጋ…

የትምህርት ሥርዓቱን የጥራት ችግር ለመፍታት የሪፎርም ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ – የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ ሰኔ 8/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ላይ የሚስተዋለውን የጥራት ችግር ለመፍታት የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ። የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አዲስ ከተመደቡት የከፍተኛ ትምህርት የቦርድ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ በዘርፉ የአምስት አመት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ማረጋገጥ በመሆኑ በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል። ለዚህ መሳካት አጠቃላይ የማኅበረሰቡና የትምህርት ተቋማት ድርሻ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው አዲስ የተመደቡት የከፍተኛ ትምህርት የቦርድ አመራሮችም የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል። የቦርድ አመራሮቹ በበኩላቸው በሚኒስቴሩ የተጀመረው የሪፎርም ሥራ እንዲሳካ የድርሻቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለይም የሙስና እና ብልሹ አሰራሮች እየተበራከቱ መምጣታቸውን ጠቅሰው ችግሩን ለመፍታት የጋራ ጥረት ይጠይቀናል ብለዋል። የትምህርት ተቋማት የእውቀት ማእከላት እንጂ የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈፀሚያዎች መሆን ስለሌለባቸው ለዚህም በልዩ ትኩረት መስራትን ይጠይቀናል ነው ያሉት። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከማንኛውም ተጽእኖ ነጻ የሆኑ ብቁ እና በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ምሁራን መፍለቂያዎች ሊሆኑ ይገባል ብለዋል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አዲስ የሥራ አመራር የቦርድ አባላት መመደባቸው ለተጀመረው ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል። የከፍተኛ ትምህርት የቦርድ አመራሮች ጋር የተደረገው የውይይት መድረክም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተጀመረውን የሪፎርም ሥራ ለማሳካት ያግዛል ብለዋል፡፡ የጎንደር ዩንቨርሲቲ ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ ተከተል ዮሀንስ (ፕ/ር) በበኩላቸውን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከሚነሱ አበይት ችግሮች መካከል የትምህርት ጥራት ዋነኛ መሆኑን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል። ለትምህርት ጥራት ስኬት ከታች ጀምሮ በትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ተገቢና በቂ ትምህርት እያገኙ እንዲያድጉ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ላይ የሚስተዋለውን የጥራት ችግር ለመፍታት የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ። የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አዲስ ከተመደቡት የከፍተኛ ትምህርት የቦርድ አመራሮች…

በአምባሰል ወረዳ ራስ ጠቆሮ ጥብቅ ደን ላይ የእሳት አደጋ ተከሰተ

በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ በተለምዶ ራስ ጠቆሮ እየተባለ በሚጠራ ጥብቅ ደን ላይ የእሳት አደጋ መከሰቱ ተገለፀ፡፡ የእሳት አደጋው ከሰኔ 6 ቀን 2014ዓ.ም ሌሊት ጀምሮ የተከሰተ መሆኑ እና እስካሁን ድረስ…

“ሰላም እንፈልጋለን ማለታችን የድብቅ ድርድር እናደርጋለን ማለት አይደለም”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሰላም ሂደቱን በተመለከተ የሚያጠና ኮሚቴ መዋቀሩን ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት ሰኔ 07/2014 ዓ. ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከአባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ…

ታጣቂዎች የጋምቤላ ከተማን በከፊል ተቆጣጥረው እንደነበረ ክልሉ ገለጸ

ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ ላይ ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ ላይ ጥቃት ከፍተው የከተማዋን የተወሰነ ክፍል ተቆጣጥረው እንደነበረ የክልሉ መንግሥት ገለጸ። የክልሉ መስተዳደር ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው በጋምቤላ ከተማ “የሸኔ እና የጋምቤላ…

አብን 40 አመራሮቹ እና አባሎቹ እንደታሰሩበት ገለጸ ከ 20 በላይ ጋዜጠኞች መታሰራቸውም ተገልጿል

በ”ሕግ ማስከበር ሽፋን” ሕፃናትን ጨምሮ 35 ዜጎች ያለፍ/ቤት በፀጥታ ሃይሎች መገደላቸውንም ገልጸዋል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ መንግስት ሕግ የማስከበር ስራ ባለው ዘመቻ 40 አባሎቹና አመራሮቹ እንደታሰሩበት አስታወቀ፡፡ የንቅናቄው የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊና…