Archive

Day: January 4, 2021

የሱዳን ጦር ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ጥቃት ፈጸመ በሁለት ግንባር ወደ ኢትዮጵያ ዘልቆ፣ ቤት አቃጠለ፤ ንብረት አወደመ!

በሁለት ግንባር ወደ ኢትዮጵያ ዘልቆ፣ ቤት አቃጠለ፤ ንብረት አወደመ!  ዜና-ሃተታ በሱዳን ወታደራዊ አዛዥ አብድል ፈታህ አልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር፣ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ጥሶ መግባቱን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በዲፕሎማሲ ለመፍታት ቢሞክርም፤…

ቅምሻ ከወዲያ ማዶ፡- የብሪታኒያ ፍርድ-ቤት የዊኪሊክስ መስራች ጁሊያን አሳንጄ ተላልፎ እንዳይሰጥ ወሰነ

የብሪታኒያ ፍርድ ቤት የዊኪሊክስ መስራች ጁሊያን አሳንጄ፣ ለአሜሪካ ተላልፎ እንዳይሰጥ ውሳኔ አሳለፈ። አሳንጄ በስዊድን ወሲባዊ ጥቃት ፈፅመሐል በሚል እንግሊዝ በሚገኘው የኢኳዶር ኤምባሲ በጥገኝነት ቆይቶ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በፊት ለፖሊስ…

67 በመቶ ህዝቧን ለመከተብ ያቀደችው ደቡብ አፍሪቃ ክትባቶቹን በቀጣዩ ወር እንደምታገኝ ተስፋ አድርጋለች

ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የኮሮና ክትባቶችን ልታገኝ እንደምትችል ደቡብ አፍሪቃ አስታወቀች፡፡ ከአጠቃላይ ህዝቧ 67 በመቶ ወይም 40 ሚሊዮን ያህሉን ለመከተብ የወጠነችው ደቡብ አፍሪቃ፣ ወረርሽኙ እስከ ዓመቱ መጨረሻ በራሱ ጊዜ…

ተፈናቃይ ዜጎች ወደ ቀያቸው ለመመለስ መንግሥትን ጠየቁ

መንግስት በመተከል ዞን የተከሰተውን አለመረጋጋት በአስቸኳይ መፍትሄ በመስጠት ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ተፈናቃይ ወገኖች ጠየቁ፡፡ ከነበሩበት ቀየ ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ በመኖራቸው ከፍተኛ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር መዳረጋቸውን በመተከል ዞን በተለያዩ የመጠለያ…

የመገናኛ ብዙኃን ሙስናን በመከላከል እና በሥነ ምግባር ግንባታ ተቀዳሚ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

የመገናኛ ብዙኃን ሙስናን በመከላከል እና በሥነ ምግባር ግንባታ ቀዳሚ ተዋናይ እንዲሆኑ የፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ- ሙስና ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ። ኮሚሽኑ “ሥነ ምግባርን በመገንባት እና ሙስናን በመከላከል ረገድ የሚዲያ ተቋሟት…

ቻዮቴ፣ የጉበት ስብ ማስታገሻ ፍሬ-አትክልት

መግቢያ፡- ቻዮቴ ድንች ለምኔ የሚያሰኝ ምርታማ ተክል ነው፡፡ ፍሬው እንደ ፍራፍሬ ሲሆን፣ ለአመጋገብ ግን እንደ አትክልት ነው፡፡ ስለዚህ፣ ፍሬ-አትክልት ቢባል ጥሩ ነው፡፡  ቻዮቴ በሳይንሳዊ ስሙ Sechium edule  ይባላል፡፡ ቀደምት መገኛው…

ለአሰላ የነፋስ ኃይል ማመንጫ ተርባይን ከሚያቀርበው ሰይሜንስ ጋሜሳ ጋር ስምምነት ተፈረመ

የኢትዮጵያ አሌክትሪክ ኃይል ለአሰላ የነፋስ ኃይል ማመንጫ ተርባይን ከሚያቀርበው ሰይመንስ ጋሜሳ ጋር ስምምነት ተፈራረመ። 100 ሜጋዋት ኃይል ያመነጫል ተብሎ የሚጠበቀው የአሰላ የነፋስ ኃይል ማመንጫ በአዳማ እና አሰላ መካከል የሚገኝ ነው።…

ዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 85 ሚሊየንን ተሻገረ

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቫይረሱ ከጸናባቸው አገራት ተጠቅሳለች! በዓለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ85 ሚሊየን መብለጡ ተገለጸ፡፡ እስካሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 85 ሚሊየን 519 ሺህ…

የፈንድቃ የባህል ማዕከል መስራች መላኩ በላይ የኔዘርላድ ፕሪንስ ክላውስ ሎሬት ተሸላሚ ሆነ

ከጎዳና ሕይወት በመነሳት ከታዳሚዎች በሚያገኛት የሽልማት ገንዘብ ትምህርቱን የተማረው እና ሕይወቱን የቀየረው የባህል ተወዛዋዡ መላኩ በላይ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ የጀመረባትን የፈንድቃ የባህል ምሽት ቤት ከአምስት ዓመታት በፊት ገዝቶ ወደ ባህል…

በሀዋሳ ለጤና ጠንቅ የሆነ እንጀራ ሲያከፋፍሉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

በሀዋሳ ባዕድ ነገር ጨምረው እንጀራ በመጋገር በሕገወጥ መንገድ የሚያከፋፈሉ ተጠርጣሪዎች በሕብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ። ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በታቦር ክፍለ ከተማ…

በአብዬ በሚገኙ ተቀናቃኝ ጎሳዎች መካከል የሠላም ስምምነት ተፈረመ

በአብዬ ግዛት የሚገኙት የሚስሪያ እና ዲንካ ጎሳዎች መካከል የሠላም ስምምነት ተፈረመ፤ በሚስሪያ በኩል ጃዕሚ አልሲድቅ እንዲሁም በዲንካ ጎሳ በኩል ደግሞ ዋር ሀመዲን ስምምነቱን ተፈራርመዋል፡፡ በአብዬ አሚት በምትባል ከተማ በተካሄደው የሁለቱ…

ግብጽ ረቂቅ ሠነዱን አልቀበልም አለች

ኢትዮጵያ እና ሱዳን ተቀበሉ! ታላቁ የሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር የሰየሟቸው ባለሙያዎች ያቀረቡት ረቂቅ ሰነድ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ሲቀበሉት ግብፅ ሳትቀበለው ቀርታለች፡፡ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ የተካሄደውን የሶስትዮሽ ውይይት…

This site is protected by wp-copyrightpro.com