ዜና
Archive

Month: August 2020

ቅምሻ ከእኛ-ለእኛ (ኢትዮጵያዬ) የማህበር ቤቶች የቤት ግንባታ አማራጭ የ2005 ዓ.ም ተመዝጋቢዎችን ቅድሚያ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ተባለ

የማህበር ቤቶች የቤት ግንባታ አማራጭ ፍላጎት ያላቸውን የ2005 ዓ.ም የ20/80 እና 40/60 ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። አስተዳደሩ እንደገለፀው የማህበር ቤቶች የቤት ግንባታ እንደ አማራጭ…

በአዲስ አበባ ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትኃዊ ዕደላ መካሄዱን ኢዜማ በጥናት አጋለጠ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ ከተማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተባባሰ የመጣ የመንግሥታዊ መዋቅሮች ድጋፍ ያለው ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሓዊ ዕደላ እንዳለ…

7 ‹ስናይፐር› ወደ አገር ቤት በሕገ-ወጥ መንገድ ሊገባ ሲል ተያዘ

በቦሌ ኤርፖርት ሰባት ስናይፐር ወደ አገር ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ ሊገባ ሲል መያዙ ተሰማ። ስናይፐሩ የተያዘው በተበታተነ መልኩ በቦርሳዎች ከሌሎች እቃዎች ጋር ተጠቅልለው እንደነበር ተገልጿል። ዛሬ ነሐሴ 25 ቀን 2012…

የአውሮፓ ሕብረት ለኢጋድ አባል አገራት 60 ሚሊዮን ዩሮ የሚያወጡ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ

3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሰርጂካል ማስክ፣ 24 አምቡላንሶች፣ 8 ተንቀሳቃሽ ላብራቶሪዎች እና 70 ሺህ መመርመሪያዎችን አቅርቧል! የአውሮፓ ሕብረት ለምስራቅ አፍርካ አገራት የልማት በየነ መንግስታት (ኢጋድ) አባል ሀገራት 60 ሚሊዮን ዩሮ…

ቅምሻ ከወዲያ ማዶ፡- ከእስራኤል ወደ አረብ ኤምሬትስ የመጀመሪያው የንግድ በረራ ሊደረግ ነው

ከእስራኤል ወደ አረብ ኤምሬትስ ለመጀመሪያ ጊዜ የንግድ በረራ ሊካሄድ ነው። ይህም በሁለቱ መካከል ያለው ግንኙነት ጤናማ እየሆነ ስለመምጣቱ ጠቋሚ ነው ተብሏል። የእስራኤሉ ኤል አል አየር መንገድ የእስራኤል ልዑካንን እንዲሁም የአሜሪካ…

ኢዜማ ሊሰጠው የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ለሁለተኛ ጊዜ ተከለከለ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ በአዲስ አበባ እየተደረገ ነው ያለውን የመሬት ወረራና ህገ-ወጥ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላ በተመለከተ ሊሰጠው የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ለሁለተኛ ጊዜ ተከለከለ፡፡ ጋዜጣዊ መግለጫው የተከለከለው መግለጫ…

ፍርድ ቤት የአቶ ልደቱን ክስ ቢዘጋም አሁንም እስር ላይ ናቸው

ሁከት በማስተባበርና በመደገፍ በፖሊስ ተይዘው የቆዩትን የአቶ ልደቱ አያሌውን ጉዳይ ሲመለከት የነበረው ፍርድ ቤት የቀረበባቸው ጉዳይ የማያስከስሳቸው መሆኑን በመግለጽ መዝገቡን መዝጋቱን ቢገልጽም፤ እስር ላይ መሆናቸውን የኢዴፓ ፕሬዝዳንት አቶ አዳነ ታደሰ…

ቅምሻ ከወዲያ ማዶ፡- ኳታር የሰራተኞችን ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን የሚደነግግ አዋጅ አጸደቀች

የኳታር አሚር ሼክ ተሚም ቢን ሃማድ አልታኒ የሰራተኞችን ዝቅተኛ የደመወዝ መጠንን የሚደነግግ አዋጅ አጸደቁ። በዚህም መሠረት የሰራተኞች ዝቅተኛው ወርሃዊ የደመወዝ መነሻ 1,000 የኳታር ሪያል ይሆናል። መጠለያ እና ምግብ የማይቀርብ ከሆነ…

ቅምሻ ከእኛ- ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) የብልጽግና ፓርቲ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች ሥልጠና በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

– የአማራ ብልፅግና ፓርቲ 1ኛ ዙር የአመራር ስልጠና በባህር ዳር ተጀምሯል! በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ በጀመረው የብልጽግና ፓርቲ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች ሥልጠና ላይ በፌዴራል መንግስት መዋቅር ውስጥ ከሚኒስትር እስከ ምክትል…

ቅምሻ ከእኛ-ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) የፌዴራል መንግስት የመሬት ይዞታ አያያዝን ለማዘመን የሚያስችል ስራ እየተሰራ ነው

የኢትዮጵያ የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የፌዴራል መንግስት የመሬት ይዞታን የሚያዘምን ስራ በማከናወን ላይ መሆኑ ተገልጿል። ለ311 ተቋማት መረጃ ተደራጅቶ ካርታ መዘጋጀቱም ተጠቁሟል። ሦስት የስትራተጂ…

ቅምሻ ከእኛ- ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) በአዲሱ ስርዓተ-ትምህርት ተማሪዎች 12ኛ ክፍልን ሲጨርሱ የሙያ ባለቤት ይሆናሉ

ትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ የትምህርት ዘርፉ የ10 አመት እቅድ ውይይት እያካሄደ ነው። በውይይቱ ላይ አጠቃላይ ትምህርት አንዱ የሙያ መማሪያ ዘርፍ እንዲሆን ትምህርት ሚኒስቴር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተነግሯል። የትምህርት ሚንስትር ጌታሁን…

ቅምሻ ከእኛ- ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) በህዳሴው ግድብ ድርድር ላይ ወጤት እየታየ መሆኑ ተገለጸ

በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል ባለፉት ሁለት ሳምንታት ሲካሄድ በነበረው ድርድር ላይ የተወሰነ ውጤት መታየቱን የኢትዮጵያ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ገለጹ። ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በትዊተር ገጻቸው…

ቅምሻ ከእኛ-ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) የጣና ሐይቅ ይዞታ ትላንትና ዛሬ

የጣና ሐይቅና ሌሎች ውሃ አካላት ልማትና ጥበቃ ኤጀንሲ እንደሚገልፀው ከሆነ በአሁኑ ወቅት በጣና ሐይቅ ላይ ያለው የእምቦጭ አረም መጠን 900 ሄክታር አካባቢን የሸፈነ ነው። ይህንን መጤ አረም ለማስወገድ ከፌደራል መንግሥት…

ቅምሻ ከእኛ-ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) በሶማሌ ክልል የኮሮና ስርጭትን ለመከላከል ከ1 ሺህ በላይ የሕግ ታራሚዎች ተለቀቁ

የሶማሌ ክልል የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሲል 1 ሺህ 200 ታራሚዎች መልቀቁን አስታወቀ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላት በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ እንዲሁም በኢትዮ-ሶማሌና በኢትዮ-ሶማሌ ላንድ ድንበር ኮሮና…

ቅምሻ ከወዲያ ማዶ፡- የብላክ ፓንተር ፊልም እውቅ ተዋናይ በካንሰር ሕይወቱ አለፈ

በብላክ ፓንተር ፊልም ትልቅ ተቀባይንት ያገኘው ቻድዊክ ቦስማን በአንጀት ካንሰር ህመም ከዚህ አለም ማለፉ ተሰምቷል፡፡ የ43 አመቱ ተዋናይ ከ4 ዓመታት በላይ በህመሙ ሲሰቃይ የቆየ ሲሆን፣ ከቤተሰቦቹ ጋር በቤት ውስጥ በነበረበት…

በአዲስ አበባ በመንግሥት አካላት የተፈጸመውን ኢ-ፍትሓዊ ድርጊት የሚያጋልጠው ሠነድ ለሕዝብ ይፋ እንዳይሆን ታገደ

የአዲስ አበባ ፖሊስ የኢዜማ ፓርቲን መግለጫ አገደ! ኢዜማ ሠነዱን ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ አማራጭ እየፈለገ ነው!  የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ፓርቲ፣ ዛሬ ነሐሴ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት…

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በሚሰጧቸው የዳኝነት አገልግሎቶች መሻሻሎች እየታየ መሆኑ ተገለጸ

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በሚሰጧቸው የዳኝነት አገልግሎቶች መሻሻሎች እየታየ መሆኑን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ገለጹ፡፡ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በ2012 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም የጋራ ውይይት አካሂደዋል። በ2012 ዓ.ም…

‹‹ብርቱ ወጣቶች የኢትዮጵያ የመጭ ዘመኗ መሀንዲሶች ናቸው›› ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ገለጹ

እንቅፋትና ጋሬጣውን አልፈው፣ መውደቅና መነሳቱን ተቋቁመው ድል የሚያስመዝግቡ ብርቱ ወጣቶች የኢትዮጵያ የመጭ ዘመኗ መሀንዲሶች መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የብልጽግና ጉዟችን ለሀገራችን ትርጉም ያለው ለውጥ ከማሳካት በዘለለ…

በአዲስ አበባ ለመጪው የትምህርት ዘመን ለተማሪዎች ምገባ 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ተባለ

በአዲስ አበባ ለ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምገባ 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ የከተማ አስተዳደሩ ገለጸ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከከተማዋ የግሉ ዘርፍ ተዋንያን ጋር…

አደይ አበባ- ለውበት እና ለጤና

አደይ አበባ (Bidens borianiana) አደይ አበባ፡- ለውበት እና ለጤና የመስቀል ወፍ እና- የአደይ አበባ፤ ቀጠሮ እንዳላቸው- መስከረም ሲጠባ፤ ማን ያውቃል!? … ሲሉ ባለቅኔውን አብዬ መንግስቱ የተቀኙት ያለ-ነገር አይመስለኝም፡፡ የሁለቱ ዓመታዊ…

የዓባይ የውኃ ከፍታ መጨመሩን ሱዳን አስታወቀች

የናይል ውኃ ከ100 ዓመታት ወዲህ ታይቶ በማያወቅ ከፍተኛ መጠን ላይ መድረሱን የሱዳን መስኖና ዉኃ ሀብት ሚኒስትር ትናንት አስታወቁ፡፡ የናይል ዉኃ እ.ኤ.አ. በ2019 ከነበረው የ 17.26 ከፍታ ጋር ሲነጻጸር የ 17.43…

ቅምሻ – ከእኛ ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) # አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አቋረጠች

ከህዳሴ ግድቡ ጋር የተፈጠሩ ልዩነቶችን መሰረት በማድረግ፣ አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አቋረጠች፡፡ አንዳንድ የአሜሪካ ባለሥልጣናት፣ ይህ እርምጃ በአሜሪካና በኢትዮጵያ መሀል የነበረውን ግንኙነት ያሻክራል ብለው ይገምታሉ፡፡ የህዳሴ ግድቡን አስመልክቶ በኢትዮጵያ ግብጽና…

በትግራይ ሊካሄድ የታሰበውን የህወሓት ምርጫ የሚቃወሙ ዜጎች ለሞት እየተዳረጉ ነው ሲል ትዴፓ ገለጸ

ህወሓት በትግራይ ክልል አካሂደዋለሁ የሚለውን ምርጫ የሚቃወሙ ዜጎች ለሞትና ስቃይ እየተዳረጉ መሆኑን የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ ገለጹ። የትዴፓ ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቃለ…

ቅምሻ – ከእኛ ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) # ሞባይል፡ ‘የኮምፒውተር ተህዋስ’ የተገጠመላቸው የቻይና ሥልኮች ኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪካ አገራት ውስጥ ተሽጠዋል

የኮምፒውተር ተህዋስ [ማልዌር] የተገጠመላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የቻይና ስሪት የሆኑ ስልኮች አፍሪካ ውስጥ መቸብቸባቸው ተሰምቷል። አፕስትሪም የተሰኘ አንድ ተቋም ነው ይህን ይፋ ያደረገው። ቢያንስ 53 ሺህ ይህ ተህዋስ የተገጠመላቸው የቴክኖ ስልኮች…

ቅምሻ – ከእኛ ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) # የመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ ፖሊሲ ፀደቀ

የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ሕግ እንዲወጣም ፖሊሲው ወስኗል ለመገናኛ ብዙኃን የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ለመስጠት ተደራሽነትና ይዘታቸውን ለማስፋት እንዲሁም በዘርፉ ፍትሐዊ የባለቤትነት ስብጥርን ለማረጋገጥ የተለመ ፖሊሲ ፀደቀ። ፖሊሲው ባለፈው ቅዳሜ ነሐሴ 16 ቀን 2012 ዓ.ም. በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ ታሪክ ውስጥ መንግሥት ያወጣው የመጀመርያው የፖሊሲ ማዕቀፍ ነው። በሰነዱ ከተካተቱት አንኳር ነጥቦች መንግሥት የመናገኛ ብዙኃንን ለማጎልበት የኢንቨስትመንትማበረታቻ ለመስጠት በግልጽና በዝርዝር የወሰነበት የመጀመርያው የፖሊሲ ማዕቀፍ እንደሆነ መረዳት ይቻላል። ‹‹በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ የሚመራበት ራሱን የቻለ የመገናኛ ብዙኃን ፖሊሲ ባለመኖሩ፣ ዘርፉን በብቃትና በጥራት በማስፋፋት ሁሉንም የኢትዮጵያ ዜጎች የመረጃ ተደራሽ ለማድረግ አልተቻለም›› የሚለው የፖሊሲ ሰነዱን አስፈላጊነት የሚገልጸው የመግቢያ ሀተታ፣ የአገራችን መገናኛ ብዙኃን የሚመሩበትና የሚደገፉበት የመገናኛ ብዙኃን ፖሊሲ ማዘጋጀት ወቅታዊና አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ፖሊሲ መቀረፁን ያስረዳል። ለሕዝብ (ለመንግሥት) መገናኛ ብዙኃን ከሚደረገው ድጋፍ ባሻገር ለንግድና ለማኅበረሰብ መገናኛ ብዙኃን የሚደረግ ቀጥተኛ የሆነ የመንግሥት ድጋፍ እስከዛሬ አለመኖሩን የፖሊሲ ሰነዱ በግልጽ አስቀምጧል። መገናኛ ብዙኃን የዜጎችን አስተሳሰብ በማነጽ ዜጎች በአገር ግንባታ እንዲሳተፉ የሚያደርጉ በመሆናቸው፣ ከማንኛውም የኢኮኖሚ ዘርፍ በተሻለ ድጋፍና ማበረታቻ እንደሚያስፈልጋቸው በመንግሥት መታመኑን በመግለጽ ታሳቢ የተደረጉትን ድጋፍና ማበረታቻዎች ይዘረዝራል። የመገናኛ ብዙኃኑን ለመደገፍ ሊወሰዱ ይገባል ተብለው ከተቀመጡት ማበረታቻ ድጋፎች መካከልም  በመገናኛ ብዙኃን መሣሪያዎች ላይ የተጣለውን ከፍተኛ የገቢ ቀረጥ መቀነስ፣ በአገር ውስጥ የሚመረቱበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ፣ መሥሪያ ቦታ፣ ብድርና የውጭ ምንዛሪ ቅድሚያ ዕድል ማመቻቸት ይገኙበታል። የመንግሥት ተቋማት ማስታወቂያና ስፖንሰርሽፕ ገቢ በውድድር እንዲከፋፈል ማድረግ ከኢንተርኔት ጋር የተሳሰረ ያልተማከለ ለሁሉም የመገናኛ ብዙኃን ውጤቶች በሁሉም ቦታ ተደራሽ የሆነ ብሔራዊ የማተሚያ ቤት ማደራጀት፣ የማተሚያ ቤት ወጪንና የመሸጫ ዋጋን መደጎም፣ የኅትመት ግብዓት ወረቀት፣ መሣሪያዎች በአገር ውስጥ እንዲመረቱ ማድረግ ሌሎቹ ማበረታቻዎች ናቸው። በቂ ማተሚያ ቤት መቋቋሙንና የግሉ ዘርፍ መሳተፉን ማረጋገጥ፣ አሳታሚዎችም በግልም ይሁን በጋራ የራሳቸው የማተሚያና የማሠራጫ አውታር እንዲኖራቸው መደገፍ፣ ጋዜጣ መጽሔት በፖስታ ቤትና በመሰል ቴክኖሎጂ ታግዞ ማሠራጨት እንዲችሉ መደገፍ እንደሚገባበፖሊሲ ሰነዱ ተዘርዝሯል። በተጨማሪም መገናኛ ብዙኃንን ለማስፋፋት፣ ለመደገፍና ቀጣይነታቸውን ለማረጋገጥ በፋይናንስና በቴክኒክ የሚደገፉበት አሠራር መዘርጋት፣ ለዚህም የድጋፍ ፈንድ በማቋቋም ወይም በሬጉላቶሪ አካሉ በኩል የድጋፍ ሥራ ማከናወን እንደሚገባ ወስኗል። አሁን ያለው የንግድ መገናኛ ብዙኃን ባለቤትነትና ስብጥር ፍትሐዊ አለመሆኑን የሚገልጸው የፖሊሲ ሰነዱ፣ ይህንን ጉድለት ለመቅረፍም የንግድ መገናኛ ብዙኃን የባለቤትነት ስብጥር ፍትሐዊና ብዝኃነትን የተላበሰ ማድረግ ይገባል ሲል ወስኗል። ብዝኃነትን የተላበሰ ፍትሐዊ የባለቤትነት ስብጥር ያለው የሚዲያ ምኅዳር እንዲፈጠርም ግለሰብን ጨምሮ የንግድ ተቋማት የንግድ የኅትመት መገናኛ ብዙኃን ባለቤት እንዲሆኑ መፍቀድ እንዳለበት ይገልጻል። ወደዚህ ለመምጣትም ግልጽ የሆነ ዝርዝር ሕግ በማውጣት የመገናኛ ብዙኃን ባለቤትነት ስብጥርን ማስፋት አስፈላጊ መሆኑን፣ የመገናኛ ብዙኃን የንብረት ቁጥጥር ሕግ አገራዊ ጥቅምን ግንዛቤ ውስጥ ማስገባቱን፣ መገናኛ ብዙኃን በተለያዩ ሰዎች መያዝን የሚያበረታታ መሆኑን፣ መገናኛ ብዙኃንን የመረጃና የሐሳብ ስብጥርንና ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትን በማበረታታት በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሒደት ተገቢውን ሚና እንዲጫወቱ ማስቻልና ማረጋገጥ እንደሚገባም በፖሊሲ ሰነዱ ወስኗል። ከዚህ በተጨማሪም ትውልደ ኢትዮጵያውያን በመገናኛ ብዙኃን እንዲሰማሩ እንዲደረግ የወሰነ ቢሆንም፣ ከፍተኛው የባለቤትነት የአክሲዮን ድርሻ ግን በኢትዮጵያውያን ይዞታና ቁጥጥር ሥር እንዲውል አቅጣጫ አስቀምጧል። ይሁን እንጂ መጠኑ በፖሊሲ ሰነዱ ላይ አልተቀመጠም።  በማኅበራዊ ሚዲያ የሚታየውን የተዛባ የመረጃ ሥርጭት ለመከላከል መንግሥት ከሌሎች ዴሞክራሲያዊ አገሮች ተሞክሮ በመውሰድና ከኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር በማጣጣም አስቻይ የሆነ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ሕግ ማውጣት እንደሚገባ አስቀምጧል። ይህንንም መሠረት በማድረግ በመደበኛው መገናኛ ብዙኃን ላይ እንደሚደረገው ቁጥጥር ሁሉ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ ባለቤቶች ወይም የሚዲያ ይዘት አሠራጮች ማንነታቸውን በይፋ እንዲገልጹ በሕግ በማስገደድ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባ በፖሊሲው ተወስኗል። ሪፖርተር ነሐሴ 16

ቅምሻ ከእኛ- ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከ20 በላይ ተለማማጅ ሐኪሞች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል እና የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሁለት ሐኪሞችና 20 ተለማማጅ ሐኪሞች [ኢንተርኖች] በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተገለፀ። ቢቢሲ ከዩኒቨርስቲው ምንጮች ባገኘው መረጃ መሰረት እስከ ማክሰኞ 17፣ ረቡዕ አራት…

ቅምሻ ከእኛ- ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) እግር የሚተካው ሰብዓዊ-ሰው

በህወሓት/ኢሕአዴግ በተፈጸመበት የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ሁለት እግሮቹን ያጣው ከፍያለው ተፈራ “መጀመሪያ ተኩስ ሲከፍቱብን 3 ልጆች ወዲያው ሞቱ። እኔ አንድ እግሬ ወዲያው ተቆረጠ፤ ቀኝ እግሬን ደግሞ ያለፈቃዴ ከቁርጭምጭሚቴ ከፍ ብለው ቆረጡት…

ቅምሻ ከወዲያ ማዶ፡- ቭላድሚር ፑቲን፡ “አስፈላጊ ከሆነ ወደ ቤላሩስ ፖሊስ እልካለሁ” አሉ

የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን አስፈላጊ ከሆነ ወደ ቤላሩስ ለመላክ ተጠባባቂ የፖሊስ ኃይል ማዘጋጀታቸውን አስታወቁ። ፑቲን “የቤላሩስ ፕሬዚደንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ የተወሰነ ተጠባባቂ የፖሊስ ኃይል እንዳዘጋጅላቸው ጠይቀውኛል። እኔም ባሉኝ መሰረት አድርጌያለሁ” ሲሉ…

ቅምሻ ከእኛ- ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) በሳዑዲ እና በኤምሬትስ በችግር ላይ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር ቤት ሊመለሱ ነው

በሳዑዲና በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሚገኙ ከ25 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው ይመለሳሉ ተባለ፡፡ በሳዑዲ ዐረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አብዱልአዚዝ አህመድ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው በርካታ ኢትዮጵያዊያን በሀገሪቱ እንደሚገኙ ለኢዜአ ገልጸዋል። በመሆኑም…

ቅምሻ ከእኛ- ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) በጉደር ከተማ በሕገወጥ መንገድ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ሲራገፍ የነበረ ስኳርና ዘይት ተያዘ

በምዕራብ ሸዋ ዞን ጉደር ከተማ በሕገ-ወጥ መንገድ በግለሰብ መኖሪያ ቤት በመራገፍ ላይ የነበረ የምግብ ዘይትና ስኳር መያዙን ፖሊስ አስታወቀ። የቶኬ ኩታዬ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ይገዙ ገብረሚካኤል ለኢዜአ እንደገለጹት ስኳርና…

በአዲስ አበባ የ2013 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ነገ ይጀመራል

በአዲስ አበባ የ2013 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ነገ እንደሚጀመር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ ምዝገባው በሁሉም ትምህርት ቤቶች ከነገ ነሐሴ 19 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ…

ቅምሻ ከእኛ- ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) ቻይና ለ3ኛ ዙር የኮሮና መከላከያ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች

የቻይና መንግሥት ለ3ኛ ዙር የኮሮና መከላከያ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ለግሷል። በዚኛው ዙር ድጋፍ 500 ሺህ ሰርጂካል የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል፣ 65 ሺህ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል፣ 10…

ቅምሻ ከእኛ- ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) የሕግ ታራሚዎች ‘ቢለቀቁ’ የሚል ምክረ ሀሳብ ቀረበ

የይቅርታና የአመክሮ መስፈርት የሚያሟሉ የሕግ ታራሚዎች ቢለቀቁ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ እንደሚረዳ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻፀም መርማሪ ቦርድ አስታወቀ። መርማሪ ቦርዱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቀነ-ገደብ ሲጠናቀቅ ሊከሰቱ እንደሚችሉ ያሰጉትንና ትኩረት…

ቅምሻ ከእኛ- ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) ‹‹የአባይን ግድብ የሚያጠቃ ካለ አብረን በጋራ እንመክተዋለን››

“የአባይን ግድብ ለማጥቃት የሚነሳ ማንኛውም ኃይል ካለ ለመመከት አብረን እንቆማለን” ሲሉ በሱዳን የ4ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ሁስማን ጁማ ተናገሩ፡፡ በሱዳን የ4ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል…

ቅምሻ ከእኛ- ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) ቤተክርስቲያን፡ “የመንግሥት ባለሥልጣናት ኃላፊነታቸውን አልተወጡም” አለች

ከ67 በላይ ምእመናን ተገለዋል፤ 38 ምእመናን ከባድ፣ 29 ምእመናን ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመንግሥት ባለሥልጣናት ኃላፊነታቸውን በወቅቱ እና በብቃት አልተወጡም ስትል አስታወቀች፡፡ ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ፤…

This site is protected by wp-copyrightpro.com