Archive

Day: February 19, 2020

‹‹አንድነትና ሰላምን ለማረጋገጥ ክላሽና ታንክ ሳይሆን የሚያስፈልገው ልማትን ማረጋገጥ ነው›› ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ የካቲት 11 ቀን 2012 ዓ.ም በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ለነዋሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት ፤  ‹‹ካለንበት ድህነት ለመውጣት የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይሆን ልማትን ማረጋገጥ ይገባል›› ብለዋል።…

ኢዜማ ከጀርመኖች ጋር ስለ ማህበራዊ ፍትሕ ሊያወያይ ነው

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ፓርቲ፣ ፌሬድሪክ ኤበርት ስቲፍታንግ ከሚባል የጀርመን አገር የማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ በኢትዮጵያ ካቋቋመው ፋውንዴሽን ጋር በመሆን የፓናል ውይይት ሊያደርግ ነው፡፡ ውይይቱ የሚካሄደው ነገ የካቲት 12 ቀን…

“አማራ የትም ይወለድ የት አማራ ነው” የአማራ ወጣቶች ማኅበር

አማራነት እና ኢትዮጵያዊነት አይጣሉም፤ አማራ በክልል የሚወሰን ማሕበረሰብ አይደለም፤ አማራነት በደም የሚለካ ሳይሆን፣ የሥነ-ልቦና አንድነት ነው፤   የአማራ ወጣቶች ማኅበር፣ በሲቭል ማኅበርነት ተዋቅሮ በአገር-አቀፍ ደረጃ መመሥረቱን አስታወቀ፤ ዛሬ ረቡዕ የካቲት…

ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ለሙያ አጋሮቹ ግብዣ ሊያደርግ ነው

ተወዳጁ ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ‹‹በሲያምሽ ያመኛል›› አልበም እና ‹‹ሰርክ አዲስ›› በተሰኘው አዲሱ የሙዚቃ ቪዲዮ ላይ ለተሳተፉ ባለሙያዎች ግብዣ ሊያደርግ ነው፡፡ ድምጻዊው በቅርቡ ለተመልካች ያበቃውን ‹‹ሰርክ አዲስ›› የተሰኝውን ሙዚቃ ቪዲዮ ምክንያት…

የጅጅጋ ኤክስፖርት ቄራ ድርጅት ወደ ስራ ሊመለስ ነው

በሶማሌ ክልል ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት እና በእንሰሳት አቅርቦት እጥረት ለሁለት አመታት ስራውን አቁሞ የነበረው የጅጅጋ ኤክስፖርት ቄራ ድርጅት ወደ ስራ ሊመለስ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ድርጅቱን ወደ ስራ ለመመለስ የሚደረገውን…

መንግስት በሽፍቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ገለጸ

እራሳቸውን ነጻ አውጪ ነን ብለው የሰየሙ ሽፍቶች በህብረተሰቡ እና በመንግስት መዋቅር ላይ ጉዳት እያደረሱ ስለሆነ መንግስት እርምጃ ለመውሰድ መገደዱን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዴሳ ገለጹ፡፡…

ኢትዮ ቴሌኮም ይቅርታ ጠየቀ

በትላንትናው ዕለት የተፈጠረው የሞባይል ድምፅ እና የኢንተርኔት ኔትወርክ መቆራረጥ የቴክኒክ ችግር መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ፡፡   ኢትዮ ቴሌኮም ትላንት የካቲት 10 ቀን 2012 ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት የሞባይል ድምጽና የኢንተርኔት አገልግሎት …

‹‹ትግራይ ራስዋን የቻለች አገር ናት ብላችሁ አውጁ›› ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል

የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ደብረጽን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህውሓት የተመሰረተበትን 45ኛውን ዓመት አስመልክቶ በዛሬው ዕለት በመቀሌ ስታዲየም ለታደሙ ሰዎች ባደረጉት ንግግር ትግራይ ራስዋን የቻለች አገር ናት ብላችሁ አውጁ አሉ። ”በኢትዮጵያ እየተከሰተ…

ሁሉንም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መቆጣጠር እንደማይችል ኤጀንሲው አስታወቀ

የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ካላቸው ብዛት አንጻር ሁሉንም ለመቆጣጠርና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የአቅም ውስንነት እንዳለበት የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ገለፀ። በሀገሪቱ አሁን ላይ ባለው ወቅታዊ መረጃ መሰረት…

This site is protected by wp-copyrightpro.com