ዜና
Archive

Month: October 2019

በአምቦ ወጣቶች “ዳውን ዳውን” ማለት ጀመሩ

በኦሮሚያ ክልል እና አጎራባች አካባቢዎች የተፈጠረውን ኹከት፣ ግጭት እና ሕገ-ወጥነት ለመከላከልና ችግሩ ዳግም እንዳይከሰት በዘላቂነት ለመፍታት፣ ነዋሪዎችን ለማነጋገር ወደ አምቦ ከተማ ያመሩት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ተቃውሞ ሊያጋጥማቸው ችሏል፡፡…

አትሌት ኃይሌ ገ/ሰላሴ ፌስቡክን ለመክሰስ እያሰብኩ ነው አለ

ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮች የከፋ ጉዳት እንዲያደርሱ የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾች፣ በተለይም ፌስቡክ ትልቅ ድርሻ እንደነበረው ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ተናገረ፡፡ አትሌት ኃይሌ ሲናገርም፣  ሀገር እየተጎዳ ነው፣…

ኢትዮጵያና ግብፅ በአሜሪካ የሚገናኙት ለውይይት እንጂ ለድርድር አይደለም ተባለ

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን በሚመለከት፣ ግብፅ አሜሪካ ታደራድረን በሚል ያቀረበችውን ሃሳብ ኢትዮጵያ አልቀበልም ማለቷ የሚታወስ ነው። ከቀናት በፊት በሩሲያ ሶቺ ከተማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድና የግብፁ ፕሬዘዳንት አብዱል ፈታህ…

ቦይንግ ኩባንያ ጥፋቱን በይፋ አመነ

“እኔም ልቤ ተሰብሯል፤ በጥልቅ አዝናለሁ!” የቦይንግ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ግዙፉ አውሮፕላን አምራች ድርጅት ‹‹ቦይንግ ኩባንያ›› 737 ማክስ ጀቶቹ ላይ የቴክኒክና የንድፍ ችግር እንደነበረባቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ በይፋ አመነ፡፡ ትላንት በዩናይትድ…

“ቀይ መስመር ተጥሷል!” ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

“ለሀገርና ለህዝብ ጥቅም ሲባል፣ ልናሰምረው እና ልናከብረው የሚገባን ቀይ መስመር አለ፤ እርሱም ተጥሷል” ሲሉ የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አስተያየታቸውን ሰጡ፡፡ የሀገሪቱ ርዕሰ-ብሔር የሆኑት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በትዊተር ገፃቸው ነው ይህን…

በጎንደር እና ባሕር ዳር ለሚገነቡ አዳሪ ትምህር ቤቶች የገቢ ማስገኛ የጎዳና ላይ ሩጫ ይካሄዳል ተባለ

በጎንደር እና ባሕር ዳር ከተማ ለሚገነቡ ሁለት አዳሪ ትምህር ቤቶች፣ የገቢ ማስገኛ የጎዳና ላይ ሩጫ፣ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች ይካሄዳሉ ተባለ፡፡ “ወንፈል” የተሰኘ የተራድኦ ድርጅት ቅዳሜ ጥቅምት 22 ቀን 2012 ዓ.ም…

ይድረስ ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

(ግልፅ ደብዳቤ)  ጥቅምት ፲፭ ቀን ፪፻፲፪ ዓ.ም ይድረስ ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አዲስአበባ ኢትዮጵያ   በቅርቡ በሀገራችን የተከሰተው ኹከትና ግጭት፣ የሰዎችን ሕይወት አጥፍቷል፤ የንፁሐንን ደም አፍስሷል፡፡ ይህ ለእኔ…

“በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች አልተከበሩም” ኢ.ሰ.መ.ጉ

በኢትዮጵያ ሀገራዊ፣ አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎች ባለመከበራቸውና መንግሥት የማስከበር ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ፣ የተለያዩ የመብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ወቅታዊ ኹኔታ አስመልክቶ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ)…

መንግሥት የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብር የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጠየቀ

ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልልና በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ በተከሰተ ኹከትና ግርግር በደቦ የተፈፀሙ የዜጎች ግድያዎች፣ መፈናቀሎች እና የንብረት ውድመቶችን አስመልክቶ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡፡ ዜጎች የአካል እና የሥነ…

በቂሊንጦ ቃጠሎ ምክንያት ክስ የተመሠረተባቸው ተከሳሾች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተሰጠ

ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቂሊንጦ እስረኛ ማቆያን በማቃጠል ወንጀል ክስ ከተመሠረተባቸው በርካታ ተከሳሾች መካከል፣ በአራቱ ላይ የፅኑ እስራት ውሳኔ ተሰጠ፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ…

“የጋራ ታሪክ የለንም የምትሉ የኦሮሞ ፖለቲከኞች፣ አዎን! እኛ ኢትዮጵያውያን ወንድሙን ከሚያርድ ሰው ጋር የጋራ ታሪክ የለንም!”

 ክቡር ጠ/ሚ፣ ዝቅ ብዬ አክብሬዎታለሁ፤ መፍትሔ የማይሰጡ ከሆነ ግን፣ ቀጥ ብዬ ቆሜ እታገልዎታለሁ!” ታማኝ በየነ (የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና አክቲቪስት) “‹ከኢትዮጵያውያን ጋር የጋራ ታሪክ የለምን› ለምትሉ ጽንፍ ረጋጭ የኦሮሞ ፖለቲከኞች፤ አዎ!…

ከአንድነት ፓርክ ጉብኝት ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ

በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ግቢ ውስጥ እየተገነቡ ካሉ ፓርኮች፣ ሙዚየሞች፣ የእንስሳት መኖሪያ ሥፍራ እና የጎብኚን አትኩሮት የሚስቡ ልዩ-ልዩ ማዕከላት ውስጥ፣ በቅርቡ ተጠናቅቆ ለጉብኝት የተከፈተው አንድነት ፓርክ፣ ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማስገባቱን…

የግዮን መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ፍቃዱ ማኅተመወርቅ የ7 ዓመት ፍርድ ተላለፈበት

የግዮን መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ፣ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዐቃቤ-ሕግ ያደረ ክስ፣ የሰባት ዓመት እሥርና የሰባት ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተፈረደበት:: በሌላ በኩል፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩን ጨምሮ 22…

ዜጎች ላይ ጥቃት የፈጸሙ ግለሰቦችና አካላትን በዓለማቀፍ ፍርድ ቤት እከስሳለሁ ሲል ግሎባል አሊያንስ ገለጸ

ከሰሞኑ በተከሰተ ኹከትና ግርግር ዜጎች ላይ ጥቃት የፈፀሙ ግለሰቦችንና አካላትን በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ጭምር ለመክሰስ እየሰራሁ ነው ሲል በአርቲስት ታማኝ በየነ የሚመራው ግሎባል አሊያንስ አስታወቀ፡፡ የጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)…

በኦሮሚያ ክልል ተፈጥሮ በነበረው ኹከት ከ359 ሰዎች በላይ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ

ሠሞኑን በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው ኹከትና ግርግር ተሳትፈው በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል በሚል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተነገረ፡፡ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ…

ሰሞኑን ለተከሰተው ኹከትና ግድያ ምክንያት የሆኑ ሁሉ በሕግ እንዲጠየቁ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለተከሰተው ኹከትና ግርግር፣ ግድያና ንብረት ማውደም ምክንያት የሆኑ ሁሉ፣ በሕግ ቁጥጥር ሥር ውለው እንዲጠየቁ ኢዜማ ጠየቀ፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን ትኩረት አድርጎ ዛሬ ረፋድ አዲስ…

አዲሱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ረቂቅ ዝግጅት ተጠናቀቀ

ለ18 ዓመታት በሥራ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የሚተካው አዲሱ የፖሊሲ ረቂቅ ዝግጅት መጠናቀቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡ በሀገሪቱ እየተከናወኑ ካሉ የማሻሻያ /reform/ ሥራዎች መካከል አንዱ የውጭ ጉዳይ ፖሊስ…

መንግሥት ችግሮችን የሚያባብስ እንጂ የሚቀርፍ እርምጃ እንዳልወሰደ መኢአድ ገለጸ

የጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት፣ ችግሮችን የሚያባብስ እንጂ የሚቀርፍ እርምጃ አልወሰደም ሲል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፓርቲ አስታወቀ፡፡ መኢአድ፣ በኦሮሚያ ክልል ከሰሞኑ የተከሰተውን ኹከትና ግጭት ያስከተለውን ሞትና የንብረት ውድመት…

የአንበጣ መንጋው እስካሁን በሰብል ላይ ጉዳት እንዳለደረሰ ተገለፀ

በአማራ ክልል የተወሰኑ ወረዳዎች ሰሞኑን የተከሰተው የአንበጣ መንጋ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት አላደረሰም ሲል የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሰለሞን አሰፋ (ዶ/ር) መንጋው የተከሰተው ክልሉን ከአፋር ጋር በሚያዋስኑ ወረዳዎች…

“በዚህ ዓለም ላይ እነርሱ ካደረሱብን ጉድ በላይ የሚጠብቀን ጉድ ሊኖር አይችልም”

የሶማሌ ክልል ም/ል ፕሬዝዳንት ህወሓት በቅርቡ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ‹‹ፌዴራሊዝሙ ሊፈርስ ነው፣ ሕገ-መንግሥቱ አልተከበረም፣ አጋር ፓርቲዎች በአዲሱ የኢሕአዴግ ግንባር ፓርቲዎች ውህደት ተጎጂ ትሆናላችሁ›› ስለማለቱ የተጠየቁት የሶማሌ ክልል ም/ል ርዕሰ…

መንግስትን እናፈርሳለን የሚሉ አካላት ባለፉት ዓመታት ሀገር ጥለው የሸሹ ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚንሥትሩ ተናገሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

“መንግሥትን በሁለት ቀን እንበትናለን የሚሉ አካላት፣ እንደዚህ ዓይነት አቅም ካላቸው፤ ባለፉት ዓመታት ሕዝብ ሲሰቃይ ለምን ሀገር ጥለው ሸሹ” ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ…

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሁለት ቀናት በነበረው ኹከት የ67 ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል ተባለ

በኦሮሚያ ክልል ባሉ ከተሞች፣ ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ በነበረው የወጣቶች ኹከት፣ መንገድ የመዝጋትና ንብረት የማውደም ብጥብጥ፣ የ67 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡ ከሟቾቹ ውስጥ አምስቱ የፖሊስ አባላት እንደሆኑ የተነገረ ሲሆን፣ 13ቱ…

በኦሮሚያ ክልል የወጣቶች እንቅስቃሴ በማኅበረሰቡ መካከል መቃቃርን እየፈጠረ ነው ሲሉ ዜጎች አስታወቁ

አክቲቪስት ጃዋር፣ በማኅበራዊ ገጹ ‹‹ፖሊስ በለሊት ጥበቆቼን ሊያነሳብኝ ነው›› ሲል ላቀረበው ህዝባዊ ጥያቄ፣ ውግንና ለማሳየት፣ በኦሮሚያ ክልል ወጣቶች በፈጠሩት ኹከቶችና ግጭቶች ‹‹የማኅበረሰቦች መቃቃር እየተፈጠረ ነው›› ሲሉ፣ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ ሆኖም፣ በአሁኑ…

ኢትዮጵያ በሩሲያ- የአፍሪካ ትብብር መድረክ ብሄራዊ ጥቅሟን ያስጠበቁ ስኬታማ ተግባራት ማከናወኗ ተገለፀ

  ጠቅላይ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይልን ለሰላማዊ ጥቅም ለማዋል ለምታደርገው ጥረት ከሩሲያ ድጋፍ የምታገኝበትን ስምምነት መፈራረሟን አንስተዋል። ኢትዮጵያ በሩሲያ- የአፍሪካ ትብብር…

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለተቀበላቸው አምስት ሺህ አዲስ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው አንድ ቤተሰብ እንዲኖራቸው አደረገ

የ‹‹አንድ ተማሪ ለአንድ ቤተሰብ›› የተሰኘው ፕሮጀክት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ አምስት ሺህ አዳዲስ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች አንድ ቤተሰብ እንዲኖራቸው የሚያደርገውን መርሃ-ግብር በያዝነው ወር መጨረሻ በይፋ ይጀምራል ተብሏል፡፡ ዩንቨርስቲው ይህን…

በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ኹከቱ ሰክኗል፤ ጠ/ሚ ዐቢይ ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል

አክቲቪስት ጃዋር ‹‹የደህንነት ጥበቃዎቼ በለሊት በፖሊስ ሊነሱብኝ ነው›› ሲል ያቀረበውን ሕዝባዊ ጥሪ ተከትሎ፣ በኦሮሚያ ክልል ‹‹ቄሮ›› ነን በሚሉ ወጣቶች ተቀስቅሶ የነበረው መንገዶችን የመዝጋት፣ የአገልግሎት ተቋማትን የማውደምና ሰዎችን ለጉዳት የመዳረግ ኹከት፣…

በድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳድር በድጋሜ ዛሬ ጧት ግጭት በመከሰቱ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ተዘግተዋል

ራሳቸውን ቄሮ ብለው የሚጠሩ ቡድኖች ከበርገሌና ሌሎች አዋሳኝ የድሬ ዳዋ አካባቢዎች ወደ ጎሮ ሐዲድ አካባቢቢ በመግባት ግጭት ፈጥረዋል፡፡ ብሔርን መሰረት ያደረገ ጥቃት ለማድረስም ሞክረዋል፡፡ ሆኖም የአካባቢው ወጣቶች በመመከት የተደራጀው ቡድን…

በአማራ ክልል አርጎባ የአንበጣ መንጋ ተከሰተ

በአርጎባ ልዩ ወረዳ 07 ቀበሌ የአንበጣ መንጋ ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ታይቷል፡፡ በደረሰ የማሽላ ሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱንም የወረዳው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ የአንበጣ መንጋው ተስፋፍቶ የወረዳው…

“በኃይለመለኮት አግዘው ሕይወት እና ስራዎች”  ላይ ውይይት ሊደረግ ነው

ሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ የመጻሕፍት ንባብና ውይይት ዝግጅት ክፍል ከኢትዮጲስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር “በቅርስ ጥበቃ ጥናትና ምርምር ባለስልጣን የማይዳሰሱ ቅርሶች ከፍተኛ ኤክስፐርት እና የታሪክ ባለሞያ በነበረው “በኃይለመለኮት አግዘው ሕይወት እና ስራዎች”…

የኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች መሰማራቱ ተነገረ

የኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት በክልሉ ጥያቄ መሠረት በኦሮሚያ ክልል ሠላምና ፀጥታን ለማስከበር መሠማራቱ ተነገረ፡፡ የተለያዩ የፀጥታ ችግሮች ባገጠሙባቸው የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በክልሉ መንግሥት ጥያቄ መሠረት ስምሪት መስጠቱን የሀገር መከላከያ ሠራዊት…

የኦሮሞ ፖለቲካ መሪዎች በወቅታዊ ጉዳይ በአክቲቪስት ጃዋር መኖሪያ ቤት መግለጫ ሰጡ

“ከመንግሥት ምላሽ እስከምናገኝ ድረስ፣ የተዘጉ መንገዶች ይከፈቱ፤ ከዚህ በኋላ ምንም ዓይነት ሰላማዊ ሰልፍ አያስፈልግም፤ በጥይት የተመቱባችሁን ሰዎች አሳክሙ፤ የሞቱባችሁን ደግሞ ቅበሩ፡፡ ከሌሎች ሰዎች ጋር ያላችሁን ማኅበራዊ ግንኙነት እንደ በፊቱ ቀጥሉ፡፡…

የሰበታ-ሀዋስ ከተማ ነዋሪዎች በስጋት ውስጥ ነን አሉ

አክቲቪስት ጃዋር መሐመድ ‹‹በፌደራል ፖሊስ ተመድበውልኝ የነበሩ ጠባቂዎቼ ‹በአስቸኳይ መሳሪያችሁን ይዛችሁ ውጡ› የሚል ትዕዛዝ ትላንት ሌሊት ተላለፈላቸው›› ሲል በማሕበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ያሰፈረውን መልዕክት ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ኹከት ተቀስቅሶ…

“ከሰንጋ ተራ እስከ አምስተርዳም”

በአገራችን ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ሚና ከነበራቸው ክስተቶች አንዱ እና ዋነኛው የ 1960ዎቹ “የያትውልድ” ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ነበር:፡፡ የዚህ እንቅስቃሴ አስኳል ደግሞ የያን ጊዜው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ፣ የዛሬው አዲስ…

በአሰላ መንገዶች፣ ሱቆች እና ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ ናቸው ነዋሪዎች በከፍተኛ ሥጋት ውስጥ መሆናቸውን ተናገሩ

የፌዴራል ፖሊስ ትላንት ለሊት ጥበቃዎቼን ሊያነሳብኝ ሞከረ በሚል አክቲቪስት ጃዋር መሀመድ በማኅበራዊ ገጹ የሰጠውን መግለጫ ተከትሎ፣ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች፣ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል፡፡ በዛሬው…

በኦሮሚያ በተካሄዱት የተቃውሞ ሰልፎች ምክንያት በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

ትናንት ሌሊት በአክቲቪስት ጀዋር መሃመድ መኖሪያ ቤት አጋጠመ የተባለውን ክስተት ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች በርካታ ሰዎች ለተቃውሞ በመሰለፍ አደባባይ ወጥተው ታይተዋል፡፡ የተቃውሞ ሰልፍ ከተደረገባቸው ከተሞች መካከል አምቦ፣ አዳማ እና…

This site is protected by wp-copyrightpro.com