Archive

Day: August 5, 2019

ስለ ሥነ-ምኅዳራችን የሣምንቱ አንዳንድ ነጥቦች

ኢትዮጵያችግኝ በመትከል የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረች ዛፎች ለሥነ-ምህዳራችን በጣም አስፈላጊ ከመሆናቸው ባሻገር፣ በሰው ሰራሽ ችግር ምክንያት የሚፈጠርን የ‹‹ግሪን-ሃውስ›› ልቀትን ተፅእኖ ሚዛን ለመጠበቅ እገዛ አላቸው፡፡ በመሆኑም፣  ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት ውስጥ በችግኝ ተከላ የዓለምን ክብረወሰን ማስመዝገቧ ጥቅሙ ከሀገር አልፎ ዓለማቀፋዊም ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በ12 ሰዓታት ውስጥ ብቻ 350 ሚሊዮን ችግኞችን ተክሏል ሲልም eco-warrior princess በድረ…

“ታሪካችን መንገዳችን ነው” ሳሚ- ኦባማ

“አውስትራሊያዊያንን ለማዝናናት አቅጃሁ” በብዙ ኢትዮጵያዊያን፣ በተለይም በውጭ አገራት በሚኖሩ እና በዩቲዩብ ተጠቃሚዎች ዘንድ የሚታወቀው አዝናኙ ‹‹ሳሚ ኦባማ››፣ የራሱን ታሪክ እና አዝናኝ ፈጠራዎችን ለአውስትራሊያ ተመልካቶች  ለማቅረብ አቅዷል፡፡ በትግራይ ክልል ዛና አካባቢ…

በሺዎች የሚቆጠሩ ሕገ-ወጥ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ተገለጸ

በሺዎች የሚቆጠሩ በሕገ-ወጥ መንገድ ከሀገር የተሰደዱ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች፣ በሕጋዊ መንገድ ወደ ሀገራቸው መመለስ መጀመራቸው ተነገረ፡፡ የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት፣ የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እንዳይኖር ባደረገው ጥረት መሠረት፣ በርካቶች ባለፈው በጀት…

በጅማ በጀልባ አደጋ አምስት ሰዎች የት እንደገቡ አልታወቀም

በጅማ ዞን ኦሞናዳ ወረዳ በጊቤ ሰው ሰራሽ ኃይቅ ላይ፣ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችው ባሕላዊ ጀልባ ሰጥማ አምስት ሰዎች የት እንደገቡ አለመታወቁን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡ የወረዳው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፉአድ ከሊፋ፣ አደጋው ቅዳሜ ሐምሌ 27 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 5 ስዓት ከ30 ደቂቃ አካባቢ ወደ አሰንዳቦ ገበያ የሚመጡ 18 ሰዎች ተሳፍረው ሲጓዙ አደጋው መከሰቱ ተነግሯል፡፡ በወረዳው አስተዳደር አካላት፣ በአካባቢው ነዋሪዎች እና በጠላቂ ዋናተኞች አማካይነት የ13 ሰዎች ሕይወት እንደተረፈም ተገልጿል፡፡ የቀሪዎቹ አምስት ሰዎች ፍለጋ የቀጠለ ሲሆን፣…

በኢትዮጵያ የበረሃ አንበጣ ክፉኛ ተፈርቷል

በሶማሌ፣ በኦሮሚያ- ሀረርጌ፣ በድሬዳዋ፣ በዐፋር፣ በዐማራ- ወሎ እና በትግራይ- ራያ እና አላማጣ የበረሃ አንበጣ ተከስቶባቸዋል ተባለ፤ በኢትዮጵያ ስድስት ክልሎች ላይ፣ የበረሃ አንበጣ በግብርና ምርቶች ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የግብርና ሚኒስቴር አስጠነቀቀ፡፡ የበረሃ አንበጣው ከሶማሊያ እና ከየመን ተነስቶ በተለያዩ የምስራቅ አፍሪካ አገራት መታየቱ የተነገረ ሲሆን፣ በኢትዮጵያም በስድስት ክልሎች ላይ የበረሃ አንበጣ መታየቱን የግብርና ሚኒስትር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ብርሀኑ ተናግረዋል፡፡ የግብርና ሚኒስቴር መ/ቤት፣ በቅርቡ ከዓለም አቀፉ የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) የበረሃ አንበጣ በሀገሪቱ ሊከሰት ይችላል የሚል ማስጠንቀቂያ እንደደረሰው ገልፆል፡፡ ድርጅቱ የበረሃ አንበጣው በየመን፣ በሱዳን፣ በኤርትራ፣ በኢትዮጵያ እና በሰሜናዊ ሶማሊያ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ውስጥ፣ በግብርና ምርቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ ስጋት ሊያስከትል ስለሚችል ቀድሞ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ታውቋል፡፡ እንደ አቶ አለማየሁ ብርሀኑ ገለፃ፣ ከጎረቤት አገራት የሚመጣውን የበረሃ አንበጣ መስፋፋት ለመከላከል ተጨማሪ ጥረቶችን በማድረግ እና ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የመከላከል እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡ በግብርና ሚንስቴር የእጽዋት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር…

ከስምንት ሺህ በላይ የቤት ሠራተኞች ሳዑዲ ሊጓዙ ነው

በኢትዮጵያ እና በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ የሚገኙ የውጪ ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ከስምንት ሺህ በላይ የቤት ሠራተኞችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሳዑዲ ለማስገባት በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ታወቀ፡፡ አል መዲና…

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አደረጉ

“ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም የተፈጠረው ክስተት እጅግ አደገኛ እና ከባድ ነበር“ “ኢህአዴግለቀጣዩአገራዊ ምርጫ በጊዜው እንዲካሄድ እየተዘጋጀ ነው“ “አገሪቷያለችበትን ሁኔታ ለመቀየር የፓርቲ ውህደት በጣም አስፈላጊ ነው“ “ኢንተርኔትለሳምንት ሳይሆን እስከ ወዲያኛው ሊዘጋ ይችላል“ (ዜና-ሃተታ) (ሀብቴ ታደሠ እና ራሔል አናጋው) ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጪ ጋዜጠኞች ጋር እምብዛም የመገናኘት ልምድ የሌላቸው ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሐሙስ ሐምሌ 25 ቀን 2011 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በጽ/ቤታቸው ከጋዜጠኞች ጋር ተገናኝተዋል፡፡ ወደ ሥልጣን ከመጡ 16 ወራቶችን ያስቆጠሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ በመደበኛ ሁኔታ ከጋዜጠኞች ጋር ሲገናኙ የአሁኑ ለሦስተኛ ጊዜያቸው ቢሆንም፣ ከሚዲያ የማይጠፉበት የተለያዩ አግባቦችን ሲጠቀሙ ነው የሚስተዋሉት፡፡ ከዚህ በፊት የነበሩት ሁለቱ የኢሕአዴግ ጠቅላይ ሚንስትሮች ከጠ/ሚር ዐቢይ በተሻለ ሁኔታ ጋዜጠኞችን የማግኘት ልምድ እንደነበራቸው ያለፉት ጊዜያቶች ማህደሮች ይጠቁማሉ፡፡ በተለይ ሟቹ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ፣ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጪ ጋዜጠኞች ጋር በአጫጭር ጊዜያት እና በተደጋሚ የመገኛኘት ልምዱ እንደነበራቸው የማይካድ ነው፡፡ ይሁን እንጂ፣ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ በተደጋሚ ቢገናኙም፣ ከሀገር ውስጥ የግል ሚዲያ ጋዜጠኞች ጋር የተገናኙት በመጨረሻ የሥልጣናቸው ማብቂያ ዓመታት ግድም ሲሆን፣ ያኔም በተመረጠ ሁኔታ የሚጋበዙ የግሉ ሚድያ ጋዜጠኞች ወደ ጽ/ቤታቸው ጎራ ማለት ችለው ነበር፡፡ የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ሌጋሲን ተከታይ የነበሩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ከውጪ ጋዜጠኞች ጋር ሳይሆን፣ በተለይ ከሀገር ውስጥ ከጋዜጠኞች ጋር በተደጋጋሚ ሲገናኙ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ ሁለቱ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትሮች በተደራጀ ሁኔታ የተዘጋጁበትን የህዝብ ግኑኝነት ሥራ ለመስራት ከጋዜጠኞች ጋር የመገናኘት ልምዱ ቢኖራቸውም፣ የአሁኑ ጠ/ሚር በተለየ ሁኔታን ጋዜጠኞችን በተደጋጋሚ ወደ ቢሯቸው ጋብዘው ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ አይታይም፡፡ ይህ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋዜጠኞችን እንደ ቀድሞዎቹ ለማቅረብ አለመሞከር የራሱ የሆነ ምክንያት ሊኖረው ቢችልም፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ በተለየ እና ከበፊተኞቹ በሚበልጥ ሁኔታ ለህዝብ ግኑኝነት በሚጠቅማቸው የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች…

የተተከሉትን ችግኞች በቀጣይ በዚህ ዓይነት ዘዴ ተንከባከቡ፡፡

ተከታታይ ክብካቤ ያስፈልጋል! የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተቀብሎ፣ ለችግኝ ተከላው ሆ… ፣ ብሎ የወጣው ህዝብ፤ በጣም ያስደስታል፡፡ አዎን! ያስደስታል፡፡ ነገር ግን፣ ደስታው ቀጣይና ዘላቂ እንዲሆን ክብካቤውም ቀጣይ መሆን አለበት፡፡ ለተከላው የወጣው…

“ኤርታሌ” የእሳተ ጎመራ ፍልቅ-ልቅ ለማስታወቂያ ሥራ ዋለ

ብዙ ሰዎች፣ በኢትዮጵያ ዐፋር ክልል የሚገኘውን ተፈጥሯዊ የእሳተ ጎመራ ፍልቅ-ልቅ ‹‹ኤርታሌ››ን ለማየት የሚያቀኑት፤ በሥፍራው ላይ ጥናት ለማድረግ (ለመመራመር)፣ የተፈጥሮን እንቆቅልሽ ለመመልከት እና ጨለማ በቦታው ሲነግስ እሳተ ጎመራው ሲፍለቀለቅ የሚያሳየውን የቀለማት…

This site is protected by wp-copyrightpro.com