ዜና
Archive

Month: August 2019

የ14 ዓመትዋን ታዳጊ አስገድዶ ደፍሮአል በሚል የተጠረጠረው ግለሰብ ወደ ኢትዮጵያ ሊያመልጥ ሲል ተያዘ

በሀገረ እንግሊዝ የ34 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ የ14 ዓመት ታዳጊዋን አታሎ ወደ ሆቴል ወስዶ ከደፈራት በኋላ ትኬት ቆርጦ ወደ ኢትዮጵያ ሊያመልጥ ሲል ፖሊስ ባደረገው ክትትል ከአየር መንገድ ሊያዝ ችሏል፡፡ ፖሊስ የተጠርጣውን ምስል…

አፋር ዳሎል ላይ በባዶ እግሯ ቆማ ፎቶ የተነሳችው ወጣት መነጋገሪያ ሆናለች

ብሪጅት ታክሬይ የ25 ዓመት የኒውዘላንድ ተጓዝ ስትሆን በኢትዮጵያ አፋር ክልል በሰልፈር በተሸፈነው እና ለአይን በሚማርከው በደናክል ዲፕሬሽን (ዳሎል) በባዶ እግሯ እየተራመደች የተነሳችው ፎቶ ግርምትን አጭሯል ተባለ፡፡ ከሩቅ ሆኖ እንኳን ቦታውን…

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ በአፍ መፍቻ ቋንቋ ያላስተማረን ዓለም ገና የሚገኝ የግል ትምህርት ቤት ዘጋ

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ጋር ተጣብቆ በሚገኘው ዓለም ገና የሚገኘው ኤቨረስት ዩዝ አካዳሚ በክልሉ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ባለማስተማሩ ተዘግቷል፡፡ ሆኖም ትምህርት ቤቱ የሚገኝበት አካባቢ ከአዲስ አበባ ጋር የተጣበቀ በመሆኑ ተማሪዎቹ…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መድሎ እንደተፈፀመባቸው የገለፁ ደንበኛውን ይቅርታ ጠየቀ

አየር መንገዱ የእግር ጉዳት ያላቸውና በአተሸከርካሪ ወንበር ወይም ዊል ቼር የሚንቀሳቀሱ ደንበኛውን ነው ይቅርታ የጠየቀው፡፡ ደንበኛው ከኬንያ ናይሮቢ ወደ አሜሪካ ለመብረር አስቀድመው የጉዞ ትኬት የገዙ ቢሆንም የሚያግዛቸው ሰው ሳይኖር አካልጉዳተኛውን…

ቶሺባ በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርግ ግብዣ ቀረበለት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ቶሺባ ኢነርጂ ሲስትም ሶሉሽን ኮፕሬሽንን በጎበኙበት ወቅት ድርጅቱ በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርግ ግብዣ አድርገዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት ኮፕሬሽኑ የእንፋሎት ተርባይኖች ማምረቻ ቦታን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳስጎበኛቸው የጠቅላይ ሚኒስትር…

ዘንድሮም መንታ መንገድ ላይ

‹‹ኢትዮጵያ መንታ መንገድ ላይ ነች፡፡ አንድም ወደ ተራራው መውጣት፤ ሌላም ወደ ገደሉ መግባት፤›› ብለው ነበር አዛዎንቱ ምሁር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ወራት በፊት በአዲስ አበባ፤ ግዮን ሆቴል በተጋበዙበት አንድ የውይይት…

በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ለአስር ዓመታት ያስቀጣል

ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን የሚከላከል ረቂቅ ሕግ እየተዘጋጀ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ አዋጅ አስታውቋል፡፡ በረቂቅ አዋጁ መሰረትም ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችን ሲያዘዋውር የተገኘ አካል እስከ አስር ዓመታት በሚደርስ ፅኑ…

በምርጫ ሕጉ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ እንደሚቀጥሉ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ

ሰላሳ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 67/2011ን ተቃውመውታል፡፡ ፓርቲዎቹ ሃያ አንቀፆች እንዲሰረዙ አሥራ ሦስት አንቀፆች ደግሞ እንዲሻሻሉም ጠይቀዋል፡፡ ሆኖም ቅሬታቸው ምላሽ ሳያገኝሕጉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አካል ጉዳተኛ ደንበኛውን ከአገልግሎት አገለለ

አየር መንገዱ የእግር ጉዳት ያላቸውና በተሸከርካሪ ወንበር ወይም ዊል ቼር የሚንቀሳቀሱ ደንበኛውን ነው ያገለለው፡፡ ደንበኛው ከኬንያ ናይሮቢ ወደ አሜሪካ ለመብረር አስቀድመው የጉዞ ትኬት የገዙ ቢሆንም የሚያግዛቸው ሰው ሳይኖር አካልጉዳተኛውን ብቻቸውን…

አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ከደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነታቸው ሊነሱ ነው

የደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያ ደርገው ስብሰባ አዲስ ርዕሰ መስተዳድር እንደሚሾም ታውቋል፡፡ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ በሚንስትርነት ማዕረግ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ)…

ዶክተር ቴዎድሮስ አድሐኖም በቶንጋ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ነው

የዓለም ጤናድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሐኖም የ169 ደሴቶች ስብስብ በሆነችው ሀገረ ቶንጋ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡ የሀገሪቱ ዜጎችም በአማርኛ ቋንቋ የተፃፉ የእንኳን ደህና መጡ ፅሁፎችን ከፍ አድርገው…

ባለፈው በጀት ዓመት ከግብርና የውጭ ገበያ 318 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል

ኢትዮጵያ ካለፈው የ2011 ዓ.ም በጀት ዓመት ወደ ውጭ ገበያ ከተላከው ከግብርና ምርት 318 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ በበጀት ዓመቱ 261 ሚሊዮን ዶላሩ ከአበባ ምርት ብቻ የተገኘ…

የባሕር ዳርና አካባቢዋ ፍርድ ቤት በእነጀኔራል ተፈራ ማሞ ላይ የተጠየቀውን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ውድቅ አደረገ

ዐቃቤ ሕግ በአራት ወይም አምስት ጊዜ ቀጠሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ባለማቅረቡ ነው የተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ይግባኙ በፍርድ ቤቱ ተቀባይነት ያጣው፡፡ አቃቤ ሕግ ይግባኝ የማለት መብቱ የተጠበቀ መሆኑንንም ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 አውሮፕላን በእርጥበት ምክንያት ተስተጓጎለ

ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 አውሮፕላን የአዲስ አበባ ማኮብኮቢያው ላይ ውሃ በመቋጠሩ ከትናንት በስቲያ ሰኞ፤ ነሐሴ 19 ቀን በሰላም ማረፍ አለመቻሉ ታውቋል፡፡ ይህ እንግዳ ክስተት በመፈጠሩም አቅጣጫውን ቀይሮ…

በሲዳማ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን የሲዳማ ሀዲቾ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አስታወቀ

በደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኋላ በክልሉ በተለይም በሲዳማ ዞን አንፃራዊ ሰላም መስፈኑን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡ የሲዳማ ራስ ገዝ አስተዳድርን ከሕግ ውጭ ማወጅ ተገቢ አለመሆኑንም የሲዳማ ሀዲቾ ዴሞክራሲያዊ…

ትናንት በአዲስ አበባ ሰውን የደበደቡ ፖሊሶች በወንጀል እንደሚጠየቁ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

በአዲስ አበባ ቄራ አካባቢ ትናንት ነሐሴ 20 ቀን ሁለት የፖሊስ አባላት በአንድ ግለሰብ ላይ ድብደባ የፈፀሙትን ድርጊት ጉዳይ እያጣራ መሆኑን እና በወንጀልና በመተዳዳሪያ ደንብ እንደሚጠይቅ ፖሊስ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡ የፖሊስ አባላቱ…

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ ጃፓን ገቡ

ጠቅላይ ሚንስትሩ በደቡብ ኮሪያ የነበራቸውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ጃፓን ገብተዋል፡፡ ጃፓን ውስጥ በዮኮሃማ ከተማ በሚካሄደው ሰባተኛው የጃፓን እና የአፍሪካ ሀገራት የልማት ጉባዔ ላይም እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡ ከጉባዔው በተጓዳኝ ከጃፓን ከፍተኛ…

ኢትዮጵያና ኤርትራን የሚያገናኘው የየብስ መንገድ በመጭው መስከረም አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው

መንገዱ ግንባታው ተጠናቆ መስከረም 1 ቀን 2012 ዓ.ም ይመረቃል፡፡ ባለፈው ዓመት ነሐሴ የተጀመረው በኤርትራ የሀገር መከላከያ ኃይል የሚገነባው ይህ የ90 ኪሎ ሜትር መንግድ በአሁኑ ወቅት ዘጠና በመቶ መጠናቀቁን ኤሪትራን ፕሬስ…

ኢትዮጵያ ጳጉሜን በበጀት ቀመሯ ባለማካተቷ በየዓመቱ 54 ቢሊዮን ብር እያጣች ነው

በጳጉሜ ወር የገንዘብ ዝውውር ቢኖርም ወሩ በበጀት ቀመሩ ግን አለመካተቱ ሀገራዊ ኪሳራ እያስከተለ መሆኑን የዘርፉ ተመራማሪ ተናገሩ፡፡ ጳጉሜ ስድት በሚል መፅሐፋቸው የሚታወቁት በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ኃብት አስተማሪው ፋሲል ጣሰው እንደገለፁት…

የፖለቲካ ፓርቲዎችን ተቃውሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውድቅ አደረገው

ሰላሳ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 67/2011ን ተቃውመውታል፡፡ ፓርቲዎቹ ሃያ አንቀፆች እንዲሰረዙ አሥራ ሦስት አንቀፆች ደግሞ እንዲሻሻሉም ጠይቀዋል፡፡  በአዋጁ ላይ ካሰሟቸው ተቃውሞዎች መካከል ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች…

በመሬት ወረራ ሳቢያ አየር መንገዱ ሊዘጋ ይችላል ተባለ

በድሬደዋ እየተበራከተ የመጣው ህገ ወጥ የመሬት ወረራ  ለስራው ፈተና እንደሆነበት የድሬደዋ  አየር ማረፊያው ገለጸ፡፡ ችግሩ በዚሁ ከዘለቀም አየር ማረፊያውን እስከማዘጋት እንደሚደርስ የተገለጸ ሲሆን  ለችግሩ መንሰራፋት ደግሞ  የአስተዳደሩ ችግር መሆኑን ተገልጿል፡፡…

ኢትዮጰያ እና ኬንያ በጁባላንድ ጉዳይ ውጥረት ውስጥ ናቸው ተባለ

በጁባላንድ በተደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሼህ አህመድ ኢስላም ማዶቤ በድጋሚ መመረጣቸው ይታወቃል፡፡ ምርጫው ፍትሃዊ እንዳሆነ የተገለጸ ሲሆን ለምርጫውም ኬንያ ደጋፍ እንዳደረገች ተሰምቷል፡፡ ምርጫውን ባለመቀበል በጁባላንድ ግጭት እንዳይቀሰቀስ የተፈራ ሲሆን፤ በቀጠናው ግጭት…

ዝናብ እና ኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያ እና ግብርና የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ

ኢትዮጵያ ውሃን ከዕለት ተዕለት መሠረታዊ ፍላጎቶቿ በተጨማሪ ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫነት፣ እንዲሁም ለመስኖ ሥራ ትጠቀምበታለች፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ ሲከሰት በሀገሪቱ የውሃ እጥረት ይጨምራል፤ የመሬት መሸርሸርም ከፍ ይላል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ የመሬት መሸርሸር ችግርን…

ከእረኝነት እስከ ፈጠራ ባለሟልነት

በደቡብ ክልል ሸካ ዞን ልዩ ቦታው ከላቻ የተባለ ሥፍራ የተወለደው መልካሙ ታደሰ የዘንድሮው ሶልቭ አይቲ የፈጠራ ሥራ ውድድር ባለ ሶስት አውታር ማተሚያ (3ዲ ፕሪንተር) በመፍጠር የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል፡፡ ከአርባ ደቂቃ…

ኢትዮጵያና ኬንያ ከጁባላንድ ጋር ለመሥራት እየጣሩ ነው ተባለ

የጁባ ላንድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሕመድ ማዶቤ ሁለት ሶስተኛውን  ድምፅ በማግኘት ማሸነፋቸው ተነግሯል፡፡ ኬንያ የጁባላንድ የድጋሚ ምርጫ ላይ ለፕሬዝዳንቱ ማዶቤ ድጋፍ እንዳደረገች ተነግሯል፡፡ ይህም ደግሞ ሀገሪቱ ከጁባላንድ ጋር ያለትን አጋርነት ማጣት…

ፖሊስ በቁልቢ ገዳም አስተዳዳሪ ግድያ የተጠረጠሩ 11 ግለሰቦችን አሰረ

በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ዋና አስተዳዳሪ መልዓከኃይል ቆሞስ አባ እንቁስላሴ ድንገተኛ ሞት ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሲስ መምያሪያ አስታውቋል፡፡ ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ…

ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በ4 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባውን ትምህርት ቤት አስመረቀ

አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ (ሻለቃ) ሚያዝያ 27 ቀን 2011 ዓ.ም በዐማራ ክልል የሚገኘውን የገልኩ የዳስ ትምህርት ቤት በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ፃግብጂ ወረዳ ለመገንባት ቃል በመገባው መሠረት፣ ትምህርት ቤቱን አስገንብቶ በዛሬው…

ኤል አምስት አንድ (የኢትዮጵያ የጥፋት ምስጢር) መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

የደራሲ ዮናስ ዓለሙ ‹‹ኤል አምስት አንድ›› (የኢትዮጵያ የጥፋት ምስጢር) የተሰኘ መጽሐፍ ዛሬ ነሐሴ 17 ቀን 2011 ዓ.ም  ከቀኑ 11 ሰዓት ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ይመረቃል፡፡ በምርቃቱ ላይ  ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን፣  ጋዜጠኛ…

ሀገረሰባዊ እምነት በሰባት-ቤት ጉራጌ -፪-

ዥምወድ ስለዥምወድ ማንነት የተለያዩ አፈታሪኮች ይነገራሉ፡፡ ከየት እንደመጣች ወይም ቀደም ስላለው የቤተሰቦቿም ሆነ የሷ ታሪክ የሚተረከው ታሪክ  ሁለት አይነት  ነው፡፡ የመጀመሪያው ታሪክ የዥምወድ ቀደም ያለ ታሪክ አይታወቅም የሚለው ነው (ጎይታኩየ…

መላ የወባ ትንኞች እንዳይናደፉ

መልካሙ ዜና እንደዚህ ይላል፡- ማጣቀሻ አንድ ኅዳር 18 ቀን 2011 ዓ.ም ፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት፤ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ስለ ወባ በሽታ ጉዳይ “በኢትዮጵያ ከወባ በሽታ ጋር በተያያዘ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር…

ለአንድ ዓመት በፖሊስ ሲፈለጉ የቆዩት የቀድሞው የሀዋሳ ከንቲባ ታሰሩ

የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል። ተከሳሹ ከሰኔ 05 እስከ 12 ቀን 2010 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ የወላይታና ሲዳማ ብሔሮችን…

ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመዋጋት ወደ ተግባር መገባቱን ተነገረ

የሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን እና ባህሎችን ለመዋጋት ወደ ተግባር መግባቱን ገለጸ፡፡ የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ ፤ ጎጂ ባሕላዊ ደርጊቶችን ለመዋጋት ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባታቸውን…

የኩላሊት ህክምና ሆስፒታል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ በ18 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የኩላሊት ህክምና ሆስፒታል በኳታር መንግስት ሊገነባ ነው፡፡ የኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ተበጀ በርሄ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን ከኳታር…

ኢዴፓ ኢዜማ ንብረቱን በሕገ ወጥ መንገድ እየተገለገለበት እንደሆነ አስታወቀ

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ቢሮውን ጨምሮ የተለያዩ ንብረቶቹን ያለአግብብ እየተገለገለባቸው እንደሆነ አስታውቋል፡፡ የተለያዩ ፓርቲዎች ራሳቸውን አክስመው ኢዜማን ሲመሰርቱ አራት የቀድሞ የኢዴፓ አባላት ወደ ኢዜማ…

ከኮንሶ ወደ ዞን መቀየር ጋር ተያይዞ በደቡብ ኢትዮጵያ ዝርፊያ እና ድብደባ እየተፈፀመ ነው

በደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በሰገን ወረዳና አካባቢው ነዋሪዎች ላይ ዝርፊያ፣ድብደባና እንግልት እየተፈፀመ ነው፡፡ ዝርፊያው የተፈፀመው ቤት ለቤት በመዘዋወር ነው፡፡ ዝርፊያ ፈፃሚዎቹ በኮማንድ ፖስት የሚመሩ ታጣቂዎች መሆናቸውንም የአካባቢው ኗሪዎች ገልፀዋል፡፡ ግጭቱ…

This site is protected by wp-copyrightpro.com