ዜና
Archive

Month: July 2019

የዓለም ምግብ ፕሮግራም 196 ሚሊዮን ዶላር እንደሚስፈልገው አስታወቀ

ሳዑዲ250 ሺህ ሜትሪክ ቶን ቴምር ረዳች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚያከናውነው የሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት የሚውል 250 ሜትሪክ ቶን የቴምር እርዳታ ከሳዑዲ አረቢያ መንግሥት አገኘ፡፡ የዓለም ምግብ…

በምዕራብ ጉጂ ዞን በታጣቂዎች የሰው ሕይወት አለፈ፤ ንብረት ተቃጠለ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት፣ በምዕራብ ጉጂ ዞን፣ በአንድ-አንድ ወረዳዎች የታጠቁ ኃይሎች ተሽከርካሪዎችን አግተው በማቃጠል የሹፌሮቹን ህይወት አጥፍተዋል ሲሉ ምንጮች ለኢትዮ-ኦንላይን አስታወቁ። ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 24 ቀን 2011 ዓ.ም በቀርጫ ወረዳ ቦረቱ ቀበሌ አካባቢ ሦስት አይሱዙ የጭነት መኪኖች በታጠቁ ኃይሎች ተይዘው አንደኛው ሹፌር ወዲያውኑ የተገደለ ሲሆን፣ ሌላኛውን ሹፌር አግተው ወደ ጫካ ወስደዉታል ያለን የአከባቢው የመረጃ ምንጫችን ነው። በተመሳሳይም በፊንጨዋ መንገድ፣ በሶዳና በዳመጋዳ በሚባሉ አካባቢዎች ሰሞኑን በታጠቁ ኃይሎች ሦስት መኪኖች ተቃጥለው ሹፌሮቹም ተገለዋል ተብሏል። በዚህም ምክንያት፣ በአከባቢው የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች በተፈጠረባቸው ስጋት ወደ ቀርጫ ከተማ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዳቆሙ ለማወቅ ችለናል። የህዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ሰጪዎች ዛሬ ከዞኑ ባለስልጣናት እና ከመከላከያ አባላት ጋር ባደረጉት ዉይይት፣ በፀጥታው ጉዳይ ስጋት እንዳይገባቸዉ እና ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ካግባቧቸዉ በኋላ፣ ከዉይይቱ እንደወጡ በቀርጫ ወረዳ ሹፌሮች እንደታገዱና እንደተገደሉ ስላወቅን፣ አሁንም ቢሆን የትራንስፖርት አገልገሎት መስጠት አንችልም ያሉት ኢትዮ-ኦንላየን ያነጋገራቸው አሽከርካሪዎች ናቸው።

የተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ ዓዋጆችን እና የውሳኔ ሃሳብ አጸደቀ

የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ዛሬ ሐምሌ 24 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው፤ የተለያዩ ዓዋጆች እና የውሳኔ ሃሳቦች ማፅደቁ ተነግሯል፡፡ ምክር ቤቱ ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታቸውን ለሚለቁ የሚከፈል የካሳ ሁኔታን ለመወሰን የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ አፅድቋል፡፡ በመሆኑም፣ የከተማ ልማት እና ኮንሰትራክሽን ሚኒስቴር በከተማም ሆነ በገጠር ባለይዞታዎች ለህዝብ ጥቅም መሬት እንዲለቁ ሲደረግ፣ የተነሺዎችን በሕገ መንግስቱ የተቀመጡ ድንጋጌዎች ባከበረና በመሬት ዘርፍ መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ርብርብ ለመደገፍና የመንግሥትን ልማታዊነት ለማረጋገጥ በሚያስችል አግባብ እንዲሆን ዓዋጁ ተሻሽሎ እንደቀረበ ምክር ቤቱ አስታወቋል፡፡ በሌላ በኩል፣ ምክር ቤቱ የጉምሩክ ዓዋጅን ለማሻሻል ተዘጋጅቶ የቀረበውን ረቂቅ ዓዋጅ ማጽደቁ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪ፣ ምክር ቤቱ ካጸደቃቸው ጉዳዮች መካከልም…

ፅናት እና ኢትዮጵያዊነት ላይ ያተኮረ የኪነጥበብ ምሽት ዓርብ ይካሄዳል

የቃል እና ዜማ ወርዊ የጥበብ ምሽት ዓርብ ሐምሌ 26 ቀን 2011 ዓ.ም ‹‹ፅናት እና ኢትዮጰያዊነት›› ላይ በማጠንጠን የሚካሄድ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጥበባዊ ምሽቱ የሚከወነው እምቢልታ ሆቴል ከፍ ብሎ በሚገኘው ገነት…

የጌዴኦ የነፍስ ጥሪ

በአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ሥር በሚገኘው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የተለያዩ ዞኖች የክልልነት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ወላይታ፣ ሲዳማ እና ከፋን ጨምሮ ወደ አስር የሚጠጉ ዞኖች በየራሳቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የክልልነት…

ኢቦላ እንዳይዘልቅ እየተጠበቀ ነው

ኢትዮጵያ የኢቦላ ቫይረስ ወደ አገሪቱ እንዳይሰራጭ ለመከላከል በመላው አገሪቱ ከ290 በላይ የጤና መኮንኖች ለቅድመ መከላከል ሥራ በድንበር መግቢያ እና መውጫ ጣቢያዎች አካባቢ ማሰማራቷን አስታወቀች፡፡ በሀገራችን የኢቦላ ቫይረስ እንዳይሰራጭ፣ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃ ባላቸው ኤርፖርቶች ውስጥ የፍተሻ እና የ‹‹ኳራንቲን›› ማዕከላት ቀደም ሲል ተቋቁሟል ሲሉ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በየነ ሞገስ በሰጡት…

የድሬ-ዳዋ አስተዳድር በባሕላዊ የሽምግልና እሴቶች ሊወያይ ነው

የድሬ-ዳዋ ከተማ አስተዳደር በባሕላዊ የሽምግልና እሴቶች ጉዳይ ሐምሌ 27 ቀን 2011 ዓ.ም ሊወያይ ነው፡፡ የድሬ-ዳዋ የተግባቦት እሴቶች ጎላ ብለው ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የድሬ-ዳዋ ከተማ አስተዳድር፣ የድሬ-ዳዋ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ እና…

በጋምቤላ የስደተኞች ማቆያ ማስፋፊያ ሊደረግለት ነው

ከደቡብ ሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት ሸሽተው፣ በኢትዮጵያ ጋምቤላ ክልል የስደተኞች ማቆያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች፤ ከስደት ጋር በተያያዘ የሚገጥማቸውን የአዕምሮ ጤና መቃወስን ለመከላከል እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ ለአእምሮ መረበሽ ተጠቂ ለሆኑ ስደተኞች የማገገሚያ ሕክምና ማዕከል ማስፋፊያ እየተደረገለት መሆኑን የስደት ተጎጂዎች ማዕከል አስታውቋል፡፡ ማዕከሉ፣ ልዩ የአዕምሮና የስሜት ቀውስ ያጋጠማቸውን ስደተኞችን የባለሙያ ምክር እንዲያገኙ በማድረግና የተለያዩ ሥልጠናዎችን በመስጠት ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡ በክልሉ ያሉ አንድ-አንድ ድርጅቶች፣ ውስን የአእምሮ ጤና ፕሮግራሞችን ብቻ የሚሰጡ ናቸው፤ ነገር ግን፣ በስደተኞች ካምፕ ውስጥ ያለውን የአዕምሮ ሕክምና ክፍተት ለመሸፈን አልቻሉም፡፡ ስለዚህ፣ ይህ ማዕከል ማስፋፊያ ተደርጎለት ከደቡብ ሱዳን በተለያዩ ጥቃቶች በድብዳባ፣ በፆታዊ ጥቃትና በጦርነት ቀውስ ሰለባ የሆኑትንና እርዳታ የሚሹ ስደተኞች በቀጥታ የሚረዳ ነው የሚሆነው ተብሏል፡፡ የባለሙያ ምክር ያገኙ ስደተኞች፣ በጣም ጥሩ ለውጥ እንዳመጡ እየነገሩን፣ ጓደኞቻቸውንና ጎረቤቶቻቸውን ወደ ማዕከሉ በማምጣት የቡድን የምክር አገልግሎት እንዲያገኙ እያደረጓቸው ነው ያሉት፣ በኢትዮጵያ የስደት ተጎጂ ሰዎች ማዕከል ዳይሬክተር ማኪ ካቶህ ናቸው፡፡ በተጨማሪም፣ በካምፑ ለስደተኞች ጠቃሚ የሆኑ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ሌሎች ድርጅቶች ቢኖሩም፣ ሥነ-ልቦናዊ እንክብካቤ የሚሰጡ አይደሉም፤ ስለዚህ፣ የስደተኞቹን ሥነ-ልቦና ለማጎልበት አዲሱ የፈውስ ማዕከል ግንባታ በጥሩ ሁኔታ በመከናወን ላይ ያለ ሲሆን፣ በሚቀጥሉት ወራት ወይም ዓመት የምንሰጠውን አገልግሎት እናስፋፋለን ብለን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ በካምፑ በተደረገ የአዕምሮ ጤና ጥናት፣ በርካታ ስደተኞች ይህን የአዕምሮ ጤና ህክምና ማዕከል እንዲኖርና እንዲስፋፋ የሚፈልጉ ናቸው ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያና ጅቡቲ የከባድ ማሽን ገበያቸውን ለማሳደግ እየሰሩ እንደሆነ ታወቀ

ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የከበባድ ማሽን ግብይታቸውን በእጥፍ ለማሳደግ በመሥራት ላይ እንደሚገኙ አሳወቁ፡፡ ሁለቱ አገራት፣ ከውጪ የሚያስገቧቸውን የከባድ ማሽኖች ግብይት በ 2018 እ.ኤ.አ ከነበረው ከሦስት መቶ ሚሊዮን ዶላር በላይ ገበያ በ2026…

የድሬ-ዳዋ አስተዳድር በባሕላዊ የሽምግልና እሴቶች ሊወያይ ነው

የድሬ-ዳዋ ከተማ አስተዳደር በባሕላዊ የሽምግልና እሴቶች ጉዳይ ሐምሌ 27 ቀን 2011 ዓ.ም ሊወያይ ነው፡፡ የድሬ-ዳዋ የተግባቦት እሴቶች ጎላ ብለው ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የድሬ-ዳዋ ከተማ አስተዳድር፣ የድሬ-ዳዋ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ እና…

ወጣቶች ትኩረት ያጡ ዕንቁዎች

(ሶሲዮሎጂ፤ ጥናት አከል-ምልከታ) ”ጋሼ!…” አለኝ ታናሽ ወንድሜ፤ ድንገት፡፡ ”ጋሼ! ለምንድን ነው የምንኖረው?!” አለኝ ጥልቀት ባለውና አንጀት በሚበላ አንደበት፡፡ አየሁት፡፡ እየቀለደ አይደለም፡፡ ፊቱን ቅጭም አድርጎ አንዳች መልስ ከኔ ይጠብቃል፡፡ ይህን ሊያሳስበው…

በሽብርተኝነት የተከሰሱት የርሃብ አድማ እያደረጉ ነው

ሦስት እሥረኞች በርሃብ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ በእሥር ላይ የሚገኙ ዜጎች፣ የርሃብ አድማ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ምንጮች ለኢትዮ-ኦንላይን አስታወቁ፡፡ ‹‹እኛ የህሊና (የግፍ) እሥረኛ እንጂ፣ አሸባሪዎች አይደለንም››…

አሜሪካ ዜጎቿን አስጠነቀቀች

የአሜሪካ ኤምባሲ፣ የተሟላ የሚዲያ አቅም ግንባታ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ ወደ ኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የሚጓዙ ዜጎች ከጉዟቸው እንዲቆጠቡ ሲል አስጠንቅቋል፡፡ ከአዲስ አበባ ውጪ በአደጋ ጊዜ ለዜጎቹ…

በኹከት የተፈናቀሉ ዜጎች በሃይማኖት ተቋማትና በተለያዩ ሥፍራዎች ተጠልለው እንደሚገኙ ተገለጸ

በሲዳማ ዞን በተፈጠረ ኹከትና ግርግር፣ ከመኖሪያ ሥፍራቸው የተፈናቀሉ በርካታ ዜጎች ውስጥ የተወሰኑት፣ በሃይማኖት ተቋማት ቅጥር ጊቢ እና በተለያዩ ሥፍራዎች ተጠልለው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ቦሬ ቅድስት ማርያም…

ኢትዮጵያ በማዕድን የምታገኘውን ገቢ ለማሳደግ እየሰራች መሆኑ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በተያዘው የበጀት ዓመት፣ በማዕድን ዘርፍ የምታገኘውን ገቢ በስድስት እጥፍ ለማሳደግ ማቀዷን ይፋ አደረገች፡፡ ይህን ትልቅ ዕቅድ ለማሳካት፣ ሀገሪቷ የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ማቋቋሟን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በብሔራዊ ኮሚቴው አባልነት የተውጣጡት የተለያዩ…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ግዢ መፈጸሙን እንደቀጠለ ነው

“ንሥረ-ኢትዮጵያ” በሚል ሥያሜ፣ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ከ73 ዓመታት በፊት የተቋቋመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከተለያዩ ተቋማት አዳዲስ አውሮፕላን ግዢ መፈጸሙን እንደቀጠለ መሆኑ ተገለጸ፡፡ በአዳዲስ አውሮፕላን ግዢ ሂደት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የካናዳ ሀቪላንድ አየር መንገድ ከሥምምነት ደርሰው፣ ደስታቸውን በጋራ…

ደኢሕዴን ተጠያቂ የምክር ቤት አባላትን “ያለመከሰስ-መብት” ሊያነሳ ይችላል ተባለ

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ከፍተኛ የአመራር አባላት፣ በህዝባዊ ውይይት ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቅርቡ ደኢሕዴን በሕግ ተጠያቂ የሆኑ የምክር ቤት አባላትን ‹‹ያለመከሰስ-መብት›› ሊያነሳ ይችላል ተብሏል፡፡ በደቡብ ክልል የሚነሱ…

የኦሮሞ ጥናት ማዕከል ዋና ጽ/ቤቱን አዲስ አበባ እንዲከፍት ተጠየቀ

የኦሮሞ ጥናት ማኅበር ጉባዔ (ኦሮሞ ስተዲስ አሶሴሽን /‹‹ኦሳ››) ዛሬ እሁድ ሐምሌ 21 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ ያከናወነውን ጉባዔ አጠናቀቀ፡፡ ትውልደ ኤርትራው ‹‹ሶሲዮሎጂስት›› አስመሮም ለገሠ (ፕ/ር) የገዳ ሥርዓት…

በምዕራብ ኦሮሚያ ሰዎች በገፍ እየታሰሩ መሆኑ ተጠቆመ

– በአምቦ እና ንዳቀኝ ከተሞች ከ150 ሰዎች በላይ ታሥረዋል – በጀልዱ የኦፌኮ ጽ/ቤት ተዘግቷል – የገፍ እሥሩ ‹‹ኦነግ ሾኔ››-ን ለማዳከም ነው- ተብሏል በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት፣ በምዕራብ ኦሮሚያ፣ ምዕራብ ሸዋ ዞኖችና…

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ባልደረቦች፣  ጓደኞች እና ትዝታው

– ወጥቶ-አደር፣ ንሥረ- ኢትዮጵያ! በ196ዐዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ከሐረር መድኃኒዓለም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አጠናቅቄ ነበር፡፡ ከዚያም፣ የኢትዮጵያ ቴሌኰሙኒኬሽን ቦርድ ተቋም የሚሰጠው የቴክኒክ ትምህርት ሙያ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ገባሁ፡፡ የሁለት ዓመታት ተኩል ሥልጠናውን…

232 ሚሊዮን ደርሰናል

የአለም ሚዲያ የኢትዮጵያን ሪከርድ እየዘገበ ነው በሀገር ደረጃ እስካሁን በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ቀን፣ 232 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶክተር) ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም አስታወቁ። ይህንኑ ተከትሎ በመላው ዓለም ላይ የሚገኙ ታላላቅ ሚዲያዎች ለኢትዮጵያ የሪከርድ ዜና ሰፊ ዘገባ እየሰጡት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ዜናውን…

ኢትዮጵያን በብሔር መከፋፈል ለምን?

ዓለማቀፉ የቀይ መስቀልና የቀይ ጨረቃ ማሕበራት ፌዴሬሽን በሪፖርቱ ይፋ እንዳደረገው፣ በኢትዮጵያ 3 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዜጎች፣ በሀገር ውስጥ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ እንደ ሪፖርቱ ሀተታ በዚህም ኢትዮጵያ ከዓለም የአንደኛነት ደረጃን ይዛለች፡፡ የዚህ…

የማህጸን ጫፍ ካንሰር ሕዝባዊ ንቅናቄ ይፈልጋል ተባለ

በኢትዮጵያ የማህጸን ጫፍ ካንሰር በሽታ ልዩ ትኩረት ካልተሰጠው፣ አገሪቱን ከፍተኛ ዋጋ ሊያስከፍላት እንደሚችል ተጠቆመ፡፡ በማህጸን ጫፍ ካንሰር ህመም ዙሪያ በአዲስ አበባ ውስጥ በሳንቴ የሕክምና ኮሌጅ አዘጋጅነት ቅዳሜ ሐምሌ 20 ቀን…

ፎቶ-ገለፃ

የተባበሩት ዐረብ ኤምሬት፣ የዛይድ ፋውንዴሽን ልዑካን ቡድን፣ በኢትዮጵያ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝቷል፡፡ ይህ ፕሮጀክት፣ በአዲስ አበባ ካሉ ትልልቅ መስጊዶች ውስጥ አንዱና በመቶዎች የሚቆጠሩ አማኞችን የሚይዘው፣ እንዲሁም የባህል ማዕከል የሆነውን ባለ ሦስት ወለል የአል ኑር መስጊድን…

የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ለሦስት መቶ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ሥልጠና ሰጠ

በኢትዮጵያ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ኤምባሲ፣ በአዲስ አበባ ለሚኖሩ ሦስት መቶ ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የማጎልበት ሥልጠና ሰጠ፡፡ ሥልጠናው ከኢትዮጵያ መንግሥት የንግድ ሥራ ፈጠራ ልማት ማዕከል እና ከተባበሩት መንግስታት ልማት ፕሮግራም ጋር…

የአፍሪካና ቻይና የአየር ግንኙነት ካለፉት አስርት ዓመታት ወዲህ እድገት አሳይቷል ተባለ

በአፍሪካና በቻይና መካከል ያለው የአየር ግንኙነት፣ ካለፉት አስርት ዓመታት ወዲህ ከፍተኛ እድገት እያሳየ መምጣቱ ተነገረ፡፡ በአሁኑ ወቅት፣ በአማካይ በቀን ስምንት የቀጥታ በረራዎች በአፍሪካ አገራትና በቻይና ይደረጋሉ ተብሏል፡፡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር…

ወደ ውጭ ከተላኩት የቡና እና የቅባት እህሎች 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ተገኘ

በዘንድሮው የ2011 ዓ.ም የበጀት ዓመት፣ ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ አገራት ከተላኩ የቡና እና የቅባት እህሎች፣ አንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለጸ፡፡ ወደ ውጭ አገራት የተላኩት የእህል ምርቶች፡- ቡና፣ ሰሊጥ፣…

ሀዋሳ ዝቅተኛ የሀገር ውስጥ መንፈሳዊ ጎብኚ አስተናገደች

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ፣ በዓመታዊ የገብርዔል መንፈሳዊ በዓላት ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሀገር ውስጥ ቱሪስት ማስተናገድ የጀመረችው ሀዋሳ፣ ትላንት ዓርብ ሐምሌ 19 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀደምት ጊዜያት አነስተኛ ቁጥር ያለው መንፈሳዊ…

በምዕራብ ኦሮሚያ ሰዎች በገፍ እየታሰሩ መሆኑ ተጠቆመ

በአምቦ እና ንዳቀኝ ከተሞች ከ150 ሰዎች በላይ ታሥረዋል በጀልዱ የኦፌኮ ጽ/ቤት ተዘግቷል የገፍ እሥሩ ‹‹ኦነግ ሾኔ››-ን ለማዳከም ነው- ተብሏል በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት፣ በምዕራብ ኦሮሚያ፣ ምዕራብ ሸዋ ዞኖችና ወረዳዎች ውስጥ በርካታ ሰዎች…

የኦሮሞ ጥናት ማዕከል ዋና ጽ/ቤቱን አዲስ አበባ እንዲከፍት ተጠየቀ

የኦሮሞ ጥናት ማኅበር ጉባዔ (ኦሮሞ ስተዲስ አሶሴሽን /‹‹ኦሳ››) ዛሬ እሁድ ሐምሌ 21 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ ያከናወነውን ጉባዔ አጠናቀቀ፡፡ ትውልደ ኤርትራው ‹‹ሶሲዮሎጂስት›› አስመሮም ለገሠ (ፕ/ር) የገዳ ሥርዓት…

እስራኤላዊው ግለሰብ ከኢትዮጵያ እስር ቤት በነጻ ተለቀቀ

እስራኤላዊው ነጋዴ ሜናሼ ሌቪ በኢትዮጵያ ማረሚያ ቤት፣ ከ2015 እ.ኤ.አ ጀምሮ ባልተጣራ ክስ በማዕከላዊ አስር ቤት በአሰቃቂ ሁኔታ ታስሮ ቆይቶ በመንግሥትና ቤተ እስራኤላውያን እስረኞች በሚደግፈው አሌፍ በተባለ ድርጅት ትብብር ከእስር እንደተፈታ…

ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማሳደግ እፈልጋለሁ አለች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በግብፅ አሌክሳንድሪያ ትላንት ሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ተገኝተው ከግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታ አል ሲሲ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም ወቅት አቶ ገዱ ኢትዮጵያ ከግብፅ…

72 ኢትዮጵያውያን በሕገወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጡ ሲሉ ተያዙ

በዐፋር ክልላዊ መንግሥት፣ ረቡዕ ሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ሌሊት ላይ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጡ የነበሩ 72 ኢትዮጵያውያን በክልሉ ፖሊስ ተያዙ፡፡ ግለሰቦቹ በሦስት የጭነት መኪናዎች በመሆን በጅቡቲ አድርገው ቀይ ባህርን አቋርጠው ወደ…

ከኢሕአዴግ መንደር! የተንበረከኩ ትንንስ ሰብዕናዎ

ጥቂት ሥለ ህወሓት-መር መከላከያ፡- ሠላም- ወንድሞች! አማረ እባላለሁ፤ የዓይናለም ልጅ፡፡ (“የገበሬ ልጅ ነኝ- የአርሶ በላተኛ፣ ሌት ተቀን ታታሪ፤ ያልሆንኩኝ ዳተኛ፤ ከአባቴ ተምሬ፣ አለኝ ልዩ ሞያ- አሃሃሃሃሃ…”) አምባቸው መኮንን (ዶ/ር)፣ ተስፋዬ…

ኦፌኮ ከ25 ሺህ ዶላር በላይ አሽሽተዋል ያላቸውን የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አገደ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ፓርቲ፣ ከ 25 ሺህ ዶላር በላይ የፓርቲውን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል ያላቸውን የፓርቲው ከፍተኛ አመራር ኦቶ ነጋሳ ኦዶ በሕግ ሊጠይቅ ነው፡፡ ግለሰቡን ከሦስት ሳምንት በፊት ከሥራ…

This site is protected by wp-copyrightpro.com