ዜና
Archive

Category: ፖለቲካዊ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ፣ ኢዜማ የመንግሥት ሥራዎችን የሚከታተሉ 22 ትይዩ የካቢኔ ሚኒስትሮችን አዋቅሮ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ።

ኢዜማ የራሱን ትይዩ ካቢኔ ማቋቋሙን ባሳወቀበት መግለጫው እንዳመለከተው፣ ይህ ትይዩ ካቢኔ የዕለት ከዕለት የመንግሥት ተግባራትን መከታተል፣ የሚወጡ ረቂቅ ሕጎችን መተቸት፣ የፖሊሲ ንድፈ ሐሳቦችና ማውጣትና መሰል ሥራዎችን ያከናውናል። የፓርቲው ትይዩ ካቢኔ…

“ዘመቻችን የኢትዮጵያን ሀገረ-መንግሥት የማጽናት ተልዕኮ ነው” የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት

አሸባሪው ትህነግ ከፍጥረቱ ጀምሮ ፀረ-ኢትዮጵያ ሆኖ የተነሳ ድርጅት ነው፡፡ በተለይም የአማራን ሕዝብ እንደ ቀዳሚ ጠላት ፈርጆ መነሳቱ በታሪክ የተመዘገበ እውነታ ነው፡፡ ሴረኝነት፣ ጸረ-ሕዝብነት፣ የግዛት ተስፋፊና ተገንጣይነት የዚህ ድርጅት መገለጫ ባህሪያት…

በአፋር ክልል 7 ቀበሌዎች ሊከፈቱ የነበሩትን 30 የምርጫ ጣቢያዎች እንዳይቋቋሙ ቦርዱ ውሳኔ አሳለፈ

በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎች በአቅራቢያቸው ባለ ሌላ ቀበሌ መመዝገብ እና ድምጻቸውን መስጠት የሚችሉ መሆኑን አስታውቋል የምርጫ ክልሎች የየትኛውም የመንግስት አስተዳድር መዋቅር አካላት አለመሆናቸውንም ቦርዱ አስታውቋልየአፋር ክልል 7 ቀበሌዎች ሊከፈቱ የነበሩትን 30 የምርጫ…

ቭላድሚር ፑቲን የኮሮና ቫይረስ ክትባት ወሰዱ

በሩሲያ 4. 3 ሚሊየን ገደማ ሰዎች ሁለቱንም ዶዝ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ወስደዋል ሩሲያ እስካሁን ስፑትኒክ ቪ የተባለውን ጨምሮ 3 አይነት ክትባቶችን አስተዋውቃለች የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት…

ኮንጎ ሪፐብሊክን ለ37 ዓመታት የመሩት ዴኒስ ሳሱ ንጉሶ ምርጫ አሸነፉ

ፕሬዘዳንቱ በዚህ ምርጫ ላይ 88 በመቶ ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸው ተገልጿል የፕሬዘዳንት ዴኒስ ሳሱ ዋነኛ ተቀናቃኝ የነበሩት ብራይስ ኮሌላስ በኮሮና ምክንያት ከምርጫው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል ባሳለፍነው እሁድ በኮንጎ…

ሱዳን ከኢትዮጵየ ጋር በሕዳሴው ግድብና በድንበር ጉዳይ በዩኤኢ የቀረበላትን የ ላደራድራችሁ ጥያቄ መቀበሏን ገለጸች

በተለይ ከድንበር ጋር በተያያዘ የሱዳን እና ኢትዮጵያ አለመግባባት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አይሏል የዩኤኢን ጥያቄ እና ጥያቄውን ሱዳን መቀበሏን በዜና መልክ መስማታቸውን አምባሳደር ዲና ገልጸዋል የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሕዳሴው ግድብና በድንበር ጉዳይ…

በአክሱም ከተማ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈፀሙን ኢሰመኮ ገለፀ

የአክሱሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወይም የጦር ወንጀል ሊሆን ስለሚችል በክልሉ የተሟላ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል ብሏል ኮሚሽኑ በሁለት ቀናት ከአንድ መቶ በላይ ሲቪል ሰዎች በአክሱም ከተማ በነበሩ የኤርትራ ወታደሮች…

“የክልሉን ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በጅምላ መውቀስና ተጠያቂ ማድረግ ፍጹም ነውርና የማይመጥን ፍረጃ ነው”-አማራ ብልጽግና

ኦሮሚያ ብልጽግና የልዩ ኃይል አባላቱ በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በሚገኙ ኦሮሞዎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል ሲል መግለጫ ማውጣቱ የሚታወስ ነው ለልዩ ኃይል “ያልተገባ ስም” የሚሰጡ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታረሙም የክልሉ የሰላምና የህዝብ ደኅንነት ጉዳዮች…

ኤርትራ “ለብሔራዊ ደህንነቴያሰጋኛል” በሚል በድንበር አካባቢ ያሉ የኢትዮጵያ ቦታዎች መያዟን ጠ/ሚ ዐቢይ ገለጹ

“ሕወሓት ማለት በነፋስ ላይ የተበተነ ዱቄት ማለት ነው” ሲሉ ጠ/ሚኒስትሩ ተናግረዋል “የአማራ ልዩ ኃይል የፌደራሉ መንግስት ጠይቆት ነው ወደ ህግ ማስከበር ዘመቻው የተቀላቀለው” ብለዋል ጠ/ሚ ዐቢይ “ከውጊያው በፊት እንደምናሸንፍ ለሕወሓት…

የሱዳን ወታደራዊ ክንፍ ከሱዳን ሕዝብ ፍላጎት በተቃረነ መልኩ ለሶስተኛ ወገን ጥቅም እየሰራ ነው – ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

መጋቢት 14 ቀን 2013 የሱዳን ወታደራዊ ክንፍ የሱዳንን ሕዝብ ፍላጎት በተቃረነ መልኩ ለሶስተኛ ወገን ጥቅም እየሰራ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለፁ። ቃል አቀባዩ በፖለቲካ፣ በምጣኔ…

“ባለፈው ስምንት ወር ያገኘነው የኤክስፖርት እድገት ባለፉት 20 ዓመታት ከነበረው ጋር አይነጻጸርም” ጠ/ሚ ዐቢይ

ኢትዮጵያ ተበድረው መክፈል ያልቻሉ ከሚባሉ ሀገራት ተርታ የተጠቀሰችው ከጂዲፒ አንጻርመሆኑን ገልጸዋል ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የወጪ ንግዱ የ21 በመቶ እድገት ማሳየቱንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት…

ኤርትራ የአውሮፓ ህብረትን ውሳኔ “መሰረተ ቢስ” ስትል አጣጣለች

ህብረቱ ለዚህ ውሳኔ የሚያበቃ “የሞራልም ሆነ የህግ ልዕልና”እንደሌለውም ገልጻለች ኤርትራ የአውሮፓ ሕብረትን የማዕቀብ ውሳኔ ተቃወመች፡፡ ውሳኔውን የተመለከተ መግለጫን ያወጣው የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ህብረቱ ተፈጽመዋል ካላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተያያዘ በኤርትራ…

የአሜሪካ ሴኔት በኢትዮጵያ ላይ ውሳኔ እንዲያሳልፍ የሚጠይቅ አንድ ሰነድ ለሴኔቱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ መቅረቡ ታወቀ፡፡

ይህንን ረቂቅ ውሳኔ ያዘጋጁት የኢንዲያና ሴናተር የሆኑት ጀምስ ሪስች እንደሆኑ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ረቂቁም ‹‹ሴኔት ሪዞሉሽን 97›› ወይንም ‹‹S. Res. 97›› የሚል መጠሪያ የተሰጠው ነው፡፡ ይህ ረቂቅ ገና በሂደት ላይ…

ዶናልድ ትራምፕ የግላቸውን የማህበራዊ ትስስር ገፅ ይዘው ሊመጡ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2013 የአሜሪካው የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የግላቸውን ማህበራዊ ትስስር ገፅ ይዘው ሊመጡ መሆኑን አማካሪያቸው አስታውቀዋል። አማካሪያቸው ጀሶን ሚለር ዶናልድ ትራምፕ በሁለት እና ሶስት ወራት ውስጥ ወደ…

አቶ ስብሃት ነጋ እና ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማን ጨምሮ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 አቶ ስብሃት ነጋ፣ ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ፣ አምባሳደር አባይ ወልዱን ጨምሮ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት ያቀረበው የአዲስ አበባ ማረሚያ…

ሠራዊቱን የማይወክል ተግባር የሚፈጽሙት ተጠያቂ ሊደረጉ ይገባል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ

የሃገር መከላከያ ሠራዊቱን እሴቶች የማይወክል ተግባር የሚፈጽሙትን ተጠያቂ ማድረግ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ጠዋት ከብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጋር መሰብሰባቸውን ገልጸዋል፡፡ “በስብሰባው ሠራዊታችን የሠላም ጠባቂ እና…

ሳሚያ ሱሉሁ ዛሬ የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ይፈፅማሉ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 የታንዛኒያ ምክትል ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን የሀገሪቱ ስድስተኛ ፕሬዚዳንት ሆነው ዛሬ ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ፡፡ ምክትል ፕሬዚዳንቷ ዛሬ ቃለ መሃላ የሚፈጽሙት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት…

አሜሪካ በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ተጨማሪ 52 ሚሊዮን ዶላር የሰብአዊ ዕርዳታ ማድረጓን ገለጸች

መጋቢት 10/2013 ዓም አሜሪካ በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ተጨማሪ 52 ሚሊዮን ዶላር የሰብዓዊ ዕርዳታ ማድረጓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን ገለጹ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የዜጎች የሰብዓዊ ሁኔታ ትኩረት የሚያስፈልገው…

ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር የግድቡን የውሃ ሙሌት በተያዘው ጊዜ አከናውናለሁ ማለቷን ግብፅና ሱዳን ተቃወሙ

ሱዳን 2ኛ አማራጭ መጀመሯ እና አሜሪካ ከሦስቱም ሀገራት ጥያቄ ካልቀረበላት ጣልቃ እንደማትገባ መገለጹ ይታወሳል ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ክረምት ሁለተኛውን ዙር የሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ከማከናወን የሚያግዳት ምንም ምክንያት እንደሌለ እና በተያዘው ጊዜ…

በትግራይ የጋራ ማጣራት ለማድረግ ከኢትዮጵያ የቀረበውን ጥያቄ መቀበላቸውን የተመድ የሰብአዊ መብቶች ኃላፊ ገለፁ

አምነስቲን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በትግራይን ክልል ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን ሲገልፁ ነበር ኃላፊዋ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት አማካኝነት የቀረበውን የ ’አብረን እናጣራ’ ጥሪ በበጎ ተቀብለውታል በትግራይ ክልል ተፈጽመዋል የተባሉ…

“ሱዳን ከሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ወደ ሁለተኛ አማራጭ እየተሸጋገረች ነው” ሱዳናዊው የፖለቲካ ተንታኝ ኦስማን ማርጋኒ

“ከዚህ በኋላ ሱዳን አዲስ የዲፕሎማሲ ዘዴን የምትጠቀም አይመስለኝም” ሲሉም ገልጸዋል “ካርቱም በግድቡ ጉዳይ የአዲስ አበባን የማይለዋወጥ አቋም እንደምትረዳ ተስፋ አድርጋለሁ” ሱዳናዌ ተንታኝ ሱዳን የውሃ ብክነትን ለማካካስ የጥንቃቄ እርምጃዎችን የመውሰድ እቅድ ወደ መተግበር…

በኢትዮጵያ “አደገኛ የሆነ የፖለቲካ ተረኝነት እንዳለ ባልደራስ ያምናል“ የፓርቲው ጽ/ቤትኃላፊ ገለታው ዘለቀ

አሁን ላይ በሀገሪቱ “አደገኛ የሆነ የፖለቲካ ተረኝነት እንዳለ ባልደራስ ያምናል“ ሲሉም የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ጽ/ቤትኃላፊ ገለታው ዘለቀ ተናገረዋል። “የብልጽግና ፓርቲ ሙሉ በሙሉ በኦህዴድ ጥላ ስር ያለ ነው“ የሚሉት ኃላፊው፣…

ሶስቱም ሀገራት ካልጋበዟት በግድቡ ድርድር መግባት እንደማትችል አሜሪካ አስታወቀች

አሜሪካ፤ ዓባይ ለግብፅ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ እና ሱዳንም ወሳኝ ወንዝ ነው ብላለች ኢትዮጵያ፣ሱዳን እና ግብፅ ካልጋበዟት በሕዳሴ ግድብ ድርድር ላይ መሳተፍ እንደማትችል አሜሪካ አስታወቀች የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የቀጠናዊ ጉዳዮች ቃል…

የህወሃት ቡድን ምዕራባውያንን ለማግባባት ገንዘብ በመክፍል ሐሰተኛ መረጃ እንደሚያሰራጭ ተጋለጠ

መጋቢት 8/2013 የህወሃት ቡድን ምዕራባውያንን ለማግባባት በውጭ ያሉና በኢትዮጵያ ይሰሩ የነበሩ ግለሰቦችን ገንዘብ በመክፈል የሀሰት መረጃ እንደሚያሰራጭ አንድ የኢሜይል መረጃ አጋለጠ። ኢትዮጵያን ዳይጀስት ባገኘው መረጃ የህወሃት ቡድን መሪ የሆኑት ዶክተር…

የቱኒዚያው ፕሬዝዳንት ወደ ሊቢያ አቀኑ

ሊቢያ ከሰሞኑ በአብዱል ሃሚድ ዲቤባ የሚመራ ጊዜያዊ የአንድነት መንግስትን መመስረቷ የሚታወስ ነው ፕሬዝዳንቱ ከጋዳፊ ከስልጣን መወገድ በኋላ ወደ ሊቢያ ያቀኑ የመጀመሪያው የቱኒዚያ መሪ ናቸው የቱኒዚያው ፕሬዝዳንት ካይስ ሰዒድ ለይፋዊ ጉብኝት ዛሬ…

ኦነግ በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ ምርጫ ቦርድ የሚፈቅድለት ከሆነ እንደሚሳተፍ አስታወቀ

መጋቢት 8 ቀን 2013 የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ህጋዊና ሰላማዊ ትግልን አማራጭ በማድረግ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተፈቀደለት በምርጫው እንደሚሳተፍ አስታወቀ። በቦርዱ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የተመራጮች ምዝገባ ቀን መገባደዱ ይታወቃል።…

በአባይ ወንዝ 86 በመቶ ድርሻ ያላትን ኢትዮጵያ የፍትሃዊ ተጠቃሚነት መብቷን ማንም አይነጥቃትም – አቶ ደመቀ መኮንን

መጋቢት 8 ቀን 2013 “በአባይ ወንዝ 86 በመቶ ድርሻ ያላትን ኢትዮጵያ የፍትሃዊ ተጠቃሚነት መብቷን ማንም ሊነጥቃት አይችልም” ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ። የታላቁ የኢትዮጵያ…

በሎስ አንጀለስና አካባቢው ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የተለያዩ የአሜሪካ መንግስት አካላት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ያልተገባ ጫና በመቃወም ሰልፍ አካሄዱ

መጋቢት 8 ;2013 ዓም )በሎስ አንጀለስ እና አካባቢው ነዋሪ የሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያዊ እና ኤርትራዊ አሜሪካውያን የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ በመደገፍ እና የተለያዩ የአሜሪካ መንግስት አካላት በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ…

የጸጥታ ሀይሎች ሁሉንም ስደተኞች በመሰብሰብ “የመጨረሻ ጸሎታችሁን አድርጉ አሉን”

ስደተኞቹ በእስር ቤቱ ያለውን አያያዝ እንዲያስተካክል ተቃውሞ እያሰሙ ነበር በየመን እስር ቤት በረሃብ አዳማ ላይ በነበሩ ስደተኞች ላይ ሀውቲዎች በተኮሱት ከባድ መሳሪያ እሳት መነሳቱን ሂዩማን ራይትስ ዋች ገለጸ ባሳለፍነው ሳምንት በየመን…

በመተከል ዞን እየተወሰደ ባለው የህግ ማስከበር እርምጃ በሰላማዊ

በመተከል ዞን እየተወሰደ ባለው የህግ ማስከበር እርምጃ በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ለሰጡ ታጣቂዎች የተሃድሶ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱ መጠናቀቁን የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥና የግብረ ሃይሉ አባል ብርጋዴር ጄኔራል አለማየሁ ወልዴ ገለጹ። በመተከል…

ኢትዮጵያ 4 አደራዳሪዎች ይግቡ የሚለውን የሱዳን ሀሳብ አልቀበልም አለች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መንግስት ስለጉዳይ በይፋ እንዳልተገለጸለት ገልጿል ሱዳን አደራዳሪ ይሁኑ ላለቻቸው አራት አካላት የአደራድሩን ጥያቄዋን በይፋ አቅርባለች ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ)፣የአውሮፓ ህብረት፣ አሜሪካና የአፍሪካ ህብረት በግድቡ ጉዳይ በአደራዳሪነት ይግቡ የሚለውን…

ህወሓት በሥልጣን ዘመኑ የፈጠረው መርህ አልባ ግንኙነት የምዕራቡ ዓለም ጫና እንዲበረታ ምክንያት ነው – አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ

መጋቢት 7 ቀን 2013 ህወሓት በሥልጣን ዘመኑ የፈጠረው መርህ አልባ ግንኙነት አሁን የምዕራቡ ዓለም በኢትዮጵያ ላይ ጫናውን እንዲያበረታ ምክንያት መሆኑን የኢሳት ጊዜያዊ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ፖለቲከኛ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ…

በየካቲት ወር ከ21 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2013 በየካቲት ወር ከ21 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ዘንድሮ የተገኘው ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ12 በመቶ በላይ ዕድገት…

ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል የታሰሩ የምርጫ 2013 እጩዎች እንዲፈቱ ጠየቀ 47 ፓርቲዎች ተወዳዳሪ እጩ አስመዝግበዋል

ምርጫ ቦርድ የደቡብ ክልል ፖሊስ ያሰራቸውን እጩዎች በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠየቀ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል በመሰቃና በማረቆ ቁጥር 2 የምርጫ ክልል የታሰሩ በግል ለመወዳደር የተመዘገቡት ሁለት እጩዎች እንዲፈቱ ለደቡብ…

ኬንያ ከሶማሊያ ጋር የገባችበትን የድንበር ውዝግብ ጉዳይ ከሚመለከተው ዓለም አቀፍ የፍርድ ሂደት ራሷን አገለለች

ሀገራቱ የሚወዛገቡበት የባህር ላይ ድንበር 160 ሺ 580 ካሬ ኪ.ሜ ስፋት ያለው ሲሆን ትልቅ የነዳጅና ጋዝ ክምችት እንዳለው ይታመናል ናይሮቢ ይህን ያደረገችው ፍርድ ቤቱን በገለልተኛነት በመክሰስ ነው ኬንያ ከሶማሊያ ጋር…