ዜና
Archive

Category: አጫጭር ዜና

የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ አዲስ አበባ ገቡ

የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ አዲስ አበባ ገቡ። አዲስ አበባ ሲገቡም የመከላከያ ሚንስትሩ ዶ/ር አብርሀም በላይ እና የብሔራዊ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን…

ኢጋድ በሶማልያ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት አወገዘ

የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) በሶማልያ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት በጽኑ አወገዘ። በሶማልያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በአጥፍቶ ጠፊ ግለሰብ የደረሰውን የሽብር ጥቃት ተከትሎ የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ መግለጫ…

ቻይና በአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ልትሾም ነው

ቻይና በአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ እንደምትሾም የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ አስታወቁ። የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከኬንያ አቻቸው ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱ ቻይና የምትሾመው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ…

የገና በአልን በላሊበላ ለማክበር እንግዶች ከተማዋ እየገቡ ነው

ገና በአልን በላሊበላ ለማክበር እንግዶች ወደ ከተማዋ እየገቡ ነው። በዓሉን ለማክበር እየገቡ ያሉት እንግዶች በሃገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ናቸው።

ወደ ኮምቦልቻ ከነገ ጀምሮ የመንገደኞች በረራ ይጀመራል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ታኅሣሥ 27 ጀምሮ ወደ ኮምቦልቻ እለታዊ የበረራ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡ አየር መንገዱ በማኅበራዊ ገጹ እንዳስታወቀው ከአዲስ አበባ የሚነሳው እለታዊ የበረራ አገልግሎቱ ረቡዕ ይጀምራል፡፡ የሽብር ቡድኑ…

የሱዳን ጦር ኢብራሂም ኤልባዳዊን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሊሾም ነው

የሱዳን ጦር የቀድሞ የሀገሪቷ ገንዘብ ሚኒስትር የነበሩትን ኢብራሂም ኤልባዳዊ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሊሾም መሆኑን ሲጂቲኤን አስነብቧል፡፡ አብደላ ሀምዶክ ከጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው መልቀቃቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው የሀገሪቱ ጦር ኢብራሂም ኤልባዳዊን በቦታው…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዳግም ወደ ላልይበላ በረራ ጀመረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላልይበላ የሚያደርገውን የሀገር ውስጥ በረራ በድጋሚ በዛሬው ዕለት ጀምሯል፡፡ አሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት በላልይበላ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ከፍተኛ ዝርፊያና ውድመት መፈጸሙን ተከትሎ አየር መንገዱ ወደ ከተማዋ…

ሩሲያ 12 ስኬታማ የኃይፐርሶኒክ ሚሳኤሎች ሙከራ አደረገች

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን የዚርኮን ኃይፐርሶኒክ ሚሳኤሎች በተከታታይ ለ12 ጊዜ በማስወንጨፍ ሀገራቸው ስኬታማ ሙከራ ማድረጓን ገለጹ፡፡ ፕሬዚዳንት ፑቲን ከሀገሪቷ እንዲሁም ከሣይንሥ እና ትምህርት ምክር ቤቶች ጋር በጥምረት ባደረጉት ስብሰባ ላይ…

122 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት ተዘጋጀ

 በገንዘብ ሚኒስቴር የተዘጋጀው 122 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡ ተጨማሪ በጀቱ ለሀገር ደህንነት ማስጠበቂያ፣ ለሰብአዊ እርዳታ፣ በጦርነትና ግጭቶች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ማቋቋሚያ እንዲሁም ለሌሎች አስፈላጊ የመንግስት ስራዎች…

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች መምሪያ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች መምሪያ ዋና ዳይሬክተር ው ፔንግ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ ውይይቱ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ማለትም ከግጭት በኋላ ስለሚደረገው መልሶ ግንባታ…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለእርዳታ ጭነቶች የ20 በመቶ ቅናሽ አደረገ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለእርዳታ ጭነቶች የ20 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አየር መንገዱ ከሚበርባቸው መዳረሻዎች ወደ አዲስ አበባ በሚጫኑ የእርዳታ ጭነቶች ላይ አሁን እየተሰራበት ካለው የጭነት…

በአፍሪካ እስካሁን ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል

ከ55 የአፍሪካ ሀገራት በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ9 ሚሊየን 505 ሺህ በላይ ሰዎች ሲደርሱ፥ በአህጉሪቱ ከ185 ሚሊየን 502 ሺህ በላይ ለሆኑ ሰዎች ክትባት መሰጠቱም ነው የተገለጸው፡፡ በአህጉሪቱ በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች…

ጠ/ሚ ዐቢይ ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ ጋር በስልክ ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በተፈጠረው ግጭት ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም ሁለቱ መሪዎች ባሳለፍነው ህዳር 22 ቀን የመከሩባቸው…

ፕሬዚዳንት ራማፎሳ አሜሪካ ባዘጋጀችው የዴሞክራሲ ስብሰባ ላይ እንደማይካፈሉ ተገለፀ

አሜሪካ ባዘጋጀችው የዴሞክራሲ ስብሰባ ላይ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ እንደማይካፈሉ የፕሬዚዳንት ጽኅፈት ቤቱ ሚኒስትር ሞንድሊ ጉንጉቤሌ አስታውቀዋል። ፕሬዚዳንቱ አሜሪካ በምታዘጋጀው እና በምትመራው ስብሰባ ላይ የማይሳተፉበት ምክንያት እንዳልታወቀም ነው የተመላከተው፡፡…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው ቅዳሜ ወደ ሰመራ በረራ ይጀምራል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጪው ታህሳስ 2 ጀምሮ ወደ አፋር ክልል መዲና ሰመራ እለታዊ የበረራ አገልግሎት እንደሚጀምር በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

ጠ/ሚ ዐቢይ ከጎረቤት አገራት መሪዎች ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስድስት ጎረቤት አገራት መሪዎች ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከጂቡቲ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን መሪዎች ጋር…

ዩናይትድ ስቴትስ ሩሲያ ዩክሬንን ትወራለች በሚል ስጋት “ከባድ የአፀፋ ምላሽ” ለመስጠት እየተዘጋጀው ነው አለች።

ይህ የአሜሪካ ማስጠንቀቂያ የተሰማው ባይደን ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ነው። በተንቀሳቃሽ ምስል እገዛ በተደረገው ስብሰባ ባይደን ሩሲያ ወታደሮቿን እየገነባች መሆኑን ጠቅሰው “ጠንካራ የኢኮኖሚና ሌሎች ቅጣቶች” ሊጣሉ ይችላሉ…

ኦሮሚያ ክልል 950 የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶ አደር እና በማህበር ለተጀራጁ ወጣቶች አሰረከበ

ኦሮሚያ ክልል 950 የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶ አደር እና በማህበር ለተጀራጁ ወጣቶች አሰረክቧል። ትራክተሮቹ በሻሽመኔ ከተማ በሚገኘው ኬኛ የእርሻ መሳሪያዎች ማምረቻ እና መገጣጠሚያ ድርጂት የተገጣጠሙ ናቸው :: ከቀረቡት 950 ትራክተሮች ውሰጥ…

አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከሱዳን ዩኒቨርስቲ ምሁራን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 29 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከካርቱም አልኒሊን እና ከሱዳን ዩኒቨርስቲ ምሁራን ጋር ተወያዩ። ውይይቱም በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካካል ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት…

የዩኤኢ ፋይናንስ ሚኒስትር አረፉ

እስከ ፋይናንስ ሚኒስትርነት በደረሱ ከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃዎችም ላይ አገልግለዋል ሼክ ሃምዳን ምክትል የዱባይ ገዢ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርም ናቸው የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የፋይናንስ ሚኒስትር ሼክ ሃምዳን ቢን ረሺድ አል መክቱም ማረፋቸው…

የመጀመሪያው የትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ጉባዔ እየተካሄደ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2013 የመጀመሪያው የትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ጉባዔ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ጉባዔው በኢትዮጵያ ሲካሄድ በዓይነቱ የመጀመሪያው ሲሆን፤ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ካዘጋጀው የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ ጋር ተጣጥሞ የሚካሄድ ነው ተብሏል፡፡ በጉባዔው…

ምክር ቤቱ 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጀምሯል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2013 5ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በሚያካሂደው 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጀምሯል፡፡ በስብሰባው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ10…

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ጉባኤ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ጉባኤ በኢትዮጵያ ይካሄዳል፡፡ ጉባኤው ከነገ በስቲያ እና ሃሙስ የሚካሄድ ሲሆን የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ እንደ ተቋም የተዘጋጀው የ10…

“በኢትዮጵያ የሚካሄድ የትኛውም ዓይነት አሉታዊ ጉዳይ ያሳስበናል”- ሴናተር ክሪስ ኩንስ፣ የጆ ባይደን መልዕክተኛ

ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር እንዲመካከሩ በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ወደ አዲስ አበባ የተላኩት ዴሞክራቱ ክሪስ ኩንስ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያዩ፡፡ ክሪስ ኩን እና ልዑካቸው…

መከላከያ ሰራዊት ወደ አጣዬ እና አካባቢው እየገባ እንደሚገኝ ተገለጸ

በአጣዬ እና በአካባቢው የተቀሰቀሰው ግጭት አጎራባች ወደሆነው የሸዋሮቢት ከተማ እና አካባቢው የመዛመት ዐይነት ሁኔታ እየታየበት ነው ተባለ፡፡ በሸዋሮቢት ከትናንት ጀምሮ የተኩስ እሩምታዎች እየተሰሙ መሆኑን የከተማው ነዋሪዎች ለአል ዐይን አማርኛ ገልጸዋል፡፡ በዛሬ…

የኮንጎ ሪፐብሊክ እጩ ፕሬዘዳንት በአውሮፕላን ውስጥ ህይወታቸው አለፈ እጩ ተወዳዳሪው የምርጫ ቅስቀሳ አድርገው ነበር

እጩ ፕሬዘዳንቱ ህመም ሲበረታባቸው ወደ ፈረንሳይ በመጓዝ ላይ እያሉ በአውሮፕላን ውስጥ ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል ኮንጎ ብራዛቪል ፕሬዘዳንታዊ ምርጫዋን በማካሄድ ላይ ስትሆን በዚህ ምርጫ ላይ እጩ ፕሬዘዳነት የነበሩት ብሪስ ኮሌላ ህይወታቸው ማለፉን…

ኢሰመኮ በጂማ ዩኒቨርሲቲ ሁከት ፈጥራችኋል በሚል የታሰሩ ወጣቶች በፍርድ ቤት ነጻ ቢባሉም እስካሁን አለመፈታታቸውን ገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እንዳስታወቀው ከየካቲት 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኘውን የወጣት ሙሃመድ ዴክሲሶንና በሱ መዝገብ የተከሰሱትን ሁለት ሰዎችን የፍርድ ቤት ሂደት በቅርበት እየተከታተልኩ ነው ብሏል።ወጣቶቹ…

ዩኤኢ ዝናብን በሰው ሰራሽ መንገድ ለማዝነብ ከእንግሊዝ ተመራማሪዎች ጋር እየሰራች ነው

ከ5 ዓመታት በፊት ለመሰል 9 የምርምር ፕሮጄክቶች የ15 ሚሊዬን ዶላር ድጋፍ ስለማድረጓም ተነግሯል ብ ኒውስ ዘግቧል፡፡ ተመራማሪዎቹ በድሮን ታግዘው ለመተግበር ላዘጋጁት የምርምር ስራ የ1 ነጥብ 5 ሚሊዬን ዶላር ድጋፍ ማድረጓም ተሰምቷል የተባበሩት…

ተመድ 2 ሚሊዬን ደቡብ ሱዳናውያንን ለመርዳት ከ1 ቢሊዬን ዶላር በላይ ገንዘብ ያስፈልገኛል አለ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአምስት አገራት ለተጠለሉ ደቡብ ሱዳናዊያን 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው አስታወቀ። እንደ ድርጅቱ መረጃ ከሆነ ከ2 ሚሊዮን በላይ የደቡብ ሱዳን ዜጎች በኢትዮጵያ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣…

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ ከወለደች በኋላ አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰደችውን ተማሪ አነጋገሩ

መጋቢት 7 ቀን 2013ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ ከወለደች በኋላ አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰደችውን ተማሪ በስልክ አነጋገሩ። ፕሬዚዳንቷ ለተማሪዋ ያላቸውን አድናቆትም ገልጸዋል። የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ የመጀመሪያ…

የፈረንሳይ ፕሬዘዳንት የአስትራዜኔካ ክትባት እንዲቆም አዘዙ

የፈረንሳይ ፕሬዘዳንት የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲውን አስትራዜኔካ የኮሮና ክትባት ቢያንስ ለ24 አሰታት እንዲቆም አዘዋል፡፡ጀርመንን፣ጣሊያንን አየርላንድንና ኔዘርላንድን ጨምሮ ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የደም መርጋትን ያስከትላል የሚል ስጋት በመጨመሩ ምክንያት ተመሳሳይ እርምጃ ወስደዋል፡፡ የአለም ጤና…

በአድማ በተሳተፉ ታክሲዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ

ታክሲዎች ከታሪፍ እና ከቅጣት ጋር በተያያዘ ምክንያት ነው አድማ የጀመሩት ዛሬ በአዲስ አበባ ተሳፋሪዎች ከፍተኛ የትራንስፖርት እጥረት ገጥሟቸዋል በአዲስ አበባ በዛሬው ዕለት ተሳፋሪዋች በታክሲ እጦት ሲንገላቱ ነበር፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከወትሮው…

የቀድሞ ቦክሰኛው ማርቪን በ66 ዓመቱ በድንገት መሞቱ ተገለጸ

የቀድሞው የመካከለኛ ክብደት ቦክሰኛው አሜሪካዊው ማርቨለስ ማርቪን ሀግለር በመኖሪያ ቤቱ በድንገት ማረፉን ባለቤቱ በፌስቡክ ገጿ ይፋ አድርጋለች፡፡ እንደ ባለቤቱ ካይ ጉሬራ መረጃ ከሆነ የቀድሞው ቦክሰኛ በአሜሪካ ኒው ሀምፕሻየር በሚገኘው መኖሪያ…

አየርላንድ የደም መርጋት ያስከትላል በሚል ስጋት አስትራዜኔካ የተባለውን ክትባት አቆመች

አየርላንድ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለዜጎቿ የምትሰጠውን አስትራዜኔካ የተባለ ክትባት ማቋረጧን አስታውቃለች፡፡ ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች የደም መርጋት ምልክት እየታየባቸው ነው በሚል ነው ክትባቱ እንዲቋረጥ የተወሰነው፡፡ ክትባቱ በጊዜያዊነት ነው ለህብረተሰቡ እንዳይሰጥ የታገደው፡፡…

በፌደራል መንግሥት እና በአቡ ዳቢ ፊውቸር ኢነርጂ ካምፓኒ ፒ.ጄ.ኤስ.ሲ

በፌደራል መንግሥት እና በአቡ ዳቢ ፊውቸር ኢነርጂ ካምፓኒ ፒ.ጄ.ኤስ.ሲ-ማስዳር የጋራ መግባቢያ ሰነድ የፊርማ ሥነ ሥርዓት ላይ በመገኘቴ ደስ ብሎኛል። የጋራ መግባቢያ ሰነዱ በጥምረት የ500 ሜ.ዋ ፒ.ቪ ፕሮጀክቶችን በኢትዮጵያ ለመጀመር ያስችላል።…

This site is protected by wp-copyrightpro.com