ዜና

ቅምሻ – ከወዲያ ማዶ # “አታካብዱ!” ሲል የነበረው ብሪያን

Views: 197

የማኅበራዊ ሚዲያ መረጃዎች አደገኛነታቸው ብቻ ሳይሆን ጥቅማቸውም የትየለሌ ነው።

ለምሳሌ ብሪያንን እንውሰድ። ብሪያን እንደ ሌሎች ሰዎች ቫይረሱ ውሸት ነው ብሎ አላመነም። ወይም በ5ጂ የመጣ በሽታ ነው ሲል አላሰበም።

እሱ ያሰበው ቫይረሱ እውነት ሆኖ ሳለ ነገር ግን መገናኛ ብዙሃን ነገሩን ከሚገባው በላይ አጋነውታል። ማኅበራዊ ሚዲያውም እያካበደ ነው ብሎ አሰበ።

ባለቤቱ የአስም በሽተኛ ናት። እርሱ ሾፌር ነበር። ሱፐርማርኬት እየሄደ በነጻነት እቃ ገዝቶላት ይመጣል። ራሱን ማግለል አስፈላጊ ሆኖ አላገኘውም።

ድንገት ቫይረሱ ያዘው። ደነገጠ። ባለቤቱንም ለአደጋ አጋለጣት።

በነገሩ በማዘኑ ወደ ፌስቡክ ገጹ በመሄድ ተናዘዘ። እኔን ያያችሁ ተቀጡ ሲል ጻፈ።

ባለሙያዎች እንደሚሉት በትልልቅ ሚዲያዎች ከሚነገሩ ማስጠንቀቂያዎች ይልቅ እንደ ብሪያን ያሉ ተራ ዜጎች የሚጽፏቸው ነገሮች የተሻለ ውጤትን ያስገኛሉ፤ ተአማኒነታቸውም ከፍ ያለ ነው።

በሐሳዊ ዜና ሕይወት ይጠፋል ሲባል ሐሰት አይደለም

በዚህ ጽሑፍ የተነሱት ምሳሌዎች እንጂ ጠቅላላ ጉዳትን አያስቃኙም። ኢንተርኔት የመረጃ ሱናሚ ነው። ፍሬውን ከገለባ መለየት አይቻልም። የመቆጣጠሪያ መንገዱም ቀላል አይደለም። ትዊተር በትራምፕ ሰሌዳ ላይ ሐሳዊ መረጃ ምልክት ማድረጉ አንድ እርምጃ ቢሆንም ነገሩ ውቅያኖስን በጭልፋ እንደማለት ነው።

ለዚህም ነው ዶ/ር ቴድሮስ የሚመሩት የዓለም ጤና ድርጅት ሐሰተኛ መረጃን ኢንፎዴሚክ ሲል የሰየምው። ራሱን የቻለ በሽታ፤ ራሱን የቻለ ወረርሽኝ ሆኗል ለማለት ነው።

ባለፈው ዓርብ ሁለት ወጣቶች ወደ ኒውዮርክ ኩዊንስ ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል በአምቡላንስ መጡ። አብረው ነበር የሚኖሩት።

“ከአንድ ሰዓት በኋላ አንደኛው ወጣት ዓይኔ እያየ ሞተ” ይላሉ ዶ/ር ፈርናንዶ። ሌላኛው በቬንትሌተር ነው እየተነፈሰ ያለው።

“ለምን ቶሎ ወደ ሐኪም ቤት እንዳልመጡ ስጠይቃቸው የሰጠኝ መልስ ‘ፌስቡክ ላይ ቫይረሱ ተራ ጉንፋን ነው’ የሚል ነገር በማንበባችነው ነው ብሎኛል።”

ቀጣዩ ስጋት እንደው ተሳክቶ ለተህዋሱ ክትባት ቢፈጠር እንኳ ሚሊዮኖች ለመከተብ ፍቃደኛ ላይሆኑ እንደሚችሉ ተገምቷል።

አንዱ ምክንያት በፌስቡክ ገና ከወዲሁ የሚነዛው ወሬ ነው። መንግሥታት የሕዝብ ቁጥርን ለመቀነስ ፈልገው ነው ቫይረሱን የፈጠሩት፤ አሁን ደግሞ በክትባት ሊጨርሱን ነው ብለው የሚያምኑ በርካታ ናቸው።

‘ቢልጌትስ ሀብቱን ለመጨመር ሲል ነው ቫይረሱን ፈጥሮ ክትባቱን ያመጣው’ ሊሉ የሚችሉ ሺህዎች አሉ።

በሴራ ትንታኔ ያምን የነበረው የፍሎሪዳው ብሪያን ከሆስፒታል አልጋ ላይ ሆኖ መልዕክት አለኝ ይላል።

“አትጃጃሉ፤ እኔን አይታችሁ ተቀጡ!”

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com