ዜና

በነገሌ 7 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የሚገመት አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ

Views: 308

ለሁለተኛ ጊዜ 7 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የሚገመት አደገኛ ዕፅ ሲያጓጉዝ የተገኘ ኤፍ ኤስ አር የጭነት ተሽከርካሪና ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የቡሌ ሆራ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ አስተባባሪ ኢንስፔክተር ዓለሙ ይመር እንዳሉት፤ ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር የዋለው በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኦሮ 14467 ኤፍ ኤስ አር የጭነት ተሽከርካሪ ነው፡፡

ይህን አይነት ሕገወጥ ተግባር ሲፈጽም ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፣ ከሻሸመኔ ወደ ሞያሌ ኬንያ 2 ሺህ 233 ኪሎ ግራም ካናቢስ የተባለ አደንዛዠ ዕፅ ሲጓጓዝ በመገኘቱ ነው፡፡

ሚያዝያ 18 ቀን 2012 ዓ.ም በጣቢያው ፈታሾች የተያዘው አደንዛዥ ዕጽ 7 ሚሊዮን 815 ሺህ ብር የሚገመት ነው ተብሏል።

የመቆጣጠሪያ ጣቢያውን ፈታሾች ለማሳሳት ከስር አደንዛዥ ዕጹን ከላይ ደግሞ የቡና ገለባ ጭኖ ከሌሊቱ 6 ሰዓት ሲጓጓዝ እንደተያዘም አስተባባሪው ተናግረዋል።

አሁን በቁጥጥር ስር የዋለው ኤፍ ኤስ አር የጭነት ተሽከርካሪ ባለፈው ህዳር ወርም ኮድ 3 ኦሮ 32161 በሚል ሌላ የሰሌዳ ቁጥር 1 ሺህ 999 ኪሎ ግራም አደንዛዥ ዕጽ ጭኖ ሲያጓጉዝ ተይዞ 100 ሺህ ብር ተቀጥቶ መለቀቁን ኢንስፔክተሩ ገልፀዋል።

አሽከርካሪው የሰሌዳ ቁጥሮችን በመቀያየር ሕገ ወጥ ተግባር በመፈጸሙ ተጨማሪ ክስ ይመሰረትበታል ተብሏል።

ተጠርጣሪው፣ ተሽከርካሪውና አደንዛዥ ዕፁን የተመለከተ የፍትህ አካላት ባካተተ መልኩ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ከአስተባባሪው ገለፃ ለማወቅ ተችሏል።Top of FBottom of Form

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com