ዜና

በአዲስ አበባ የቤት ለቤት ልየታ ምርመራ እየተካሄደ ነው

Views: 245

የኮሮና (ኮቪድ 19) ተኀዋስ ለመከላከል፣ የአዲስ አበባ ከተማ መሥተዳደር የቤት ለቤት ጉብኝት ልየታ ጀመረ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስሩም ክፍለ ከተሞች ተጠናክሮ የሚካሄድ ይሆናል የተባለው የቤት ለቤት ልየታ ምርመራ፣ ለጊዜው ተጋላጭነታቸው ከፍ ያለ ነው የተባሉ አካባቢዎች ላይ ነው የሚያተኩረው ተብሏል።

በዛሬው ዕለት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ፣ በጦር ሓይሎች፣ ወይራ ሠፈር ትኩረት መደረጉን የኢትዮ ኦንላይን የዜና ወኪል ከሥፍራው ተመልክቷል።

የቤት ለቤት የሕክምና ቡድኑ፣ ጥንድ ጥንድ ሆነው በየአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ሲሆን፣ አንደኛው የሕክምና ባለሟል የግል፣ የቤተሰብና የማህበረሰብ መረጃ ሲሰበስብ፣ ሌላኛው የሕክምና ባለሟል ደግሞ የሰዎችን ሙቀትና ጤንነት ሲመረምር እንደ ነበር የዜና ወኪላችን ተንቀሳቅሶ ተመልክቷል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com