ዜና

ቻይና ጉልበቷን ማሳየት ጀመረች

Views: 597

ዓለም በኮሮና (ኮቪድ 19) ተኅዋስ /ቫይረስ ወረርሽኝ በተጨናነቀበት በአሁኑ ሰዓት፣ ቻይና ጉልበቷን ማሳየት ጀምራለች፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው፣ ሆንግ ኮንግ ውስጥ በተደረገ ተቃውሞ፣ የቻይና መንግስት 15 የሀገሩ ተወላጆችን ያሰረ ሲሆን፣ አሜሪካና እንግሊዝ እርምጃውን ተቃውመዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ፣ ባለቤትነቱ አጨቃጫቂ በሆነው የደቡባዊ ቻይና ባህር አካባቢ መርከቦች በመላክና አውሮፕላኖች የማብረር ሰሞናዊ ድርጊቷ፣ ባህሩ ይገባኛል፣ ንብረቴ ነው የምትለውን ታይዋንን አስቆጥቷል፡፡

ይህ ባህር ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን፣ የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል በአካባቢው በመስፈር ቻይና ባህሩን እንዳትቆጣጠር ጥረት ማድረግ ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ቻይና በበኩሏ ባህሩ የግዛቴ አንድ አካል ስለሆነ፣ አሳልፌ አልሰጥም ባይ ናት፡፡

ይህ እንዳለ ሆኖ፣ ሁኔታውን ያባባሰው ኮሮና ቫይረስ መዛመት እንደጀመረ፣ ጉዳዩን ለዓለም ካሰወቁ አገሮች አንዷ የቻይና ባላንጣ የሆነችው ታይዋን ስትሆን፣ ከቻይና ጋር የሚያውስናትን ድንበር በመዝጋትም ሆነ ከቻይና የሚመጡ መንገደኞችን ላለመቀበል በመወሰን የመጀመሪያዋ ናት፡፡

ታይዋን ድንበርዋን ከዘጋች በኋላ፣ ጥብቅ ምርመራና ፍተሻ በማድረግ፣ ኮሮኖ ቫይረስን ከተዋጉና ጉዳቱ እንዲገደብ ካደረጉ አገሮች መካከል አንዷ ናት፡፡ ታይዋን እ.አ.አ እስከ 1949 ዓም የቻይና አካል የነበረች ሲሆን፣ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ሥልጣን ሲይዝ፣ ፔኪንግ የነበረውና ቻይናን ያስተዳድር የነበረው የቻንጋይ ሼክ መንግስት ተሸንፎ ወደ ታይዋን ደሴት ሄደ፡፡

በምዕራብ አገሮች ድጋፍም ራሱን የሚያስተዳድር አገር ሆነ፡፡ ይሁንና፣ እስከአሁን ድረስ የተባበሩት መንግስታት አባልነት ተነፍጓት እንደቆየች ነው፡፡

ታይዋን ከቻይና በጥቂት ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ የምተገኝ ቢሆንም፣ በበሽታው የተየዙት ቁጥር 425 ሲሆን፣ የሞቱ ደግሞ 6 ናቸው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com