ከዜና ባሻገር- ጥንቃቄ ለሁሉ! የእጅ ማጽጃ ፈሳሾችን ተጠቅሞ ወዲያው ወደ ኩሽና መግባት አደጋ እያስከተለ ነው!

Views: 159

ውድ የኢትዮ-ኦንላይን ሚዲያ አንባቢያንና አድማጭ- ተመልካቾቻችን፣ የኮሮና (ኮቪድ-19) ቫይረስ ወረርሺኝ ሥርጭት ለመከላከል ሲባል፣ እጆቻችንን በእጅ ማጽጃ ፈሳሾች (ሳኒታይዘር) ማጽዳት ተገቢና አስፈላጊ ነው፡፡

ሆኖም፣ ፈሳሹ (ተቀጣጣይነት ያለው ‹‹አልኮሆል›› ስላለው)ን ከተጠቀምን በኋላ እጃችን ሳይደርቅ እና/ወይም በውኃ በአግባቡ ሳንታጠብ ኩሽና (ማዕድ ቤት) ገብቶ ምግብ ለማብሰልም ሆነ የሆነ ነገር ለመሥራት ‹‹ስቶቭ››፣ ቡታጋዝ እና እንጨት ወይም ክሰል ማንደድ ጉዳት እያስከተለ ነው፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች እናቶቻችንና እህቶቻችን እንዲሁም የየቤቶቻችን አገልጋዮች፣ በእሳት የመለብለብና የመቃጠል ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑን የዲጂታል ሚዲያ ተከታታዮቻችን በስልክ ገልጸውልናል፡፡

እናም፣ እባካችሁ ባላችሁበት ሥፍራ ሁሉ፣ እናቶቻችንን፣ እህቶቻችንን እና የቤት ውስጥ አገልጋዮቻችንን (ሠራተኞች) አንቋቸው፣ አሳውቋቸው፣ ንገሯቸው!!! በሠላም ኑሩልን፤ ሌሎች እንዲኖሩም ዕድል አስፉ፤ ሠላም!!!

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com