አንደበተ ርትዑ መጋቢ አዲስ እሸቱ ለይቶ-ማቆያ ሥፍራ ገቡ

Views: 2579
  • በጊዮን ለይቶ ማቆያ ሥፍራ 10 ቀን ይቆያሉ!
  • በብሉይ ኪዳን ጊዜ ሰዎች ማዕጠንት በማጠን የበሽታን ተዛማችነት ገትተዋል!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅኔ መምህር የሆኑትና በልዩ-ልዩ ሕዝባዊ መድረኮች ላይ ጥዑመ-ሃሳብ የሚያቀርቡት መጋቢ አዲስ እሸቱ፣ ከሰኞ መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ሳምንት በጊዮን ሆቴል ለይቶ-ማቆያ ሥፍራ መግባታቸው ታወቀ፡፡

መጋቢ አዲስ እሸቱ፣ ቀደም ሲል በአውስትራሊያ/ኒውዝላንድ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኘው የሜልቦርን ከተማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ባቀረበላቸው ግብዣ መሠረት ለአንድ ወር ከአሥራ አምስት ቀን አገልግሎት ሄደው የነበረ ሲሆን፣ በዓለም ላይ በተፈጠረው የኮሮና (ኮቪድ 19) ቫይረስ ሥርጭት አውስትራሊያ የጋራ አምልኮን ስታግድ ጉባዔው ተቋርጦ በ15 ቀናቸው መመለሳቸውን ለኢትዮ-ኦንላይን በስልክ ገልጸዋል፡፡

በኹኔታው ምንም ያይነት መደናገጥ አልተሰማኝም ሲሉ ለኢትዮ-ኦንላይን የገለጹት መጋቢ አዲስ እሸቱ፣ በተቃራኒው ለጸሎትና ምዕላ ሱባዔ እንደገባሁ ነው የምቆጥረው፤ በጊዜውን ለጥሞናና ለንባብ ለንባብም እያዋልኩት ነው ብለዋል፡፡

እንዲህ ዓይነት ወረርሺኝ ዛሬ የጀመረ አይደለም የሚሉት መጋቢ አዲስ፣ ከብሉይ ኪዳን ጊዜ ጀምሮ የሰው ዘርን ሲያጋጥመው የነበረና የምንሻገረው ነው፤ ሙሴ ሦስት ሚሊዮን ህዝብ ይዞ እየመራ ሲወጣ በወረርሺኝ እና በተላላፊ በሽታ ብዙ ሰዎች ይሞቱ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን የሚወጣበት ሕግ ነበረው፤ በዚያ ሕግ ችግሩን ተወጥቶታል፡፡

በጊዜው፣ ለይቶ በማቆየትና በማከም፣ በሽታው ከህመምተኞች ወደ ጤነኞች እንዳይተላለፍ ጥረት ይደረግ ነበር፤ ማይጠንት በማጠን የተላላፊ በሽታን ተዛማችነት ለመከላከል ጥረት ይደረግ ነበር፤ ውጤትም አይተውበታል ሲሉ የቅኔ መምህሩ መጋቢ አዲስ እሸቱ ለዘጋቢያችን በስልክ ገልጸዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com