ዜና

ሚሊኒየም አዳራሽ ለጤና አገልግሎት መስጫነት እንዲውል ሊደረግ ነው

Views: 499

የሚሌኒየም አዳራሽን የጤና አገልግሎት መስጫ አድርጎ ለመጠቀም ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

የኮሮና ቫይረስን ወረርሽኝ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የሚሌኒየም አዳራሽን የጤና አገልግሎት መስጫ አድርጎ ለመጠቀም ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

 

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ የተለያዩ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሚገኙ ሚኒስትሯ ጠቅሰዋል፡፡

 

ዶ/ር ሊያ እንዳስታወቁት በሽታው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ግለሰቦች እና ተቋማት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል ሲል ኢቲቪ ዘግቧል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com