የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ያወጣው መረጃ በስህተት ነው ተባለ

Views: 97

በትላንትናው ዕለት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ባዘጋጀው የኢትዮጵያ የተቀናጀ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) መከታተያና መቆጣጠሪያ መረብ ሲስተም ላይ በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 20 ብሎ የጠቀሰው በስህተት ነው ተባለ፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንዳሉት የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ባዘጋጀው የኢትዮጵያ የተቀናጀ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) መከታተያና መቆጣጠሪያ መረብ ሲስተም ያወጣው መረጃ በስህተት እንደሆነ እና በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 12 ናቸው ብለዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com