ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ትዕዛዝ የተላለፉ ዜጎችን ዐርባ ጅራፍ እገርፋለሁ ብለዋል!

Views: 158
  • ዑጋንዳ የህዝብ መጓጓዣንና የገበያ ሥፍራዎችን አገደች!
  • በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 14 ደርሰዋል!
  • ሱቆች ተዘግተዋል! ሰው ቤቱ ከትሟል!
  • የጭነት መኪናዎች መሠረታዊ ግብዓቶች እንዲያጓጉዙ ተፈቅዶላቸዋል!

አፍሪቃዊቷ አገር ዑጋንዳ፣ ህዝቦቿን ከኮሮና (ኮቪድ 19) ቫይረስ ሥርጭት ለመታደግ፣ የተለያዩ አርምጃዎችን መውሰድ ቀጥላለች፤ በዛሬው ዕለት የሕዝብ መጓጓዣ አገልግሎት የሚሰጡ አቡቶቡስ፣ ሎንቺና፣ ሚኒ ባስ፣ ቦዳ-ቦዳ (ሞተር ባይስክል) እና ሌሎች ህዝባዊ አገልግሎቶችን ሁሉ ለሁለት ሳምንት ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆኑ አድርጋለች፡፡

የጭነት መኪናዎች መሠረታዊ የምግብ ፍጆታና አስፈላጊ የሕክምና እና ለችግሩ ጠቃሚ የአገልግሎት ቁሳቁሶችን ለማዘዋወር ብቻ እንዲውሉ የተፈቀደ ሲሆን፣ የቤት መኪናዎችም እንዲንቀሳቀሱ ተፈቅዶላቸዋል፡፡

የሀገሪቱ መንግሥት ትልልቅ የመገበያያ ሥፍራዎችን ቀደም ብሎ የዘጋ ሲሆን፣ ከምግብና ከመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች አቅርቦት ውጪ ያሉትን ትንንሽ ሱቆች ሁሉ ዝግ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ በዚህ የተነሳም ከተማው ሁሉ ረጭ ማለቱን ከሥፍራው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የመንግሥት የደህንነት ኃይሎችና ሠራዊት ከአስቸኳይ ጊዜ የሕግ ማዕቀፍ ውጪ የሆኑ ግለሰቦችን፣ ማኅበረሰቦችና ኃይሎች ዓዋጁን በማስጠበቅ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡

መንግሥት ከዱባይ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል ኢንቴቤ ዓለማቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ የደረሰውን በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ዜጋውን፣ በምርመራ ከለየ በኋላ፤ የሀገሪቱን ዳር ድንበር በየብስ፣ በውኃ፣ በአየር ከጎረቤት አገራትና ከመላው አለም ዝግ ማድረጉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com