የትግራይ የብልጽግና ፓርቲ 50 አመራሮች ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያ ድጋፍ አደረጉ

Views: 65

ብልጽግና ፓርቲም 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል

50 የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት አመራሮች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለገሱ፡፡

በሀገሪቱ የተለያዩ ስፍራዎች የተለያዩ አካላት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚውል ድጋፍ ማድረጋቸው እንደቀጠለ ነው።

50 የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት አመራሮች ትናንት መጋቢት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ባደረጉት ስብሰባም የቫይረሱ ስርጭትን ለመግታት ለሚደረገው ጥረት እንዲውል የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለግሰዋል።

የብልፅግና ፓርቲ በቅርቡ ባደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ካሰባሰበው ገንዘብ ውስጥ 100 ሚሊየን ብር ቫይረሱን ለመከላከል እንዲውል ለግሷል።

ገንዘቡ በመላው ሀገሪቱ የንፅህና መጠበቂያ መግዛት ለማይችሉ ዜጎች እንደሚውል ተመልክቷል ሲል ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com