ትግራይ ክልል አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ

Views: 20

የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችል ውሳኔ ማሳለፉን አስታወቀ፡፡

ክልሉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ባወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ገበያዎችንና ብዛት ያለው የሰዎችን እንቅስቃሴ የሚገድብ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

በትግራይ ከልል ደረጃ የቫይረሱ ስርጭት የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ በ22 ዋና፣ ዋና ጉዳዮች ላይ ከመከረ በኋላ ሦስት ዐበይት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ማሳለፉን የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ደብረጽዮን ገ/ ሚካኤል (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡

ምክትል ርእሰ መስተዳደሩ በሰጡት መግለጫ በትግራይ ክልል ከገጠር ወደ ከተማ ፣ ከከተማ ወደ ገጠር፣ ከከተማ ወደ ከተማ የሚደረጉ ዝውውሮች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት ታግደዋል፡፡

ሕዝብ የሚበዛባቸው ገበያዎችም እንዳይካሄዱ መታገዳቸውንም ዶ/ር ደብረጽዮን ገልጸዋል፡፡

እንደ ሰርግ እና ተስካር ያሉ ማኅበራዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ጉዳዮችም ለጊዜው እንዳይካሄዱ የክልሉ ሥራ አስፈጻሚ ወስኗል ብለዋል፡፡

ምክትል ርእሰ መስተዳድር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እንዳሉት የተላለፉት ውሳኔዎች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት ተግባራዊ እንሚደረጉ እና በሽታው ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ እየተገመገመ የተለያዩ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ መናገራቸውን የትግራይ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com