የኤርትራ መንግሥት ግብጽ በኤርትራ ደሴት ላይ የባህር ኃይል ልታሰፍር ነው መባሉን ሐሰት ነው አለ

Views: 72

በኤርትራዋ ኖራህ ደሴት ላይ ግብጽ የባህር ኃይሏን ለማስፈር ከኤርትራ ጋር ተስማምታለች መባሉን የኤርትራ መንግሥት ሐሰተኛ ወሬ ነው ሲል አጣጣለው።

‘ዘ አረብ ዊኪሊ’ የተባለው ድረ-ገጽ ከ10 ቀናት በፊት ግብጽ በኤርትራዋ ኖራህ ደሴት ላይ የባህር ኃይሏን ለማስፈር ከኤርትራ ጋር ከስምምነት ለመድረስ ተቃርባለች ሲል ዘግቦ ነበር።

የኤርትራ መንግሥት ግን ባወጣው መግለጫ ይህን “መሠረተ ቢስ ሐሰተኛ ወሬ ነው” ብሎታል።

መቀመጫውን ለንደን ያደረገው ድረ-ገጽ ኤርትራን የተመለከቱ መሠረተ ቢስ የሆኑ መረጃዎች ያስራጫል ያለው የኤርትራ ኢንፎርሜሽን ሚንስቴር።

ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ጨምሮም “የኤርትራ መንግሥት ይህን መሠረት ቢስ የሆነና እውነታውን የማያመላክት ግላዊ አስተያያትን አይቀበልም” ብሏል።

ኖራህ ደሴት ከዳህላክ በሰሜን አቅጣጫ በቀይ ባሕር ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ በደሴቷ ላይ የራሻይዳ፣ አፋር እና ትግረ ብሄር ተወላጅ የሆኑ ኤርትራውያን ይኖሩባታል።

ዘገባው የቢቢሲ ነው

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com