በግብፅ ከ550 በላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተገለጸ

Views: 259

‹‹ሁሉም ወታደሮችና መኮንኖች ስለ ቫይረሱ ስርጭት ለቤተሰቦቻቸው እንዳይናገሩ ተደርጓል››

በግብፅ ከ550 በላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው በጦር ሰራዊቱ አባላት እና በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥና ፍርሀት መፈጠሩ ተነገረ፡፡

በግብፅ ባለፋት ቀናቶች ሁለት የጦር ጀኔራሎችና አንድ የአገሪቱ የመከላከያ ሃይል የኢንጂነሪንግ ዲፓርትመንት ሃላፊ የነበሩ ግለሰብ በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸው እንዳለፈ የሚታወስ ሲሆን፣ከ550 በላይ የአገሪቱ የሰራዊት አባላት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ደግሞ አረቢክ 21 የተሰኘው የአገሪቱን የመረጃ ምንጭ ጠቅሶ ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል።

በግብጽ የፖለቲካ እና ስትራቴጂካዊ ጥናቶች ተቆጣጣሪና የሰነድ ክፍል ኃላፊ መሀመድ ጀማል እንዳሉት ከ550 በላይ የሀገሪቱ የሰራዊት አባላትና ኃላፊዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ይህ ቁጥር ያለማቋረጥ እንየጨመረ እንደሆነ እና በጉዳዩ ላይ ብዙ ሚስጥራዊነት አለ ብለዋል፡፡

በዚህ ቫይረስ የተጠረጠሩት የሰራዊቱ አባላት አብዛኛዎቹ በኢንጅርግ ዲፓርትመንት የሚሰሩ ሲሆን በካይሮ በሚገኘው አልማዛ ወታደራዊ ሆስፒታል እና በሻርዲያ ግዛት ሳካ ሆስፒታል በለይቶ ማቆያ ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የሚድል ኢስት ዘገባ ያመላክታል፡፡

በቫይረሱ የተያዙ የሰራዊቱ አባላት ቁጥር በጨመረ ቁጥር በሰራዊቱ ውስጥ ከፍተኛ ጭንቀትና ግራ መጋባት እንዳለ መሀመድ ጀማል ይናገራሉ፡፡ በተጨማሪም ሁሉም መኮንኖችና ወታደሮች ለቤተሰቦቻቸው ስለ ቫይረሱ ስርጭት መረጃ እንዳይሰጡ ጥብቅ ማስጠንቀቂያዎች ተሰጥቷቸዋል ብለዋል፡፡

የግብጽ ሜጀር ጀነራል ሻፊ አብደል ሀሊም እና ሜጀር ጀነራል ካሊድ ሻልታት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ ይፋ ሲሆን የሰራዊቱ መኮንኖች እራሳቸውን እንዲጠብቁና መረጃዎችን እንዳያወጡ ተግሳጽ ተሰጥቷቸዋል፡፡

የሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቭዥን እንደዘገበው ሁለቱ ጀነራሎች ህይወታቸው ያፈው የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በሚያደርጉት ጥረት እንዳልሆነ እና በቫይረሱም የተያዙት ህዝባዊ ስፍራዎችን ለማጽዳት ከመውጣታቸው በፊት እንደነበር ዘግቧል፡፡

የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታ አል-ሲሲ የጀነራሎቹን በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን ማጣታቸውን ከመናገር ይልቅ ጀነራሎቹ ህይወታቸውን ለሀገራቸውና ለህዝቡ ሲሉ መስዋዕት አድርገዋል የሚል ፕሮፓጋንዳ እየነዙ እንደሆነ እና እውነታው ግን ሌላ እንደሆነ ሚድል ኢስት ሞኒተር ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

እንደ ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ቫይረሱ ሊስፋፋ የቻለው በጦር ኃይሎች የኢንጅነሪግ ክፍል ውስጥ ያሉ አንድ መኮንን ጣሊያን የነበራቸውን ስራ ጨርሰው ሲመለሱ ቫይረሱ ተገኘባቸው፡፡ ሆኖም ግን እኚህ መኮንን ቫይረሱ እንዳለባቸው ሳያውቁ በፊት አሁን በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡትን ጀነራሎች አግኝተው ስለ ጉዟቸው ውይይት አድርገው ነበር፡፡ ከዚያም ሁለቱ ጀነራሎች በሰራዊቱ አመራሮች ስብሰባ ላይ ተገኝተው የሰራዊቱን የኢንጅነርግ ዲፓርትመንት ዋና ኃላፊ ኢሃብ ኤል-ፋር አግኝተዋል እኚህ ባለስልጣን ደግሞ ፕሬዝዳንት አል-ሲሲን እንዳገኙ ዘገባው አመላክቷል፡፡

ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ በዚህ ንክኪ ምክንያት ስጋት ስላደረባው እራሳቸውን አግለው ምርመራ ከተደረገላቸው በኋላ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው የሚታወስ ነው፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com