መላ ለኮሮና ቫይረስ! በአፍ እና በአፍንጫዎት ምሽግ እንዳይዝ በደንብ አጽዱ! (ክፍል ፫)

Views: 124

ሀ/ የኮሮና (ኮቪድ 19) ቫይረስ ወረርሺኝ ሥርጭት ለመግታት፤ (ለተጨማሪ የግርጌ ማስታወሻ አንድ ላይ ያለውን ሊንክ አንብቡ)

 • አዘውትረን እጃችንን መታጠባችን መልካም ነው፡፡
 • አፍና አፍንጫ መሸፈን ደግሞ ጥሩ መከላከከያ ነው፡፡
 • በተለያየ ጭሳ-ጭስ እና በእንፋሎት ቫይረሱን በአየር ላይ ማዳከም ጥሩ ነው፡፡
 • የመድኃኒት እፀዋት ቀቅሎ እንፋሎቱን መታጠን ደግሞ በጣም መልካም ነው፡፡

ለ/ መደበቂያውን አጽዱ

የተባለው ሁሉ እንዳለ ሆኖ፣ ይህ ቫይረስ ከእጅ አልፎ፣ በአየር ውስጥ አልፎ ከገባ በኋላ የመጀመሪያው መደበቂያው አፍ ውስጥ መሆኑን አስተውሉ፡፡ አፍ ውስጥ ከገባ ምሽግ አገኘ ማለት ነው፡፡

አፍ ውስጥ ብዙ ሰዓት ወይም ጥቂት ቀናት ይሰነብታል ተብሎ እየተነገረ ነው፡፡ ስለዚህ፣ ለሌላው መከላከያ ዘዴ በተሰጠው ትኩረት ልክ ለአፍ ጽዳት ትኩረት አድርጉ፡፡ በተቻለ መጠን (ለምሳሌ)፣

 • ከምግብ በፊት እና በኋላ አፍን ሙልጭ አድርጎ ዘወትር ማጽዳት ግድ ነው፤
 • ጠዋት እና ማታ ጥርስን ማጽዳት፣ አፍን ሙልጭ አድርጎ ማጽዳት፤
 • አፍን በሎሚ ፍንካች በቀን ሁለት ጊዜ ማጽዳት ይበጃል፤
 • አፍን እና ጉሮሮን ጭምር በጨው ውሃ በቀን ሁለት ጊዜ ማለቃለቅ፣
 • አፍን ካፀዱ በኋላ፣ የዝንጅብል ፍንካች ማኘክ፣ ጉሮሮን ያፀዳል፣
 • በጤና አዳም እንጨት ጥርስን ማጽዳት፣
 • በየቀኑ አንድ ጊዜ ቀረፋ ወይም ቅርንፉድ ማኘክ፣ አፍ ውስጥ ጥቂት ደቂቃ ከምራቅ ጋር እያገላበጡ ማቆየት እና መትፋት ከዚያ በሌላ ውሃ አፍን ማጽዳት፤

እነዚህን እና የመሳሰሉትን ሌሎችንም ዘዴዎች ተጠቀሙ እና መደበቂያ እና ማረፊያ ምሽግ አሳጡት፡፡

ሐ/ መግቢያ ላይ አስቀሩት

አፍንጫም ሌላው የቫይረሱ ሾልኮ መግቢያው እና ማረፊያው መሆኑን አስቡ፡፡ በተፈጥሮ ፀረ ቫይረስ የሆኑ ቅጠላትን በአፍንጫ ላይ ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡  በሰው ብዛት፣ ወይም በቆሻሻ ምክንያት አስጊ በሆኑ አካባቢዎች ስትደርሱ፣ ለምሳሌ፣ ቀጥሎ ከተጠቀሱት ኃይለኛ ጠረን ካላቸው መዓዛማዎች ውስጥ የምታገኙትን እና አለርጂ የማያስከትሉባችሁን ለጋ ቅጠል፣ አስቀድማችሁ በደንብ እጠቡ እና በቦርሳችሁ ወይም በኪሳችሁ ያዙ፡፡ የግርጌ ማስታወሻ ሁለት  አስፈላጊ ነው ስትሉ  በአፍንጫችሁ በአንዱ በኩል ብቻ ለጥቂት ሰዓት አስቀምጡ፣

 • የጤና አዳም ለጋ ቅጠል፣
 • የዳማከሴ ለጋ ቅጠል፣
 • የአሪቲ (ነጭ ሪያን) ቅጠል፣
 • የአርቲሚሲያ ቅጠል፣
 • የጭቁኝ ቅጠል፣
 • የሴጅ ቅጠል
 • የባሕር ዛፍ ቀንበጥ፣
 • የላቬንደር ቅጠል፣
 • የሎሚ ቀንበጥ፣
 • የናና ቅጠል፣
 • የአጁባን ቅጠል፣
 • ታጌታስ ቅጠል የግርጌ ማስታወሻ ሶስት

በመጨረሻም ቅጠላቱን ከአፍንጫችሁ ውስጥ ሙልጭ አድርጋችሁ አስወግዱ፡፡

በዚሁ ዘዴ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በጥጥ ወይም ስስ ጨርቅ ላይ ጠብ በማድረግ አፍንጫ ውስጥ መወተፍ ይረዳል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ታሞ ከመድቀቅ፣ አስቀድሞ ቫይረሱን ባለበት ማነቅ ይበጀናል!!!

                                               

የግርጌ ማስታወሻ አንድ https://ethio-online.com/archives/7977 ለኮሮና ቫይረስ አማራጭ ህክምናን በየቤታችሁ፡

የግርጌ ማስታወሻ ሁለት  በብዙ የገጠር አካባቢ የነጭ ሪያን  ወይም ጭቁኝ ቅጠል ጆሮአቸው ላይ የሚያስከምጡትን አስተውላችሁ በሆነ፡፡ የመጥፎ ነገር  ሽታ ሲያጋጥማቸው በአፍንጫቸው ሊያሸቱት ዝግጁ ቦታ ማስቀመጣቸው ነው፡፡

የግርጌ ማስታወሻ ሶስት  የሴጅ፣ አጁባን፣ ላቬንደር፣ ታጌታስ  ምስል፣ በዚህ  https://ethio-online.com/archives/4646    ሊንክ ላይ ተመልክቱ፡፡

ምስሉ የተወሰደው https://eyewire.news/wp-content/uploads/sites/2/2020/03/banner-210×97.png

በቀለች ቶላ

(የእጽዋት ተመራማሪ እና ደራሲ)

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com