ጠ/ሚ ዐቢይ ለደህንነት ሲሉ ሠራተኞቻቸውን አሰናበቱ

Views: 171

የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የኮሮና (ኮቪድ 19) ቫይረስ ሥርጭት ለመግታት፣ ከግማሽ በላይ ሠራተኞቹ ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንት ከቤታቸው ሆነው ሥራቸውን እንዲያከናውኑ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ዛሬ ረቡዕ መጋቢት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ኮሮና (ኮቪድ 19)ን ለመከላከል የወጣውን የሚኒስቴሮች ምክር ቤት ውሳኔን ተከትሎ፣ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ሠራተኞች ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሰጡት መመሪያ መሠረት፣ አማካሪዎችን ጨምሮ ከ289 የጽ/ቤቱ ሠራተኞች መካከል፣ 184 ሠራተኞች ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ከቤታቸው ሆነው ሥራቸውን የሚከውኑ ይሆናል።

ይህም ከቤት ሆኖ የሚሠራውን ሠራተኛ ከአጠቃላዩ 64 በመቶ ያደርገዋል ተብሏል።

የፌደራል መንግሥት ተቋማትም የኮሮና (ኮቪድ 19) ሥርጭትን ለመግታት ይሄንኑ አካሄድ የሚከተሉ ይሆናል።

እነዚህ ርምጃዎች በሕዝብ የትራንስፖርት መገልገያ ውስጥ የሚኖረውን መጨናነቅ ለመቀነስ ታስበው የሚፈጸሙ ናቸው።

ስለዚህ፣ የመንግሥት ሠራተኞች ከቤት የመሥራቱን ፖሊሲ በጥብቅ ተገንዝበው በቤታቸው ሊቆዩ ይገባል ተብሏል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com