በኢ-ፍትሓዊ ኹኔታ የታሰረውን ጋዜጠኛ ኮሮና ቫይረስ አስፈታው

Views: 90

በኢትዮጵያ፣ በኢ-ፍትሓዊ ኹኔታ የታሰረው የዕንቁ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቀ፣ በኮሮና (ኮቪድ 19) ቫይረስ ሥርጭት ሥጋት ሳቢያ፣ በምህረት ሊፈታ ነው፡፡ የጋዜጠኛው ባለቤት ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ባለቤቷን ለመቀበል እያመራች መሆኗን ለኢትዮ-ኦንላይን ገልፃለች፡፡

በኢትዮጵያ የኮሮና (ኮቪድ 19) ቫይረስ ወረርሽኝ ሥርጭትን ለመግታት ለ4011 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል፡፡

ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ ቀደም ሲል ያሳትመው የነበረው ዕንቁ መጽሔት በህወሓት/ኢሕአዴግ በሕገ-ወጥ መንገድ ተወንጅሎ ሲከሰስ የመጽሔቱ ሥራ አስኪያጅ ከሀገር በመሰደዱ እርሱ (በውክልና) የመጽሔቱን ሕትመት ከማስቀጠሉ ጋር የተያያዘ ነው፤ በወቅቱ የስድስት መጽሔቶችና አንድ ጋዜጣ የሥራ ባልደረቦች በፖለቲካዊ ጫና ሀገር ጥለው መሠደዳቸው ይታወሳል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ሆነው በቅርቡ የተሾሙት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ቀደም ሲል በሚንሥትርነት ይመሩት የነበረው የገቢዎች ሚንሥትር ውንጀላ 7 ዓመት ተፈርዶበት ማረሚያ ቤት ከወረደ ወራት ተቆጥረዋል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ ለታራሚዎች ምህርት ሲያደርጉ እንደተናገሩት፣ “አንድ ጋዜጠኛ ከዚህ በፊት በምህርት አጠቃላይ የሀገራችን ጋዜጠኞች በሚታዩበት ሰዓት ጉዳዩ አልታየም ነበር።

በውጭ ቆይቶ በኋላ ወደ ሀገር ውስጥ ሲመጣ ተፈርዶበት ማረሚያ ቤት ውስጥ ነው ያለው። እስካሁን ድረስ ባለው የመረጃ ማጥራት ሂደት የቆየ ነው፤ ከለውጡ በኋላ ነው ፍርዱ የተወሰነበት፡፡

ስለዚህ፣ ይሄም ጋዜጠኛ ታይቶ እንዲወጣ፣ ይቅርታ የተደረገበት ሁኔታ አለ። በቅድመ አንድ አመት የቀራቸው የሚለው ውስጥ ስለማይካተት ነው የሱን ለብቻው ልገልፅላችሁ የፈለኩት ብለዋል።

ስለዚህ፣ በቀሪው ሌሎች የሀገራችን ጋዜጠኞች ባየንበት ማዕቀፍ መታየት ስላለበት፣ የእርሱም ‘ፍቃዱ ማህተመወርቅ’ እንዲታይ የተወሰነበት ሁኔታ አለ ብለዋል።” ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

በይቅርታው የተካተቱት ታራሚዎች በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስር ባሉ አምስት ማረሚያ ቤቶች ማለትም በቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት፣ ቂሊንጦ፣ ሸዋ ሮቢት፣ ዝዋይ እና ድሬድዋ የሚገኙ ታራሚዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

 

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com