የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች እንደ ሀገር ሊደረግ ለሚችል ጥሪ ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ፡፡

Views: 79

የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች በቀጣይ እንደአገር ሊደረግ ለሚችለው አገራዊ ጥሪ ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ በተለይ የህክምና ተማሪዎች ያሏቸው ዩኒቨርስቲዎች ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ፡፡

የትምህርት ተቋማቱም ቢሆኑ ባሉበት ክልል ለሚደረግላቸው ማንኛውም ጥሪ መድረስ እንዲችሉ ዝግጅታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ዩኒቨርስቲዎችም ተማሪዎቻቸውን ወደ ዋና ዋና ከተሞች ድረስ እንዲሸኟቸው፣ አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የትራንስፖርት ወጪ ድጋፍ እንዲያደርጉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ከሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዚዳንቶች ጋር በጉዞ እቅዳቸው ላይ የቪዲዮ ኮንፈረንስ አካሂዷል፡፡

በዚህም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ጋር በመተባበር ጉዞውን እንዲያስተባብር ተወስኗል።

ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከዩኒቨርስቲዎች ወጥተው መሄድ ለማይችሉ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲዎች እንደየራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ የምግብ ቤት ሠራተኞችን አስገብተው እንዲያስተናግዱ እና በጉዞ ወቅት መኪኖችን ከማፅዳት ጀምሮ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲኖርና ዩኒቨርስቲዎች በቅንጅት እንዲሰሩ አቅጣጫ መሰጠቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com