አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ሸኘ፤ ቀድሞ የወጡትን ወደ ጊቢ አላስገባም አለ

Views: 98

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ሁሉ በግዳጅ ከትምህርት ገበታ አሰናብቶ ሸኘ፤ ቀደም ብሎ ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ጊቢ የወጡትን ደግሞ በጭራሽ አላስገባም ሲል በፌዴራል ፖሊስ ተከላከለ፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የኮሮና (ኮቪድ 19) ቫይረስ ሥርጭት ለመግታት፣ በልዩ-ልዩ ትምህርት ክፍል (ካምፓስ) ተሰብስበው በመማር ላይ የነበሩ ተማሪዎቹን የግዳጅ መልቀቂያ-ቅጽ እያስሞላ ማስወጣት ጀመረ፤ ከዶርም ውጪ ቤተ-ዘመድ ጋር ሆነው በተመላላሽ ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎቹን ደግሞ ወደ ዩኒቨርሲቲው ቅጥር ጊቢ አላስገባም ብሎ በፌዴራል ፖሊስ ተከላክሏል፡፡

‹‹ዩንቨርሲቲው ተማሪዎች ወደ ግቢ ውስጥ እንዲገቡ ኃላፊነቱን መውሰድ ስለማንችል ከግቢ መውጣት እንጂ ወደ ውስጥ መግባት አትችሉም›› ተብለናል ሲሉ እቃቸው ከዶርማቸው (የማደሪያ ክፍላቸው) ለማውጣት የዩንቨርስቲው በር ላይ የቆሙ ተማሪዎች ለኢትዮ ኦንላይን ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በራሱ ወጪ የመጓጓዠ መኪኖችን የመደበ ሲሆን፣ በአንድ አካባቢ የሚጓጓዙ ተማሪዎች እየተመዘገቡ ወደ ተመደቡበት አቡቶቡስ ያመራሉ፡፡

በአሁኑ ጊዜ የኢትዮ-ኦንላይን ዘጋቢዎች ከሥፍራው እንዳስተዋሉት በርካታ ተማሪዎች ቅጽ ሞልተውና ሻንጣዎቻቸውን ሸክፈው እየወጡ ሲሆን፣ ከጠዋቱ 12፡30 ሰዓት ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲው ቅጥር ጊቢ ለመግባትና ቅጽ ሞልተው ዕቃዎቻቸውንና ሻንጣዎቻቸውን ለማውጣ እየሞከሩ ሚገኙ ከ200 በላይ ተማሪዎች በጊቢው ጥበቃዎችና በፌዴራል ፖሊስ ታግተው ከግቢ ውጪ ይገኛሉ፡፡

አዲስ አበባ የኒቨርሲቲ በሠሌዳ ላይ ባወጣው ማስታወቂያ ተማሪዎች በዛሬ መጋቢት 16 እና በነገው 17 ቀን 2012 ዓ.ም ጊዜ ውስጥ የግዳጅ የመልቀቂያ ቅጽ ሞልተው ዕቃዎቻቸውንና ሻንጣዎቻቸውን ይዘው መውጣት አለባቸው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና (ኮቪድ 19) ቫይረስ ተጠርጣሪ ሰዎች ሃያ ደርሰዋል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com