ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለኮቪድ-19 ድንገተኛ ሁኔታ የሚያገለግል ብሔራዊ አቅርቦት አፈላላጊ ኮሚቴ አቋቋሙ

Views: 89

ጠቅላይ ሚኒስትሬ ለኮቪድ19 ድንገተኛ ሁኔታ ዝግጅት የሚውል ገንዘብ እና ሌሎች አቅርቦቶችን የሚያሰባስብ ብሔራዊ የአቅርቦት አፈላላጊ ኮሚቴ አቋቁመዋል።

መንግሥት ጠቀም ያለ በጀት መደቦ የመጨረሻው አስከፊ ሁኔታ ቢከሰት ለመቋቋም የሚያስችሉ ግብአቶችን በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ሆኖም ግን በእንዲህ ያለው ጊዜ የእያንዳንዱን ግለሰብ አስተዋጽኦ የሚፈልግ ስለሆነ እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ጊዜ ውስጥ ስናልፍ፣ በድል አድራጊነት ለመወጣት የሚያስችሉን በኅብረት እና በሚገባ በመቀናጀት የምናደርጋቸው ጥረቶች ትልቅ ቦታ አላቸው ተብሏል።

ተረጋግቶ አስተዋጽኦ ማድረግ’ን በቀዳሚነት ተግባራዊ በማድረግ የብሔራዊ ኮሚቴው አባላት የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለብሔራዊው የኮቪድ19 አቅርቦት ማሰባሰቢያ እንደለገሱ ከጽህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com