በኢትዮጵያ ከአራት ሺህ በላይ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገላቸው

Views: 103

የኮሮና ወረርሽኝን ለመግታት ለ4011 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በፌደራል ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ለ4011 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንደሚፈቱ ጠቅላይ ዓቃቢተ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።

በይቅርታው የተካተቱ ታራሚዎች

1ኛ. እስከ 3 ዓመት የሚደርስ ቀላል እስራት የተፈረደባቸው ታራሚዎች

2ኛ. በማረሚያ ቤት ሆነው አንድ ዓመት የአመክሮ ጊዜ የሚቀራቸው ታራሚዎች

3ኛ. በግድያ ወንጀል ያልተከከሰሱ የሚያጠቡ እና ነፍሰ-ጡር እናት ታራሚዎች

4ኛ. ከግድያ በመለስ የተለያዩ ወንጀሎች ውስጥ የተሳተፉ የውጭ ሀገር ዜጎች እንዲለቀቁ እና ወደ የመጡበት ሀገሮች እንዲላኩ መወሰኑን ጠቅላይ ዓቃቢተ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል።

በይቅርታው የተካተቱት ታራሚዎች በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስር ባሉ አምስት ማረሚያ ቤቶች ማለትም በቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት፣ ቂሊንጦ፣ ሸዋ ሮቢት፣ ዝዋይ እና ድሬድዋ የሚገኙ ታራሚዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com