የኮሮና ቫይረስ በሽታን ቻይና ቀድማ አውቃ ለመደበቅ በመሞከሯ በሚል ክስ ተመሰረተባት

Views: 105

በሀገረ አሜሪካ ላስ ቬጋስ ግዛት የሚገኝ የጥብቅና ድርጅት ኮሮና ቫይረስን ቻይና አስቀድማ አውቃ ለማድበስበስ በመሞከሩዋ ክስ ተመሰረተባት፡፡

ክሱ የተመሰረተው የቻይና መንግስት የኮረና ቫይረስ በውሃን ከተማ ሲቀሰቀስ መጀመሪያ ምልክቶቹን አይተው ያስጠነቀቁ የህክምና ሰዎችን በማሰር እና በማስፈራራት ስለ ቫይረስ በወቅቱ ማሳወቅ ሲገባት አላሳወቀችም በሚል እንደሆነ ላስ ቬጋስ ሪቪው ጆርናል ዘግቧል፡፡
በላስ ቬጋስ የሚገኘው ይህ የጥብቅና ድርጅት የቻይና መንግስትን፣የአገሪቱን ጤና ሚኒስቴር እና ሌሎች ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉ ቢሮዎችን ከሷል፡፡

በላስ ቬጋስ እና ኤሊኖይስ በሚገኙ አራት ድርጅቶች ስም የተከፈተው ክስ ቻይና ከትሪሊየን በላይ ሀብት በአሜሪካ ስላላት የፍትሐ ብሄር ክሱ ውጤት ካገኘ የጉዳት ካሣውን ለማግኘት ተስፋ ያደረገ ሲሆን ክርክሩ በቀላሉ እንደማይቋጭ ከወዲሁ ግምት አለ።

ጠበቃ ሮበርት ኢልጌት ለዜና አውታሮች በትላንትናው ዕለት እንደተናገሩት ክሱ የቀረበው በቻይና መንግስት ላይ እንጂ ህዝቡ በዚህ ክስ ተጠያቂ አይደለም ብለዋል፡፡

ይህ ክስ በታህሳስ ወር በውሃን ያሉ ሰዎች ህይወታቸው ማለፍ ሲጀምር የሀገሪቱ መንግስት መረጃው ለማገድ፣ የተመዘገቡ መረጃዎችን ለማጥፋትና ምርመራውን ለማቆም ሞክሯል የሚል እንደሆነ ጠበቃው ተናግረዋል፡፡

አክለውም በታህሳስ ወር መጨረሻ የቻይና መንግስት ለዓለም የጤና ድርጅት እንዳሳወቀው ‹‹የሳምባ ምች በሽታ›› ባልታወቀ ምክንያት ተክስቷል በማለት ጉዳዩ በጣም ከዘገየ በኋላ ጥቆማ አቅርቧል ብለዋል፡፡

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ሞርጋን ኦርቶጉስ እና በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ሁዋ ቹንግዚ በቅርቡ ባደረጉ የትዊተር ልውውጥ ላይ የቻይናዋ ቃል  አቀባይ እንዳሉት የኮሮና ቫይረስ በቻይና ከተከሰተበት ወቅት ጀምሮ ሀገሪቷ መረጃዎችን ለአሜሪካ አሳውቃለች ብለዋል፡፡

ቻይና ለተከሰተው በሽታ ቀድማ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ባለማሳወቋ በሰዎች ህይወት እና በዓለም ኢኮኖሚ ላይ የቢሊየን እና ከዛ በላይ ዶላር ኪሳራን እንዲደርስ በማድረጓ ልትከሰስ ይገባታል ተብሏል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com