አሽከርካሪው እና ረዳቱ በቁጥጥር ሥር ውለዋል

Views: 41

በአዳማ ከተማ “በኮሮናቫይረስ ምክንያት ረዳቱን መልስ አይጠይቁ” የሚል መልዕክት ለጥፈው የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩት አሽከርካሪ እና ረዳት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

የምዕራብ ሸዋ ዞን የትራፊክ ቁጥጥር ክፍል ኃላፊ የሆኑት ኢንስፔክተር እስማኤል አባድር “አሽከርካሪው ከተሳፋሪዎች በሕገ-ወጥ መንግድ ገንዘብ ለመሰብሰብ ጥረት አድርጓል” ብለዋል።:

“መልስ አጥጠይቁ ማለት ዘረፋ ነው” ያሉት ኢንስፔክተሩ፤ ረዳቱ እና አሽከርካሪው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን እና ምረመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ኢንስፔክተሩ ጨምረውም ማህብረሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት ሲጠቀም እራሱን ለቫይረሱ እንዳያጋልጥ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርበት አስታውሰዋል ሲል ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com