ከሳውዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ የነበሩ 390 ኢትዮጵያውያን ወደመጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

Views: 834

ከትናንት በስቲያ ማለትም እሑድ መጋቢት 13 ቀን 2012 ዓ.ም 390 ገደማ ኢትዮጵያውያንን ይዞ ከሳውዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ የጀመረ የሳውዲ አየር መንገድ አውሮፕላን ወደመጣበት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡

መረጃው እንደሚያመለክተው ይህ የበረራ ቁጥሩ SV-3618 የሆነ እና ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ይዞ ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ ያደረገው አውሮፕላን ወደ ጅዳ ተመልሶ እንዲያርፍ ተደርጓል ሲል ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ዘግቧል።

አብዛኞቹ ተሳፋሪዎችም በህገ-ወጥ መንገድ ሳውዲ የገቡ፣ ከእስር ቤት የተለቀቁ እንዲሁም ጥቂት በፍቃደኝነት ወደ ሀገር ለመመለስ የፈለጉ ነበሩ።

በጉዳዩ ላይ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘሁት መልስ እንደሚያመለክተው ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ሳውዲ አረቢያ በብዛት ስደተኞችን ከሀገሯ እያስወጣች ትገኛለች።

“ግን ደግሞ ይህ በቅንጅት እየተሰራ ያለ አይደለም። በተለይ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ጥንቃቄ ያስፈልግ ነበር፣ ምክንያቱም ካለ ምንም ዝግጅት ቢመጡ ወደ ክልሎች መበተናቸው አይቀርም። ያ ዝግጅት ሳይደረግ ዝም ብሎ ማምጣት አይቻልም። ካሁን በሁዋላ የሚመጡትን ግን ምርመራ እንዲደረግላቸው እና የኳረንቲን ስፍራ እንዲጠቀሙ ይደረጋል” ይላል የሚኒስቴሩ መረጃ።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com