የግብፅ ሶስተኛው ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው አለፈ

Views: 198

የግብፅ ጦር ኃይሎች የኢንጂነሪንግ ባለስልጣን ዋና ሃላፊ ሚጀር ጀነራል ማህሙድ ሻሂን ህይወታቸው ማለፉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ይህም በ 24 ሰዓታት ውስጥ በ ኮሮና ቫይረስ የሞተ ሦስተኛው የግብጽ ከፍተኛ መኮንን ያደርጋቸዋል፡፡

ሚዲል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው የሜጀር ጀነራል መሀሙድ ህልፈተ ህይወት በባልስልጣናት አልተረጋገጠም ብሏል፡፡

ግብጽ ከትላንት በስቲያና ትላንት ሁለት ከፍተኛ የጦር መኮንኖቿ በኮሮና ቫይረስ አጥታለች፡፡

በዚህ የተነሳ የግብጹ ፕሬዝደንት አብደልፈታህ አል-ሲሲ እና ቤተሰባቸው ለሁለት ሳምንት በኳረንቲን እንደቆዩ ሚድል ኢስት ዘግቧል፡፡

እንደ ዘገባው ከሆነ ፕሬዝደንቱ በኳረንቲን እንዲቆዩ ተደርገው የነበረው ሰኞ በኮሮና ቫይረስ ህይወቱ እንዳለፈ ከተነገረው አንድ ከፍተኛ የግብፅ ወታደራዊ አባል ጋር ግንኙነት ስለነበራቸው ነው።

በሌላ ዜና የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ በሀገሪቱ ውስጥ የሚታየውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት መንግስት ተጨማሪ የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስድ አዘዋል ተብሏል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት የግብፃውያን አስፈላጊ ዕለታዊ ፍላጎቶች ችግር ውስጥ ሳይከት ተጨማሪ የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲተገብር ኃላፊነት ወስዷል ብለዋል ፡፡

ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ የግብፅ ህዝብ የአገሪቱን ደህንነት በሚጠብቅ መልኩ እነዚህን እርምጃዎች ላይ ምላሽ እንደሚሰጥ እምነት እንዳላቸው በአፅንኦት ገለጸዋል፡፡

ግብፅ የአየር ትራፊክ እገዳን ጨምሮ ፣ በመንግስት ተቋማት የሚሰሩ ሠራተኞችን ቁጥር በመቀነስ እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን ፣ ዩኒቨርሲቲዎችን ፣ መስጊዶችንና ቤተክርስቲያኖችን በመዝጋት በሀገሪቱ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሚረዱ ጥብቅ እርምጃዎችን ተግባራዊ አድርጋለች፡፡

በግብጽ እስካሁን በዚህ ቫይረስ 366 ሰዎች ሲያዙ 19ኙ ህይወታቸው አልፏል ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.1 ዘግቧል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com