ታዋቂው የካሜሩን ሙዚቀኛ ማኑ ዲባንጎ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ህይወቱ አለፈ

Views: 94

ካሜሩናዊ የአፍሮ ጃዝ ሙዚቃ ኮከብ ማኑ ዲባንጎ በኮሮናቫይረስ ህመም ምክንያት ማረፉን ቤተሰቦቹ አስታወቁ።

“የማኑ ዲባንጎ (ፓፒ ግሩቭ) ህልፈትን ይፋ ስናደርግ በታላቅ ሃዘን ውስጥ ሆነን ነው” ያሉት ቤተሰቦቹ፤ የዲባንጎ ህይወት ዛሬ መጋቢት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ያለፈው ዓለምን እያስጨነቀ ባለው የኮቪድ-19 ቫይረስ ምክንያት መሆኑንም አመልክተዋል።

የሙዚቀኛው ቤተሰብ የማኑ ዲባንጎ የቀብር ሥነ ሥርዓት ከቤተሰቡ ውጪ ፈጽሞ ማንም እንዳይገኝ የሚፈልጉ መሆኑን ገልጸው፤ ነገር ግን ወደፊት የሚታወስበትን ሥነ ሥርዓት እንደሚያዘጋጁ አሳውቀዋል።

ማኑ ዲባንጎ የአገሩን ባህላዊ ሙዚቃ ከሌሎች ጋር በማዋሃድ አፍሮ ጃዝ የተሰኘውን የሙዚቃ ስልት በመጀመር በኩል ፈር ቀዳጅ እንደሆነ ይነገርለታል።

የ86 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋ የነበረው የታዋቂው ሳክስፎን ተጫዋች ሞት ሲሰማ በአድናቂዎቹ ዘንድ ከባድ ድንጋጤን ፈጥሯል።

በተያያዘም የ30 ዓመቱ የዙምባቡዌ ጋዜጠኛ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሕይወቱ በትላንትናው ዕለው ህይወቱ አልፏል፡፡

የ30 ዓመቱ ወጣት የብሮድካስት ጋዜጠኛ ዞሮሮ ማካምባ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወቱን ማጣቱን ተከትሎ በኮሮና ቫይረስ ወጣት ሊሞት አይችልም ተብሎ የሚነገረውን ሐሰት ያደረገና ዚምባቡዌያውያንን ያስደነገጠ ሆኗል።

ቅዳሜ በቫይረሱ እንደተጠቃ በምርመራ የተረጋገጠው ዞሮሮ የጤናው ሁኔታ በፍጥነት ስላሽቆለቆለ በአገሪቱ መዲና ሀራሬ በጽኑ ሕሙማን ማቆያ ገብቶ ነበር።

በዚምባቡዌ ሦስት በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች የነበሩ ሲሆን፣ የዞሮሮ ሞት በአገሪቱ ያሉትን የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ሁለት አድርጎታል ሲል ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com