‹‹ምዕመናን ባሉበት ሆነው በጸሎት መሳተፍ ይችላሉ››

Views: 66
  • ኮሮና (ኮቪድ 19) ቫይረስ ሥርጭት እንከላከል!
  • በእድሜ የገፉ ሰዎች ቸልተኛ መሆን የለባቸውም!

 

 

የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አቢያተ ክርስቲያናት ሕብረት የኮሮና (ኮቪድ 19) ቫይረስ ሥርጭት ለመግታ በሚደረገው ሀገራዊ እንቅስቃሴን በተመለከተ፣ ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ሳር ቤት በሚገኘው ጽ/ቤቱ መግለጫ ይሰጣል፡፡ ምዕመናን በተለይ ደግሞ በእድሜ የገፉ ሰዎች  በቤተ ክርስቲያናት ተከማችተው ሳይሰባሰቡ ለፈጣሪ ጸሎት ማድረስ ይችላሉ፤ ቸልተኛ መሆን የለባቸውም ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አቢያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝዳንት ፓስተር ፃድቁ አብዶ ለኢትዮ-ኦንላይን በስልክ እንደገለጹት፣ የኮሮና ቫይረስን ሥርጭት ለመግታት በኢትዮጵያ ሃይማኖቶ የጋራ ጉባዔ ላይ በተወሰነው የጋራ ሥምምነት መሠረት ዜጎች መተላለፊያ መንገዱን አውቀው የባህርይ ለውጥ በማምጣት ራሳቸውንና ወገናቸውን እንዲጠብቁ የምናስተምር ይሆናል ብለዋል፡፡

ሕብረቱ ለኢትዮ-ኦንላይን እንደገለጸው፣ ዜጎች ዝም ብሎ መደናገጥ አስፈላጊ አለመሆኑን አውቀው፣ መንግሥት፣ የጤና ጥበቃ ሚንስትር እና የጤና ባለሙያዎችን ምክር በማድመጥ የግልና የጋራ (የአካባቢያቸውን) ጽዳት በመጠበቅ መተላለፊያ መንገዱን መግታት አለባቸው ብለዋል፡፡

ስለዚህ፣ ኮሮና (ኮቪድ 19) ቫይረስ፣ እኛ (አማኝ ስለሆንን) አይነካም የሚል የእምነት ታብዮ አያስፈልግም ያሉት ፓስተር ፃድቁ አብዶ፤ አንዲት ሴትዮ አለችው እንደሚባለው ‹‹እግዚአብሔርንም አምናለሁ፤ ለጥንቃቄ በሬንም እዘጋለሁ›› ብለዋል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ጥንቃቄ ይጠብቅኃል፤ ማስተዋልም ይጋርድኃል›› ይላል ያሉት ፓስተር ፃድቁ፣ መጽሐፉ ጽዳትንም በሚገባ ያስተምራል፤ በወረርሺኝ ጉዳት ሲደርስ ገለል ብሎ የመታከም አስፈላጊነት ሁሉ ያስተምራል ብለዋል፡፡

ቀደም ሲል፣ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ቫይረስ ሥርጭት ሲከሰት፣‹‹ እኛ እንዲህ- እንዲህ ስለሆንን አይነካንም የሚለው ተአብዮ፣ የብዙ ሰዎች ሕይወት ዋጋን አስከፍሎናል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ጠቃሚ መረጃ፡-

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የእርስዎ ጥንቃቄ ለወገንኦት ሁሉ መድህን ነው፤ እጅኦን በሚገባ በሳሙና ይታጠቡ፤ ሳልና ማስነጠስ ሲኖር በማህረብ ወይም በሶፍት ወረቀት አሊያም በክርንኦ አፍና አፍንጫዎን ይከልሉ፤ ሌሎችም ይህንኑ እንዲያደርጉ ይምከሩ፤ በሚንቀሳቀሱበት ሁሉ ማኅበራዊ እርቀት (ፈቀቅ- ይበሉ!) ይጠብቁ፤ ተራርቀው ይቀመጡ፤ ተራርቀው ይሰለፉ፤ ሰዎች ከሚበዙበት ቦታ ራቅ ይበሉ፤ የሰው ልጅ ቀደም ሲል እንዲህ ዓይነት መከራዎችን ተጋፍጦ አልፏል፤ ዛሬም በእርስኦ ጥንቃቄና ትብብር የኮሮና (ኮቪድ 19) ቫይረስ ሥርጭት ተቆጣጥረን እንወጣዋለን፤ እናም በሕይወት እንኖራለን፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com