የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የእጅ ማጽጃ (ሳኒታይዘር) ማምረት ጀመረ

Views: 80

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ መከሰትን እና አሁን ላይ ያለው የእጅ ማጽጃ (ሳኒታይዘር) እጥረትን ተከትሎ የወላይታ ዩንቨርሲቲ የእጅ ማጽጃ ማምረት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

የእጅ ማጽጃው የኮሮና በሽታን ለመከላከል አገልግሎት ላይ እንደሚውልና ምርቱን የሚሰራው የዩኒቨርስቲው የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንደሆነ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል፡፡

ዩኒቨርስቲው በኢትዮጵያ የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር እጥረት መኖሩን ከግምት በማስገባት መስራቱን የኮሌጁ የፋርማሲ ትምህርት ክፍል ኃላፊ መምህር ታምራት ባልቻ መናገራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘሩ ትክክለኛ ኬሚካላዊ ኡደትን ተከትሎ የተሰራ እንደሆነም መምህር ታምራት አክለው ገልጸዋል፡፡

ለጊዜው የኮሮና ቫይረስን ለመከላል በተቋቋመው ግብረ ኃይል ውስጥ ለሚሰሩ የህክምና ባለሞያዎች የሚከፋፈለው ይህ ምርት በቀጣይ በብዛትና በተሻለ ጥራት ይመረታል ተብሏል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com