በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዘ ተጨማሪ አንድ ሰው ተገኘ

Views: 555

በኢትዮጵያ በኮቪድ_19 በሽታ የተያዘ ተጨማሪ አንድ ሰው መገኝቱን እና በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስራ ሁለት (12) መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡

ግለሰቡ የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊ ወጣት ሲሆን ከዱባይ ወደ ሀገር ውስጥ መጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም የገባ ነው ብለዋል፡፡

ግለሰቡ የህመም ምልክት የነበረው በመሆኑ በመጋቢት 13 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ጤና ተቋም የሄደ ሲሆን ተቋሙም ለህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሪፖረት በማደረግ በተደረገለት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል፡፡

ታማሚውም በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገለት ሲሆን ጤንነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ዶ/ር ሊያ ገልጸዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከታማሚው ግንኙነት የነበራቸው 15 ሰዎች በክትትል ላይ ይገኛሉ፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com