በምዕራብ አርሲ ዞን ከወትሮ የተለየ በረዶ ጣለ

Views: 26

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ወቅቱን ያልጠበቀ እና ከወትሮ የተለየ በረዶ ጣለ።

ከወትሮ የተለየ በረዶው ምዕራብ አርሲ ዞን ኮፈሌ ወረዳ አሾካ ቀበሌ መጣሉን የዞኑ የመንግስት ኮሙዪኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በረዶው በአካባቢው ያለውን መንገድ እና መኖሪያ ቤቶች መሸፈኑም ነው የተገለፀው።

በአካባቢው የጣለው በረዶም የትራፊክ እንቅስቃሴውን እያስተጓጎለ መሆኑን የገለፀው ጽህፈት ቤቱ፤ አሽከርካሪዎች በስፍራው ላይ በጥንቃቄ እንዲያሽከረክሩም አሳስቧል ሲል ኤፍ ቢሲ በዘገባው አመላክቷል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com