የወረቀት ላይ ፈተና ሊቀር ነው

Views: 153

የሀገረ አቀፋ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ፣ ከ2012 ዓ.ም በኋላ የወረቀት ላይ ፈተናን እንደሚያስቀርና ስህተት ተፈጥሯል በሚል ውጤት የማስተካከል ሂደት እንደሚቀር አስታወቀ፡፡

 

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሔር ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ላይ እንደገለጹት በፈተና እርማት፣ ፈተናውን ማስተዳደር፣ መፈተንና ውጤት አገላለፅ ድረስ ያሉ ሂደቶችን ዘመናዊ በማድረግ የወረቀት ላይ ፈተና እንደሚቀር አሳውቀዋል፡፡

 

ፈተናን በ‹አይፓድ› መፈተን እንደሚቻልና ከሂደቱ ጀርባ ሊሟሉ የሚገቡ በርካታ ነገሮች ቢኖሩም፣ ኤጀንሲው በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

 

በዘንድሮ ዓመት 450 ሺ የሚጠጉ የ12ኛ ክፋል የመልቀቂያ ፈተና እንደሚወስዱ ይገመታል ያሉት አቶ አርአያ፣ መንግሥት ማሟላት የሚገባውን አሟልቶ ተማሪዎችን የፈተና አሰጣጡን እንዲለማመዱ በማድረግ ፈተናውን በላፕቶፕ፣ በኮምፒውተርና በአይፓድ መስጠት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

 

ባለፉት ዓመታት ኤጀንሲው እድገት አሳይቷል ሲሉ የገለጹት አቶ አርአያ በዚህም አገልግሎቱን አውቶሜት ማድረጉ ነው፤ ማንኛውንም የፈተና መረጃ ተደራጅተው በአውቶሜሽን እንዲቀመጡ ሆኗል ብለዋል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com