“የምግብ ፍጆታ የዋጋ ጭማሪ ሆን ተብሎ የተፈጠረ ነው”

Views: 119

በአዲስ አበባ ከተማ በየጊዜው እየናረ ለሚመጣው የቀን-ተቀን የምግብ ፍጆታ የዋጋ ጭማሪ፣ ዋነኛ ምክንያቱ፣ በዘርፉ ላይ ተሰማሩ ግለሰቦች የሚፈጥሩት ተገቢ ያልሆነ የጥቅም ትስስር ነው ተባለ፡፡

 

ከግንቦት ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ የአትክልትና ፍራፍሬ ዋጋ መጨመሩንና ለአብነት የሽንኩርት ዋጋ ከገበሬው ማሳ ላይ በኪሎ ስድስት ብር ገዝተው በመዲናዋ አዲስ አበባ በኪሎ እስከ አርባ ብር እንደሚሽጡ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድና ልማት ቢሮ የኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዳይሬክተር ተናግረዋል፡፡

 

በዋጋ ንረቱ የሚስተወሉ ችግሮችን ለመፍታት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ዘመቻ መጀመሩንና በሂደቱ 28.7 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የግብርና ምርት በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር መያዙን ቢሮው አስታወቋል፡፡

 

ወጤቱ የተገኘው ከአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ከገቢዎች፣ ከዐቃቤ ሕግ፣ ከፖሊስና ከድንብ አስከባሪዎች ጋር በተደረገው ትብብር እንደሆነና በዘመቻው 62 መኪና አትክልትና ፋራፍሬ፣ 52 ኪሎ ጤፍና ስንዴ በንግድ ውስጥ ምንም ተሳትፎ በሌላቸው ግለሰቦች እጅ መገኘቱን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com