ከቀረጥ ነጻ የገቡ የእርሻ መሳሪያዎችና ተሽከርካሪዎች ዱካቸው ጠፋ

Views: 237

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገር የገቡ የእርሻ መሳሪያዎች እና ተሽከርካሪዎች የት እንደገቡ ዱካቸው እንደጠፋ ክልሉ አስታውቋል፡፡

 

በክልሉ የግል ባለሀብቶች ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገር ያስገቧቸውን 56 የእርሻ ትራክተሮችና 26 መለስተኛ የጭነት መኪኖች የት እንደገቡ እንዳልታወቀ የክልሉ መሬት አስተዳደርና ኢንቨስትመንት ቢሮ የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አህመድ ራማ ተናግረዋል፡፡

 

በተጨማሪም በክልሉ እጣን ለማምረት ተፈቅዶላቸው መሬት የተረከቡ 16 ባለሀብቶች የተሰጣቸውን መሬት አላለሙም በማለት ክልሉ መሬቱን ነጥቋቸዋል፡፡

 

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 711 ባለሀብቶች በእረሻ ኢንቨስትመንት፣ በእጣን ምረትና በማዕድን ዘርፍ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡

 

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com