የዓድዋ ድል በዓል በአሜሪካ ግዛት ይከበራል

Views: 145

በአሜሪካን አገር ሜሪ ላንድ ግዛት ሞንትገሞሪ አውራጃ መጋቢትን “የዓድዋ መታሰቢያ ወር” በማለት ለዘጠነኛ ጊዜ እንደሚያከብር በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ውርስ እና ቅርስ ማኅበር አስታወቀ፡፡

ዓመታዊ የዓድዋ ድል በዓል ዝግጅትን በማስመልከት በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ውርስ እና ቅርስ ማኅበር፣ በፈረንጆች  አቆጣጠር የፊታችን መጋቢት 29 ቀን 2020 ዓ.ም በሚከበረው ፕሮገራም ላይ የታሪክ መምህር እና በተለያዩ ታሪክ ነክ ጉዳዮች ላይ በማህበራዊ ሚዲያዎች ትምህርት በመስጠት የሚታወቁት አቶ ታዬ ቦጋለን ከኢትዮጵያ በክብር እንግድነት አንደሚጋብዝም ከማህበሩ የወጣው መግለጫ አሳውቋል፡፡

በውጭው ዓለም የተወለዱ እና ያደጉ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወላጆች አሜሪካ ውስጥ የተወለዱ እና ያደጉ ወጣቶች ስለ ዓድዋ ድል በዓል መጣጥፎች እንደሚያቀርቡ ነው የተገጸው፡፡

በተጨማሪም በየአመቱ እንደሚደረገው በአርቲስት አለምጸሐይ ወዳጆ የሚመራው የጣይቱ መዝናኛ ማዕከል ተውኔት እና ባህላዊ ዘፈኖችንም እንደተሰናዳ ገልጾ፤ ለመላው ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የግብዣ ጥሪም አስተላልፈዋል፡፡

በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ውርስ እና ቅርስ ማኅበር፣ የዓድዋ ድል በዓልን በማስመልከት የታሪክ ምሁራንን፣ ተመራማሪዎችን እና ታዋቂ ግለሰቦችን በመጋበዝ እና የዋሽንግተን ዲሲ ከተማን እና የሜሪላድ ግዛት ሞንትገሞሪ አውራጃ አስተዳዳሪዎችን የአድዋ ድል የተደረገበትን መጋቢትን ወር “የአድዋ መታሰቢያ ወር” ሆኖ እንዲያውጅ በማስደረግ ላለፉት 8 ዓመታት አመርቂ ዝግጅቶች ማካሄዳቸው ይታወሳል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com