“ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ጉዞ” ዜጎችን በአንድ ላይ አስተቃቀፈ

Views: 294

“ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ጉዞ” በሚል የተዘጋጀው ኮንሰርት፣ የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)ን ሀገራዊ ፍቅር እንደሚያንጸባርቅ አድናቂዎቹ ገለጹ፡፡

የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ዝግጅት በመስቀል አደባባይ የካቲት 14 ቀን 2012 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን፣ 150 ሺ የሚሆኑ ህዝቦች ተገኝተውበታል ተብሎ እንደሚገመት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የሙዚቃ ዝግጅቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ የአንድነትን ተምሰሌት ከመሆኑም ባሻገር፣  የሀገሪቱን ሠንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ምክንያት መሆኑን አድናቂዎች ገልጸዋል፡፡

“በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር” በሰላም እና በፍቅር እንደተጠናቀቀ በቦታው የተገኘው አቶ አሸናፊ ወንድሙ ለኢትዮ ኦን ላይን ገልጸዋል፡፡

አቶ አሸናፊ አያይዘውም፤ ቴዲያችን የፍቅር ሰባኪያችን ነው በማለት አድናቆታውን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ፣ ቴዎድሮስ፤ ምኒልክ፤ ሰብልዬ፤ ጥቁር ሰው፤ የሚሉትን ዘፈኖች ቴዲ አፍሮ ሲጫወት፣ ታዳሚው ህዘብ አብሮ ሲዘፍን መመልከታቸው ኢትዮጵያዊነት በወጣቱ ትውልድ ውስጥ ምን ያህል ጥልቅ ፍቅር እንዳለው መረዳታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዲጄ የሙዚቃ ዝግጅት የተጀመረው የሙዚቃ ኮንሰርት  ከምሽቱ ወደ 2፡30 አካባቢ በአቦጊዳ ባንድ ታጅቦ ቴዲ አፍሮ መድረኩን የተረከበ ሲሆን፣ እስከ ሌሊቱ 6፡30 ድረስ በርካታ ሙዚቃዎችን በመዝፈን ህዘቡን በጥበባዊ ብቃቱ አስደምሟል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com