የፈርኒቸርና የቤተ-ውበት አውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው

Views: 116

የ‹‹ፈርኒቸር›› እና የቤተ-ውበት ዓውደ-ርዕይ በአዲስ አበባ ከተማ ሊካሄድ ነው፡፡ አዘጋጆቹ ‹‹ፕራና ኢቨንትስ›› እና ኢቲ መባቻ ንግድ ኃ/የተ/የግ/ ማኅበር ናቸው፡፡

ሀገራችን ካለችበትን ፈጣን የግንባታ እንቅስቃሴ አንጻር የፈርኒቸርና የቤተ-ውበት ዘርፍ በቂ ትኩረት የሚያሻው በመሆኑ በዘርፉ ለተሰማሩ የሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ኩባንያዎች የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበትና ተጨማሪ የገበያ ዕድል የሚፈጥሩበት ዓውደ-ርዕይ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያ ነው ያሉት ዓውደ ርዕይ፣ በምስራቅ አፍሪካ የንግዱ ማኅበረሰብ በሀገራችን ስለሚመረቱ ምርቶች የጥራት ደረጃ፣ የዋጋ ተወዳዳሪነትን የሚያሳይና የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል እንደሆነም አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡

ዓውደ ርዕዩ ከየካቲት 26 – 28 ቀን 2012 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com