ምክር ቤቱ ምርጫው መካሄድ የለበትም የሚል አቋም ወሰደ

Views: 77

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል የሆኑ ሃምሳ ስድስት አገር አቀፍ እና ክልላዊ ፓርቲዎች፣ ምርጫ 2012 ዓ.ም እንዲራዘም ሊጠይቁ ነው፡፡

ፓርቲዎቹ ለምርጫ ቦርድ ፒቲሽን ፈርመው ሊያስገቡ በሂደት ላይ መሆናቸውን ምንጮች ለኢትዮ-ኦንላይን የገለጹ ሲሆን፣ ሀገሪቱ ምርጫ ለማከናወን የሚያስችል ሁኔታ ላይ አይደለችም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ ምርጫ 2012 ን በሚመለከት በየካቲት 7 ቀን 2012 ዓ.ም ባደረገው ውይይት የተደረሰበትን ውሳኔ በሚመለከት በራስ ሆቴል ነገ ዓርብ የካቲት 13 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ ገዢው ፓርቲ ብልጽግናን ጨምሮ ከሃምሳ ስድስት ፓርቲዎች በላይ አባላ የሆኑበት ምክር ቤት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com