ህወሓት ለጋሽ አገራትን በምርጫው ላይ ጫና እንዳይፈጥሩ እጠረጥራለሁ አለ፣ ዓረና ደግሞ ህወሓት ጫና ፈጥሮብኛል ሲል አቤቱታ አቅርቧል

Views: 126

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው የባለድርሻ አካላት ኮንፈረንስ ላይ የተሳተፉት የህወሓት አባል፣ ምርጫው እንዲከናወን እያገዙ ያሉ ስድስት የዓለማቀፍ ተቋማት ከድጋፋቸው ባሻገር ምርጫው ላይ ተጽዕኖ እንዳይፈጥሩብን ስጋት አለን፣ እንዴት ነው ራሳችንን የምንከላከለው ሲሉ ጠይቀዋል።

በቅርቡ የኤርትራው ፕሬዝደንንት በትግረኛ ቋንቋ በሰጡት መግለጫ ላይ፣ ኢትዮጵያ ምርጫ አያስፈልጋትም፣ ፌዴራሊዝም አያስፈልጋትም፣ ጨዋታው አልቋል (The Game is over) እያሉን ነው።

እኛ ድንበር ተጋሪ ስለሆንን ስጋት አለብን፣ ያሳስበናል ሲሉ የህወሓት ፓርቲ ተወካይ ገልፀው፣ ምርጫ ቦርድ ህወሓት ከብልጽግና ፓርቲ ጋር የሃብት ክፍፍል ሲጠይቅ ቦርዱ ያስተናገደበት ፈጣን ምላሽ እና ምርጫውን ለማከናወን ብዙ እርቀት መሄዱን ስለተረዳን እናመሰግናለን ብለዋል።

በአንፃሩ በትግራይ የሚንቀሳቀሰው የዓረና ፓርቲ ተወካይ በበኩላቸው ፓርቲያቸው በትግራይ ክልል በአግባቡ እንዳይንቀሳቀስ ህወሓት ከፍተኛ ጫና እንደፈጠረባቸው ገልጸው ምርጫ ቦርድ በክልላችን ተገኝቶ ችግራችንን የማይመለከተው ፈርቶ ነው ወይ ሲሉ ጠይቀዋል።

የዓረና ፓርቲ ተወካይ የኤርትራ መንግስት ምርጫው ላይ ጣልቃ ገብቶ ተጽእኖ ይፈጥራል ብለን እኛም እንደ ትግራይ ስጋት አለን ብለዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com