‹‹ለኢትዮጵያውያን በምቾትና ደስታ መኖር ሩቅም ብርቅም አይሆንም››

Views: 174

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
በምቾትና ደስታ መኖር ለኢትዮጵያውያን የሰርክ ህይወት እንጂ ብርቅ እንደማይሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ የካቲት 6 ቀን 2012 ዓ.ም ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የተሰባሰቡና ከ15 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በዱባይ አል አህሊ ስታዲየም አግኝተው መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት እንደገለፁት የኢትዮጵያ ሰላምና ብልፅግና ተረጋግጦ ዜጎቿ በምቾትና ደስታ የሚኖሩበት ጊዜ ሩቅም ብርቅም አይደለም፤ ይልቁንስ ይህ ኑሮ የሰርክ ህይወት ይሆናል ብለዋል፡፡

የዜጎች መከበር የሃገር መከበር መሆኑን በመገንዘብ መንግስት የዜጎችን መብት እና ጥቅም ለማስከበር የሚችለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በስነ ስርዓቱ ላይ ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ ሊባኖስ፣ ኩዌት፣ ኦማን፣ ኳታር እና ባህሬን የተውጣጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com