የድምጽ መስጫ ቀን ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓም ሆነ

Views: 116

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሻሻለውን የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ አስታወቀ። የድምፅ መስጫ ቀን ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓም ሆኗል።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በአሁኑ ጊዜ ለባለድርሻ አካላት እንደገለፁት፣ በተከለሰው የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት፣ የድምጽ መስጫ ቀን ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓም ሆኗል።

ቀደም ሲል በጊዜያዊነት ለድምፅ መስጫ ቀን ተይዞ የነበረው ነሐሴ 10 ቀን 2012 ዓም ነበር።

በወቅቱ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች የተጋነነ የዝናብ ወቅት እንደማይሆን የሚትሮሎጂ ትንበያ መኖሩን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ2012 ዓም አጠቃላይ ምርጫ ዋና ዋና ቀናት እና ተግባራት ሲል ባሰራጨው ሰነድ ላይ፣ የምርጫ ክልል ካርታ ይፋ ማድረግ መጋቢት 1 ቀን 2012 ዓም፣ የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር ይፋ ማድረግ መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓም፣ የድምፅ መስጫ ወረቀት ቅደም ተከተልን አስመልክቶ ፓርቲዎች እጣ የሚያወጡበት ቀን ሰኔ 27 ቀን 2012 ዓም እና የምርጫ ድምፅ መስጫ ቀን ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓም መሆኑን ይገልጻል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com