“በኢመደበኛ አደረጃጀቶች ፓርቲዎች ታውከዋል፣ ኢመደበኛ አደረጃጀቶችን የሚደግፉ ፓርቲዎች ደግሞ አሉ”

Views: 145

በሀገሪቱ በተከሰተው የሕግ ጥሰት መበራከትና የሰላም እጦት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሳይቀር በኢመደበኛ አደረጃጀቶች ታውከዋል፣ እንደልባቸው ተንቀሳቅሰው መስራት ተቸግረዋል።

በአንፃሩ አንዳንድ ፓርቲዎች ደግሞ ኢመደበኛ አደረጃጀቶችን ተጠቅመው ሁከት ይፈጥራሉ ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ተወካይ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (ዛሬ) በአዲስ አበባ በኢትዮጵያ አየርመንገድ ስካይላይት ሆቴል እያከናወነ ባለው የምርጫ ባለድርሻ አካላት ኮንፍረንስ ላይ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ተወካይ ዓለሙ ስሜ (ዶክተር) ይህን የኢመደበኛ አደረጃጀት አንዳንድ ፓርቲዎች እየተገበሩት እንደሆነ ይታወቃል ብለዋል።

እነዚህ (በስም ያልተጠቀሱ) ፓርቲዎች በኢመደበኛ አደረጃጀት ሁከት እየፈጠሩ፣ መንግስት ሕግ ለማስከበር ተጠርጣሪዎችን ሲይዝ ደግሞ አባላቶቻችን ተያዙብን ሲሉ አቤቱታ ያቀርባሉ ብለዋል።

መንግስት ደግሞ ሕግ ማስከበር አለበት፣ ሕግን እንዲያስከብር ከማሕበረሰቡ፣ ከምርጫ ቦርድ እና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጫና አለበት ብለዋል የብልጽግና ፓርቲ ተወካይ ዶ/ር ዓለሙ ስሜ።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com